Thursday, December 5, 2013

‹‹ጥቅም›› ላይ ሳይውል የመሸጋገሪያ ድልድይ ፈረሰ


December 5/2013
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጆሊ ባር...
፣ ኮጆሊ ባር ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገርያ የሚያገለግል የብረት መሰላል መሥራቱ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣኑ ይህንን መሸጋገሪያ መሰላል የሠራው፣ በአካባቢው የሚተላለፈው የሕዝብ ብዛት ከሌሎች አካባቢዎች የበዛ ስለሆነ፣ የትራፊክ መጨናነቅና በየቀኑ በተሽከርካሪ አደጋ እየተቀጠፈ ያለውን የሰው ሕይወት (ምንም በተባሉት ቦታዎች እስካሁን የከፋ አደጋ ባይደርስም) ለመታደግ በሚል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ሦስተኛ መሸጋገሪያ ድልድይ የሠራው ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ወደ ራስ መኰንን፣ ወደ አዲሱ ገበያና ወደ አፍንጮ በር (ውቤ በረሃ) በሚወስደው አደባባይ ላይ ነው፡፡
ይህ መሰላል አቀማመጡ ወይም የተሠራበት አቅጣጫ ለተጠቃሚው አመች ባለመሆኑ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሲጠቀሙበት የሚስተዋሉት የጐዳና ተዳዳሪዎች ናቸው፡፡
 በአካባቢው የሚኖሩት የጐዳና ተዳዳሪዎችም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥር ሥር የሚያድሩና በልመና ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ፣ መሰላሉን መፀዳጃ በማድረጋቸው፣ መተላለፊያነቱ ቀርቶ የበሽታ ማስተላለፊያ እስከመሆን ደርሶ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያሠራው የፒያሳው የመተላለፊያ መሰላል በአካባቢው በሚገነባው የቀላል ባቡር ተርሚናል ምክንያት ሰሞኑን እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ የተሠራበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን የሚያስታውሱ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ‹‹አስተዳደሩ የሚመራው በዕቅድና በፕሮግራም ከሆነ፣ ቀላል የባቡር መስመር በቅርብ እንደሚሠራ እያወቀ በዚህን ያህል ወጪ ለምን አሠራው?›› በማለት በትዝብት እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡   ‹‹ጥቅም›› ላይ ሳይውል የፈረሰው መሸጋገሪያ

No comments:

Post a Comment