Sunday, December 15, 2013

የልመና እድገትና ትራንስፎርሜሽንእሰቲ እንተማመን በአሁኑ ወቅት ስንት ጨዋ አረጋውያን ኑሮ አሸንፏቸው ለልመና ተዳረጉ?? እሰቲ በሚታየው ብቻ እንሂድና ፅዱ ነጭ ነጠላ፣ ሙሉ ልብስ የለበሱ የሰው ዓይን ከስብዕና በታች ሲያደርጋቸው በፊታቸው የሚነበብባቸው አረጋውያን አይደሉም እንዴ አደባባዮቻችን ላይ የፈሰሱት? አቅጣጫ እንደሚጠይቁ ሁሉ ሰው መርጠው በመጠጋት እየተሳቀቁ ችግርተኞች መሆናቸውን ለማሳመን የሚከብዳቸው አረጋውያን ስለመኖራቸው መንግስት እንደምን ይወቅ? ምክንያቱም የኢኮኖሚ እድገት አለ የሚለንና ማንን ተጠቃሚ እንዳደረገ የሚያውቀው ራሱ መንግሥት ተብዬው ነው።

የመንግሥት ባለሥልጣናት እነዚህ ለማኝ አረጋውያን ስለመኖራቸውም ሊያውቁ የማይችሉባቸው ሁለት ምክንያቶች ብቻ ሊኖሩ ይችላሉ
1ኛ ፦በየአደባባዩ የመዘዋወር እንደ "ተራ ሰው" የእነዚህ አሳዛኝ ለማኝ አረጋውያን እጅ ተዘርግቶ አያጋጥማቸውም።
2ኛ ፦የታማኞቻቸውን መረጃ ብቻ ያነፈንፋሉ። ታማኞቻቸው ደግሞ ይህን መናገር ዋጋ አያሰጣቸውም።

ካድሬዎች ሆይ ስለዚህ እውነትን ብቻ ይዛችሁ ትጓዙ እንደሆነ አለቆቻችሁ ይህን ያዩ ዘንድ ልትነግሯቸውና ልታሳውቋቸው ይገባል።

No comments:

Post a Comment