Wednesday, December 4, 2013

በመርካቶ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለአዲስ አበባ ፣ ህዳር 25፣ 2006 – ዛሬ ከሰዓት በኋለ 8:30 ላይ በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የእሳት አደጋ ደረሰ።

በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

እንደ አቶ ንጋቱ እነዚህ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ተክለሃይማኖት ሆስቲታልን ጨምሮ በተለያዩ የህክምና ተቋማት የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል።

9:14 ሲል የስልክ ጥሪ ደረሰን ያሉት አቶ ንጋቱ አደጋው በደረሰበት አቅራቢያ ያሉት የአዲስ ከተማና የአራዳ ጣቢያ ኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጋር በመተባበር እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

እሳቱን ለማጥፋት 12 መኪኖች በስራ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፥ ሌሎች የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎችም ውሃ በማቅረቡ ተሳትፈዋል።

ለአደጋው መባባስ የቤቶቹ አሰራርና በውስጣቸው ያሉ ተቀጠቀጠቀይ ነገሮች በምክንያትነት የተጠቀሱ ሲሆን፥ በንብረት ላይ የደረሰውን አደጋ ከአሁን በኋላ የሚታወቅ መሆኑን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

በአደጋው በሁለት መደዳዎች በሚገኙ ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙ የምገብ ዘይቶች፣ የሽቶዎች እና የጆንያ መጋዘኖችና ሱቆች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል

No comments:

Post a Comment