Tuesday, December 31, 2013

ኢትዩጵያ ህጻናትን ወደ ውጭ በጉዲፈቻ ስም በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑዋና መረጃዎች አመለከቱ


December 31/2013
ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት።

በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት የህይዎት ታሪክ ላይ የሚጻፈው ” ተጥለው የተገኙ ወይም ወላጆቻቸውን  በህይዎት ያጡ ” የሚል በመሆኑ በልጆቹ ህይወት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው።

የሴቶች እና ህፃናት ሚኒስቴር የሆኑት ወ/ሮ ዘነቡ መንግስት ህጻናቱን ወደ ውጭ ለማላክ ለፍርድ ቤት የሚያስከፍለው 25 ብር ብቻ መሆኑን ይናገሩ እንጅ፣ የጉዲፈቻ አሳዳጊዎች፣ አንድ ህጻን ለማግኘት እስከ 20 ሺ ዶላር እንደሚከፍሉ ይናገራሉ፡፡

የደቡብ ክልል የሴቶች እና ህፃናት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ  በህፃናት የሚነግዱ አካላት በርካታ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ኢትዩጵያ ያወጣችው አማራጭ የህፃናት መመሪያ በራሱ ሙሉ አለመሆኑንና ለችግሩ መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ይገልፃሉ፡፡ በርካታ የፖሊስ እና የመንግስት አካላት ” ህጻናት ወደ ውጪ ቢሄዱ ይለወጣሉ” የሚል አመለካከት መያዛቸው ስህተት ነው የሚሉት ሃላፊዋ፣ በደቡብ ክልል እንደወጡ የቀሩ ልጆችን የሚጠብቁ እናቶች ዛሬም መንግስትን እያማረሩ ነው ፡፡

ኢቲቪ በቅርቡ ባቀረበው ዘገባ 832 ህጻናት በየአመቱ ከኢትዮጵያ ይወጣሉ ብሎአል። ይሁን እንጅ ከፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው በ2005 ብቻ 2 ሺ 201 ህጻናት ከአገር እንዲወጡ ፈቃድ ተሰጥቷል።
ከአፍሪካ ሀገራ ላይቤራ እና ዛምቢያ ጉዲፊቻን በማገድ ለህጻናቱ በቂ እንክብካቤ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ ጉዲፈቻ ለመጀመርያ ጊዜ የሕግ ከለላ የተሰጠው በ1952 ዓ.ም. በወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ ነው

በጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በጽናት እንታገለዋለን ። ሰማያዊ ፓርቲ ልዩ መግለጫ December 30/2013


አርቲስት ዳንኤል ተገኝ በማጭበርበር ክስ ታሰረ




አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ታሰረ
December 31/2013

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ገመና ድራማ የዶ/ር ምስክርን ገፀ ባህርይ ወክሎ የተወነውና በተለያዩ ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ መታሰሩን የዘሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ገለጹ። አርቲስቱ የታሰረው በካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እስር ቤት እንደሚቆይም ይጠበቃል፡፡

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የአርቲስቱን የክስ መዝገብ በመጥቀስ እንደዘገቡት ዳንኤል የታሰረበት ምክንያት አንዲት ባለትዳር ሴትን ከሌላ ወንድ ጋር ስትሳሳሚ ፎቶ አንስቼሻለሁ ይህንንም ፎቶ በፌስ ቡክ አለቀዋለሁ ብሎ በስልክና በአካል በማስፈራራቱ ነው፡፡ አርቲስቱ ከዚህችው ወ/ሮ ፊልም እሰራለሁ ብሎ 500 ሺ ብር እንደተቀበለና በማጭበርበር ክስ እንደቀረበበት በተለያዩ ሚዲያዎች በዘገቡ ይታወቃል፡፡( ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ቅዳሜ ለንባብ የበቃው ቁም ነገር መፅሄት ሁለቱንም ወገኖች ማነጋገሩ ይታወቃል) ሰለጉዳዩ ተከታትለን እናቀርባለን።







አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ታሰረ
December 31/2013

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ገመና ድራማ የዶ/ር ምስክርን ገፀ ባህርይ ወክሎ የተወነውና በተለያዩ ፊልሞች ላይ                       የተወነው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ መታሰሩን የዘሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ገለጹ። አርቲስቱ የታሰረው በካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ዛሬ                   ፍ/ቤት ይቀርባል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እስር ቤት እንደሚቆይም ይጠበቃል፡፡

             
የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የአርቲስቱን የክስ መዝገብ በመጥቀስ እንደዘገቡት ዳንኤል የታሰረበት ምክንያት አንዲት ባለትዳር ሴትን ከሌላ ወንድ ጋር ስትሳሳሚ ፎቶ አንስቼሻለሁ ይህንንም ፎቶ በፌስ ቡክ አለቀዋለሁ ብሎ በስልክና በአካል በማስፈራራቱ ነው፡፡ አርቲስቱ ከዚህችው ወ/ሮ ፊልም እሰራለሁ ብሎ 500 ሺ ብር እንደተቀበለና በማጭበርበር ክስ እንደቀረበበት በተለያዩ ሚዲያዎች በዘገቡ ይታወቃል፡፡( ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ቅዳሜ ለንባብ የበቃው ቁም ነገር መፅሄት ሁለቱንም ወገኖች ማነጋገሩ ይታወቃል) ሰለጉዳዩ ተከታትለን እናቀርባለን።


