Sunday, December 8, 2013

አዋሽ ባንክ በሰራተኛ ተዘረፈ::!!!!!!!


Image
ምንጭ >.ላይፍ መጽሄት የህዳር ወር እትሙ::
በዳዊት ሰለሞን
ንጉስ ክፍሌ
በ 1978 ም በ 486 መስራች ባለአክሲዮኞች በ24 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒተል ስራ የጀመረው የአዋሽ ባንክ አ/ማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መልካም ስም ሊያጠፉ የሚችሉና በባንኩ ውሥጥ መዋለ ነዋያችውን ያፈሰሱና ገንዘባቸውን የስቀመጡ ሰዎች የሚያሳስብ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ
የባንኩ የቀድሞው ፕሬዝዳንት አቶ ለይኩን ብርሀኑ ለእስር መደረጋቸው በእሳቸው እግር የገቡት ፕሬዝዳንትም ለሰራተኞች ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የተፈቀደን ብድር በመውሰድ ቤቶችን እየገነቡ በትርፍ በመሸጥ ገቢያቸውን ማደለባቸው ንትርክ ፈጥሮ ቆይትዋል ይህንን መረጃ ለህዝብ ያደረሱ የህትመት ውጤቶች የላይፍ መጽሄትና የእኛ ፕሬስ ጋዜጣ አዘጋጆች በማእከላዊ ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደርዋል
የባንኩ የመጀመሪያ ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ባንኩ አሁን ስለሚገኝበት ሁኔታ በስልክ ተጠይቀው ›››› የሚሰማው ነገር አስደሳች እንዳልሆነ በመጥቀስ በባንኩ ውስጥ ከፍተኛ አክሲዮን ያላችው ግለሰቦችና ለባንኩ እዚህ መድረስ በቅንነት ሲሰሩ የቆዩ ሀላፊዎች ችግሩን ለመቅረፍ መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው መክረዋለወ›››››››››
በአሁኑ ወቅት ያለው አስተዳደር መተቸት ወይም ህገመንግስቱ ያስቀመጠውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን በመጠቀም በጋዜጦች ስለባንኩ አስተዳደሮች መጻፍ ከስራ ለመባረር ምክንያት እንደሚሆን ላይፍ ያነጋገራቸው ሰራተኞች ገልጠዋል በሪፖርተር ጋዜጣ ሀሳባቸውን የገለጡ የባንኩ የህግ ክፍል ሀላፊም በአስተዳደሩ ውሳኔ ለስንብት መዳረጋቸው ተነግሯል::
የባንኩ ፕሬዝዳንትና ምክትላቸው ወሰዱ የተባለው ብድር  ከህገደንብ ውጪ መጠቀማቸውን የተመለከተ መንግስታዊው አዲስ ዘመን በሁለት የነሀሴ ወር ተከታታይ እትሙ መውጣቱን ተከትሎ ባንኩ ምላሽ መስጠቱም አነጋጋሪ ሆንዋል፤፤ ህገወጥ ደረጊት በሁለት ሀላፊዎች እንደተፈጸመበት ጠቅሶ ሳለ መልስ መስጠት ይገባቸው የነበሩት ሁለቱ ሃላፊዎች ቢሆኑም ባንኩ በቀጥታ እንዲናገር መደረጉ ሂደቱን ሲከታተሉ የቆዩ ሰዎችን አስገርሟል፤፤
ባንኩ በዚህ ውጥረት ውስጥ እየተናጠ በሚገኝበት ሰአት ከተለያዩ አዋሽ በንክ ቅርንጫፎች በሰራተኞችና ደንበኛ በመምሰል አካውንት በከፈቱ ሰዎች ጥምረት ዝርፊያ መፈጸሙን ለላይፍ የደረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ እንደ መረጃ ምንጫችን ዘገባ ከሆነ አራት ኪሎ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ቴዎድሮስ ትእግስቱ በተባለ ገንዘብ ከፋይ ማለዳ ለስራ ሲገባ የተሰጠውን 510.000 ብር በላይ ይዞ ተሰውሯል ፤፤ መረጃው እንደደረሰን  በሰራተኛ ዝርፊያ እንደተፈጸመበት የተነገረበትን የባንኩን ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታነህን በስልክ ጠይቀናቸው ‹‹ዜናው እውነት መሆኑን ..ነገር ግን ማንኛውንም አይነት መረጃ የሚሰጠው በማእከል ደረጃ በመሆኑ….. ከዚህ በላይ ምንም ሊነግሩን እንደማይችሉ በመግለጥ ስልኩን ጆሮዋችን ላይ ዘግተውታል፤፤
ገንዘብ ከፋዩ ይህንን ያህል ገንዘብ በኪሱ ይዞ ሊወጣ እንደማይችል የሚገልጡት ምንጮች ዝርፊያው የተፈጸመው በቅንጅት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስርረዋል ፤፤ የአራት ኪሎው ዘረፋ ከመፈጸሙ ቀደም ብሎ እጃችን የገባው መረጃ እንደሚጠቁመው በፒያሳ ጎተራ ሀዋሳና መቻራ ቅርንጫፎች በርከት ያለ ገንዘብ ተዘርፍዋል ፤፤ከዘራፊዎቹ መካከል በባንኩ የሂሳብ መዝገብ በመክፈት በሁለት ባንኮች ዝርፊያ የፈጸሙ ንደሚገኝበት ተጠቅስዋል፤፤
በተደጋጋሚ ዝርፊያ ባንኩ እየተፈጸመበት ከዘራፊዎች እራሱን ለመከላከል የሚያስችል ስልት  መከተል አለመቻሉም አሳሳቢ ነው፤፤
የባንኩ ሃላፊዎች ለላይፍ ኢ-መደባኛ በሆነ ግንኙነት እንደተናገሩት ከሆነ ዝርፊያው የፈጸሙትን ሰዎች  ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል ላይ ይገኛል ብለዋል ፤፤ሃላፊዎቹ ዝርፊያ የሚፈጸመው በእኛ ባንክ ብቻ አይደለም ጋዜጦች አዋሽ ላይ ብቻ ጽኩረጽ ማድረጋቸው  ተገቢ አይደለም የሚል እምነት እንዳላቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ተናግረዋል፤:
ምንጭ ላይፍ መጽሄት የህዳር ወር እትሙ::

No comments:

Post a Comment