Thursday, December 5, 2013

የካርቱም ድራማ፡ እነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሕዝቡን ስብሰባ ጠርተው እነርሱ ቀሩ


አብርሃ በላይ ከመቀሌ
(ከካርቱም የተላከልኝ መረጃ ነው፤ እንዳለ ለጥፌዋለሁ።) ትላንት ማክሰኞ (ህዳር 24, 2006 ዓም) በኢትዮጵያ ስዓት አቖጣጠር ልክ ከ10:00ጀምሮ ለተለያዩ የማህበራት አመራሮችና እድሮች ዛሬ ሮብ ለሚደረግ ስብሰባ ሰዉ እንዲጠሩ መልዕኽት ተላለፈ። መልዕክቱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለች የሚመሩትና ሌሎች ሚንስትሮች የሚገኙበት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ5:00 የሚጀመር ስብሰባስላል ከየማህብራችሁ 200 ሰዉ እንድትጋብዙ የሚል በስልክ መደወል ተጀመረ። በተሰጠዉ መምሪያ መሰረት ሁሉም አመራሮች ወደ አባሎቻቸዉ መደወል ያዙ። በአካል ያገኙትም ለሌላዉ እንዲናገር ወሬው ድፍን ካርቱም እንዲዳረስ አደረጉ። የሚገርመዉ ከሃይለማሪያም ደሳለኝ ውጭ ሌሎች ሚኒስትሮች ከባለፈዉ ዓርብ ጀምሮ መግባት ጀምረዋል። እስከ ትላንትና ቀን ሁሉም በየመጡበት ፊና የተለያዩ ስራዎች ሲያከናዉኑ ቆይተዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደግሞ ትላንት ማክሰኞ ምሽት ላይ ካርቱም ገቡ። አይነጋ የለ ለሊቱ ነጋ። በካርቱም የሚገኙው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስትገባ የመጀመሪያዉ በር ስታልፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ/ማህበረሰብ/ ሬስቶራንት አለ ከዛ አልፎ ሌላ ሁለተኛ በር ልዩ ፍተሻ የሚደረግበት አልፎ ኤምባሲዉ ትገባለህ። hailemariam and samora በዚህ መስረት ስብሰባዉ ዛሬ ሮብ ይደረጋል ተብሎ የኮሚኒቲዉ ሰራተኞች ሁሉም ከጥዋቱ 2:00 ስራ ገብተዉ ግቢዉን ሲያፀዱ ዉለዉ ረፋድ ላይ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር 6:00 ዛሬ ስራ ስለሌለ ወደ ቤታችሁ ሂዱ ተባሉ። ጊዜዉ እየገፋ ነዉ ስዓቱ እየተቃረበ ነዉ። ስብሰባዉ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኙዉ መናፈሻ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ምክንያቱ ሁሌም የተለያዩ ፖለቲካዊ ና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚደረጉት በዚሁ አከባቢ ነበር። ዛሬ ግን ሌላ ነገር ተደረገ። ለታዳሚዉ የሚሆኑ ወንበሮች በኤምባሲው ግቢ ዉስጥ በለችሁ ትንሽ ሚዳና ዛፎች ስር ተደረደሩ። ስዓቱ ገፋ ኤምባሲዉ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞ ከዉትረዉ ለየት ባለ አለባበስ ግማሾች ሱፍ በከራቫታ ግማሾቹ ደግሞ ነጭ ቲሸርት በክራቫታ ለብሰዉ ውር ውር ማለት ጀመሩ። የደህንነት ሰዎች ግቢዉን ሁሉ መመርመር ጀመሩ። የተወሰኑ የፀጥታ ሰዎች ከተመደቡ በኋላ ልክ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር 10:30 ወደ ውስጥ መግባት ተጀመረ። ህዝቡ ቀስ ያለ መምጣት ጀመረ። ኤምባሲዉም ሆነ የኮሚኒቲ ሬስቶራንቱ በሱዳን ፖሊሶች ተከቧል። የመጀመሪያዉ በር ፍተሻ ላይ ሰዉ በማህበሩ ወይ በእድሩ እየተጠየቀ ሞቫይሉን በትልቅ ፌስታል ዉስጥ በማስቀመጥ ተፈትሾ ባዶ እጁን ወደ ግቢዉን ይገባል። ከዛም በተጨማሪ የኤምባሲዉ መግቢያ ሁለተኛ በር ጋር ድጋሜ ተፈትሾ ወደ ውስጥ ይገባል። በስተግራ ወደ ተዘጋጁት ወንበሮች ሁሉ ገብቶ ቦታ ቦታዉን መያዝ ይጀምራል። እንድህ እንዲህ እየተባለ እስከ 12:00 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሁሉም ገብቶ ቁጭ ይላል። ሌላዉ የሚገርመዉ ትዕይንት ደግሞ የገዛ ኢምባሲያችን ህንፃ ላይ ተራ ፖሊሶች ወጥተዉ አከባቢዉን እየቃኙ ጠበቃዉን ተያይዘዉታል። በተጨማሪም በኤምባሲዉ ዙርያ በሚገኙት ህንፃዎች የተለያዩ ፖሊሶች ተመደቡ። በተለይ ከኤምባሲዉ አጠገቢ በሚገኝ ሲንድያን ሆቴል አከባቢ ትንሽ እንግዶች በመስኮት ወጣ ገባ ሲሉ በፖሊሶች አርፈዉ እንዲቀመጡ ተነገራቸዉና ተደበቁ። ህዝቡ ተሰብስቦ ዝምታ ሰፍነዋል። መድረክ አከባቢ ለሚኒስትሮችና የተወሰኑ ዲፕሎማቶች ተብሎ 15 ቪ ኣይ ፒ ወንበሮች ተቀምጠዋል። ከነሱም አለፍ ብሎ ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የመድረኩ መሪዎች ይቀመጡባቸዋል ተብለዉ ከነ ጠሬጲዛና ማይክሮፎን የተዘጋጁተዉ ነበሩ። ሁሉም የእንግዶችን መምጣት መጠባበቅ ጀመረ። አንዴ የኤምባሲዉ ደህንነቶች ወደዚህ ወደዚያ ይላሉ። ምንም የማያዉቁ የሱዳን ቦዲጋርዶች /አጃቢዎች/ ገብተዉ ወደዚ ወደዚያ ይላሉ። በመሃል ከተሰበሰበዉ ህዝብ 3 ኤርትራዉያን ተይዘዉ እንዲወጡ ተደረጉ። አሁን ስዓቱ ሄደ ልክ 1:30 ሆነ። እንግዶች አሁንም አልመጡም። ሁኔታዉ ያላማራቸዉ የኤምባሲዉ ዲፕሎማቶች ግራ ተጋቡ። በዚህ መሃል የአምባሳደር አባዲ ዘሞ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ፍረወይኒ እና የኤምባሲዉ ፋይናንስና አስተዳደር አቶ ቀለሙ የሃይለማርያምንና የመድረክ መሪዎች ወንበር ያዙ። ወ/*ሮ ፍረወይኒ ትንሽ ማይክሮፎኑን መታመታ በማድረግ “ሚኒስትሮቹ ወደዚህ አገር የመጡት ዋና አላማ ከሱዳን መንግስት ጋር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ነበር የመጡት። ለዚህም ጉዳይ ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2:00 ወደ ገዳሪፍ /የሱዳን ሌላዉ ከተማ / ሄደዋል። የሄዱበት አላማ ደግሞ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ የ200 ኪሎዋት የኤሌትሪክ ሃይል ለመዉሰድ ለማስወረቅ ነዉ። እዛ ዉለዉ ከዛ በኋላ በሱዳን ወደ ሚሰራዉ መርሃዊ በተባለዉ ቦታ ያለዉ ትልቁ ግድብ ለመጎብኘት ሄደዋል። የዛሬዉ ፕሮግራም እነሱ በፈለጉት መስረት ከህዝቡ ጋር መገናኘት እንፈልጋለን ይህንን ስዓት ያዙልን ብለዉን ነዉ ስንጠብቃቸዉ የዋልነዉ። እስከ ቅርብ ስዓት ድረስ ስንደዉልላቸዉ ነበር። እንደሚመጡ ነግረዉን ነበር። አሁን ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ግን በኢትዮጵያ መንግስት ስም ህዝቡን ይህንን ያህል ስዓት ስላስቆየነዉ ይቅርታ ጠይቁልን ብለዋል። እኔም የመንግስት