Thursday, December 12, 2013

የዳግማዊ ምኒልክ ሕልፈት 100ኛ ዓመት በአዲስ አበባ ,,,,,,,,,,,,,



ለዘመናዊት ኢትዮጵያ መፈጠር ዓይነተኛ ሚና የነበራቸው ዳግማዊ ምኒልክ ያረፉበት 100ኛ ዓመት ሕልፈት፣ ነገ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከበር የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ተቋም አስታወቀ፡፡

በዓሉ የንጉሠ ነገሥቱ አፅም ባረፈበት የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ በዓታ ታዕካ ነገሥት ገዳም ረፋድ ላይ የሚከበር ሲሆን፣ የንጉሠ ነገሥቱን ተግባራት የሚያወሱ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ በ1888 ዓ.ም. ወርሮ የነበረው የኢጣሊያ ሠራዊት ዓድዋ ላይ የካቲት 23 ቀን በንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ጠቅላይ አዝማችነት ድል መመታቱ ይታወሳል፡፡


ዳግማዊ ምኒልክ በወቅቱ የዘመናዊ ሥልጣኔ መገለጫዎች የነበሩትን ዘመናዊ ትምህርት ቤት፣ ስልክ፣ ሆቴል፣ የባቡር ትራንስፖርት፣ ባንክ፣ ሲኒማ፣ ወዘተ. በማስገባት የሚታወቁ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን የሚኒስቴር አደረጃጀትም መፍጠራቸው ይታወሳል፡፡
ከአፄ ዮሐንስ አራተኛ ሰማዕትነት በኋላ በ1881 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ነሐሴ 11 ቀን 1836 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ አንጎለላ ኪዳነ ምሕረት የተወለዱ ሲሆን፣ ሕይወታቸው እስካለፈበት ታኅሣሥ 3 ቀን 1906 ዓ.ም. ድረስ ኢትዮጵያን መርተዋል፡፡

Source : Ethiopian Reporter

No comments:

Post a Comment