Saturday, December 7, 2013

ልብን የሚነካዉ የኢትዮጵያዉያን ጉዞ በሳዑዲ አረቢያ

ከሳዲቅ አህመድ ከተመላሾቹ መካከል አንዱ አባት ያራስ-ቤት ልጁን ጸጉር እየዳበሰ እራሱን በጥልቅ ፈገግታ አንጾ ነበር! ደስ አይልምን?..ልብ ያለዉ ልብ ይበል! በአብዛኛዉ ሰላም ወዳድ ህግ አክባሪ ቢሆንም ጥቂቶች በሚፈጽሙት ደባ ሰለባ ላለመሆን “ዉጡ እስክተባልን ድረስ እነዉጣል” ይላሉ ተጓዦቹ።በሰላም እንደገቡ በሰላም የመዉጣት ግዴታን እየተገበሩ መሆናቸዉን ይናገራሉ። የትም ቢሆን የት እምነትን ተግባሪ መሆናቸዉን እያስመሰከሩ,ለሶላት ሲጠራም ህጻናት እንኳ ከሰጋጆችም ነበሩ። ፤መንፈስንና አካልን ለማነቃቃት እንዳቅሚቲ ኳስን የሚጫወቱም ነበሩ። ብቻ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቢገደዱም ፊታቸዉ ላይ የተስፋ ብርሃንን ,ሆዳቸዉን ባር-ባር ብሎት የእንባ ዘለላን በጉንጮቻቸዉ ላይ ያፈሰሱም ነበሩ። በደል ከበዛባት ኢትዮጵያ በደልን ሸሽተዉ በሙስሊም ወንድሞቻቸዉ ጉያ ቢሸሸጉም ተሸሽገዉ እስኪያልፍ ያለፋል ቢሉም፤ ከዚያ የጥገኝነት ጉያ ዉጡም ተባሉ , ግን ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅልታ፣ እሪታ፣ዋይታ አንባገነኖች የዚህን የመንፈስ-እንባ ካሳ በምድርም ካልያም በወዲያኛዉ አለም መክፈላቸዉ አይቀሬ ነዉ። source. zehabesha

No comments:

Post a Comment