አካል ስለሆንኩኝ ይቅርታዉ እያስተላለፍኩ ነዉ” ሲሉ ተስብሳቢዉ የተወሰነ ማለትም 10% ሲያጨበጭብ 90% ማጉረምረምና በስሜት መናገር ጀመረ። በዚህ መሃል ፍረወይኒ ንግግርዋን በመቀጠል ይቅርታ ነገ ደሞ ወደ ፈረንሳይ ይበራሉ ስለዚህ 80 ሚሊዮን ህዝብ ሃላፊነት ተሸክመዉ እየዞሩ ነው ስለዚ ምናልባት ለመናገር የምትፈልጉት ነገር ካላችሁ አንድ ሁለት ሰዉ እድል ልስጥ ትላለች። በዚህ ግዜ የመጀመሪያ እጅ አዉጥቶ ዕድል የተሰጠዉ ሼክ ዳዉድ የአማራ ልማት ማህበር ሊቀመንበር እንዲሁም በባለፈዉ ዓመት በሱዳን የኮሚኒቲው ወክሎ ከሌላ አገራት የዲያስፖራ አካላት ጋር በመሆን የህዳሴን ግድብን ጎብኝቶ የመጣ ሰዉ ነዉ። ሼክ ዳዉድ ሲናገር ፥- እኔ በበኲሌ ይህ ይቅርታ በምንም ታአምር አልቀበለዉም ብሎ ሲናገር ህዝቡን ሁሉ አጨበጨበ ንግግሩን በመቀጠል , በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም እና ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም አለመምጣታቸዉ ለማመኑ በሚያስቸግር ሁኔታ ከብዶኛል፡ ይህ ንቀት ነዉ። የሰዉ አገር 200 ሜጋ ዋት ሃይል እሰጡ እየረዱ የኛ ችግር አልታይ ብሎዋቸዉ ነዉ ወይ በጣም በጣም ያሳዝናል። መንግስታችን የሰዉ አገር ፀጥታ እያስከበረ የኛን መብት ማስከብር አለመቻሉ ጉልበት ስላጣ አይመስለኝም በጣም በጣም አዝኛለሁኝ በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት ለመጠየቅ ከያዝኩዋቸዉ ጥያቄዎች አንዱ በቅርቡ እምዱርማን ተብሎ በካርቱም በሚገኙዉ ሰፈር ሰሙኑን አንድ ማዚን የሚባል የሱዳን ጦር መሪ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ ሰጥቶኛል እያለ ወረቀት እያሳየ ሰዎች ከቤታቸዉ እያስወጣ ወደ እስርቤት እየወረወረ ነዉ። ይህ ለምን ይሆናል። ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጭብጨባ በዛ በመቀጠል መኪ ያተባለ የጉራጌ ልማት ማህበር ሊቀ መንበር ሲናገር ችግሩ የኛ ነዉ ሌላ ጊዜ ወደ ኢምባሲ አንመጣም ባለስልጣን ሲመጣ ግን እንዲህ ለምን እንመጣለን ለምን በማህበር አትደራጁም ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ህዝቡ ማጉረምረም እና አንዳንዶችን መሳደብ ጀመሩ። ጩሆት ሆነ በዚህ ማሃል ወ/ሮ ፍረወይኒ እንዲህ ቀጠለች “ ጠላ ቤት አይደለም ኤምባሲ ነዉ እንደፈለጋችሁት አትጭሁ ስነስርዕእት ስነስርዓት እንደማመጥ። መኪ ያለዉን ትክክል ነዉ። እስቲ እንነጋገር በእዉነት እናንተ በአገራችሁ ከፍቶዋችሁ ነዉ የመጣችሁ? ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ መጥፎ ስለሆነች ነው ወይ? በማለት ህዝቡን ለማግባባት ብትሞክርም ህዝቡ ማጉረምረሙ ቀጠለ በመጨረሻም ስብሰባዉ ያለፍሬ በይቅርታ ተበተነ። የሚገርመዉ ሰዉ ሲገባ ሞቫይል በፊስታል ነበር የተሰበሰበዉ። ከስብሰባዉ ሁሉ ሲወጣ ሌላ ግርግር ሆነ። ሁሉም እስኪወጣ ድረስ 2:30 ሆነ፡ ድራማዉ በእንዲህ ተጠቃለለ:: ምንጭ ፥ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10472

No comments:

Post a Comment