Thursday, December 12, 2013

አቶ አማረ አረጋዊ በጸና መታመማቸው ታወቀ



ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ውስጥ ለ18 ኣመታት በሕትመት ላይ የቆየው የሪፖርተር አማርኛ እና እንግሊዝኛ ጋዜጦች አሳታሚ የሆነው ሚዲያ ኤንድ ኮምኒኬሽን ሴንተር ባለቤትና የቀድሞው የህወሃት ታጋይ አቶ አማረ አረጋዊ በጠና ታመው በአዲስ አበባ በኮሪያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ አማረ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በኮሪያ ሆስፒታል ሲረዱ 10 ቀናት ያለፋቸው ሲሆን ሕመሙ ከበድ በማለቱ ከፍተኛ ክትትል በሚደረግበት በ”አይ ሲ ዩ” ውስጥ መግባታቸው ታውቋል ፡፡ የስራ በልደረቦቻቸው ለመጎብኘት ቢሄዱም ፈቃድ ተከልክለዋል ፡፡

አቶ አማረ በጥቅምት ወር 2006 መጨረሻ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሚዲያ ሊደርስ ፎረም ስብሰባ ወቅት የሰውነት ክብደታቸው ቀንሶና ተጎሳቁለው መታየታቸውን ምንጮቻችን አስታውሰው ሆኖም የበሽታው ምንነት እስካሁን አለመታወቁን ገልጸዋል፡፡

አቶ አማረ ከሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ጋር በገቡት እሰጥአገባ ምክንያት ከአምስት ዓመት በፊት ጭንቅላታቸውን በድንጋይ ተመትተው በሕክምና ዕርዳታ መትረፋቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ሕመም ከዚህ ከቀድሞው ጉዳት ጋር በቀጥታ ይያያዝ፣አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም፡

No comments:

Post a Comment