Thursday, December 19, 2013

ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ለመንግስት ሰራተኛው የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም ተባለ ...

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ መሆኑን እንደሚያዉቁ የተናገሩት ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ሶስትና አራት አመታት በጉልህ የሚታይ ደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር ገልጸዋል።

በየአምስት አመቱ የቤተሰብ ፍጆታቸው በተመረጡ ናሙናዎች ተወስዶ በሚለካው የግሽበት አሃዝ ስሌት መንግስት የኑሮ ውድነቱ በአንድ አሃዝ መውረዱን ቢገልጽም፣ የኑሮ ውድነት ግን አለመርገቡን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳሚያ ዘካርያ እንደተናገሩት የፍጆታ እቃዎች የዋጋ ግሺበት በአንዴ የሚለካው ለአምስት አመታት ነው ።ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በየቀኑ በሚጨምረው ገበያ እና በምርት እጦት እየተማረሩ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ባጠናው ጥናት 57 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ገቢውን የሚያውለው ለምግብ ነክ ጉዳዩች ነው፡፡ አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት እንዴት ያዩታል ተብለው የተጠይቄት ወ/ሮ ሳምያ ” የዋጋ ግሽበቱን አይተው የደሞዝ ማሰተካከያ የሚያደርጉ ሃገራት አሉ ፤ ማስተካከያ ካልተደረገ የዋጋ ግሺበቱን ጫና መቀነሳ አይቻልም” የሚሉት ወ/ሮ ሳምያ ማሰተካካያ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም የመንግስት ፖሊሲ እንደማይፈቅድ ተናግረዋል።

“አሁን ያለውን የኑሮ ውደነት እኔም አውቃለሁ” የሚሉት ሃላፊዋ ፣ ችግሩን ስር እንደሰደደ የምረዳው በርካታ ሰራተኛች ከአዲስ አበባ ለመልቀቅ ማመልከቻ ለማስገባት ሲረባረቡ ሳይ ነው” ብለዋል፡፡

“የወር ደሞዛቸው የቤት ኪራይ መሸፈን እንኳን አለመቻሉ የሚናገሩት ወ/ሮ ሳምያ፣ የህዝብና ቤት ቆጠራ ስናይ አሁን ከዚህ ቤት ሰው ይኖራል ወይ ብለን እንጠይቃለን ” በማለት በኢትዮጵያ ስላለው የኑሮ ውድነት በግልጽ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ” የመንግስት ሰራተኛው በልቶ የማደር ፈተና ውስጥ እና መጠለያ ቤት እጦት እንደሚያንገላታው እናውቃለን” ያሉ ሲሆን፣ ጫናው በርካታ ባለሙያዋች ስራቸውን እንዲለቁ እንዳደረጋቸው መረጃ አለኝ ብለውል፡፡

“በ2006 ዓ.ም ምንም አይነት የደሞዝ ጭማሪ በጀት የለም” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፣ እንዲያውም የፋይናንስ እጥረት እያጋጠመ በመምጣቱ ከቴሌ ኮሚኒኬሺን ፣ ከመብራ ሃይል እና ከውሃ ከሚሰበሰበው በብድር መልክ ተቀብለን ያስተላለፍነው የደሞዝ ክፍያ በርካታ ነው ሲሉ ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡

የደሞዝ ጭማሪው ለመጭዎች ሶስት እና አራት አመታት የሚታይ ጭማሪ ሊኖረው አይችልም ሲሊ ሚኒስትር ዴኤታው ለዘጋቢያችን በስልክ አረጋግጠዋል።

No comments:

Post a Comment