የሁሉም ሰው ሥጋት ሕገ-መንግሥቱን ያወጣውም ያጸደቀውም ያንቆለጳጳሰውም ኢህአዴግ ሕገ-መንግሥቱን እንዳይሸሸው ብቻ ነው።

ኢህአዴግ እስካሁን ብዙ ነገር ሸሸ። ቃል ሸሸ። የሰው ስም ሸሸ። የጣት ምልክት ሸሸ። ሸሽቶ ሸሽቶ ከራሱ መሸሽ ግን አልቻለም። የዛሬን አያድርገውና 97 ላይ ኢህአዴግ ቅንጅት የምትለውን ቃል አጥብቆ ፈራት። ጠላት። ሸሻት። እናም በየትኛውም ቃላት ውስጥ ቅንጅት የምትባል አማርኛ ላለመጠቀም ማለ። ጥምረት በሚል ቃል ለወጣት። 

በቀደሙት ‘ቀዳሚ እመቤታችን’ የበላይነት የሚንቀሳቀሰው የሴቶች ጥምረት ሥራውን የምታስተዋውቅለት “ቅንጅት’ የሚል ርዕስ ያላት መጽሔት አሳተመ። የዋሆቹ አዘጋጆች ‘ቃሉ ሌላ ፓርቲው ሌላ’ አሉና መጽሔቱን በየዋህነት በተኑት።የመንግሥት ተሞዳሟጆች ያቺ አደገኛ ቃል በመጽሔት ስም ላይ ሊያውም በራሱ በፓርቲው አባላት መጽሔት ላይ ተንጠላጥላ ስትመጣ ጊዜ ደንብረው ኡኡ… አሉ። ከዚያም ያቺ በስያሜዋ ካልታሰበችበት ቦታ የዋለች መጽሔት ከያለችበት ተለቃቅማ ታጎረች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‘ቅንጅት’ የምትል መጽሔት ድራሿ ጠፋ። ስያሜዋን ለውጣ ሸሸች።

በዚሁ ጊዜ ደግሞ የአሸናፊነት (ቪክትሪ) ምልክት ሆኖ የዘለቀው የሌባና የመሃል ጣት ቪ ቅርጽ ድራሹ እንዲጠፋ ተደረገ። ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በምርጫ ምልክትነት ይጠቀምበት ስለነበር ‘ጣቱን የሚቀስር ጣቱን ይቆረጣል’ በሚል ማስፈራሪያ የአሸናፊነት ምልክቱ ከሁለቱ ጣቶች ወደአንዱ ወደአውራ ጣት እንዲዘዋወር ተደረገ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በዚያን ዘመን የሚገቡበት ጠፍቷቸው የሚኮሩበትን የክለባቸውን አርማ የሸሹበት ጊዜ ነበር። ኢህአዴግ ጣት ሸሸ።
ይህ ፓርቲ ሌላም ሌላም ነገር ይሸሻል። የቴዲ አፍሮ ዘፈንንም ሸሽቶታል። ዶክተር ብርሃኑ ‘ጃ ያስተሰርያል’ የሚለውን ዘፈን እወደዋለሁ ስላሉ ይህ ዘፈን በራዲዮ እንዳይዘፈን ተከለከለ። ቴዲ አፍሮም በፖለቲከኛ ዓይን ታየ። ፓርቲው የእኔ በሆነው ነገር የእሱ ድምጽ እንዳይሰማ አለ። ኮንሰርቱ ጭምር የሚዲያ ሽፋን ተነፈገ።

ይህ ፓርቲ ማንዴላ በኢትዮጵያ ወስጥ የነበራቸው ቆይታ ያለፉትን መንግሥታት በጎ ምግባር የሚያጎላ መስሎ ስለታየው ታሪክ ሸሽቷል። ደቡብ አፍሪካ ሄደው ማንዴላ ቀብር ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን የኢትዮጵያንና የማንዴላን ጥምረት በተመለከተ አንዲት መስመር እንኳን አልተናገሩም። ምክንያቱም ፓርቲያቸው ሲወቅሳቸው ለኖሩት ላለፉት መንግሥታት ስም እንደመስጠትና እውቅናቸውን እንደመጨመር አድርጎ አስቦታልና ታሪክን በተዘዋዋሪ መንገድ ሸሽቶታል። ኢህአዴግ በተለይ ታሪክ ሽሽት ላይ አንደኛ ነው። ‘ኢግኖር’ ሲያደርግ የሚችለው የለም።
ኢህአዴግ እንደፓርቲ የሚቃወሙትን ያገልላል ይባላል እንጂ የሚሸሸው ራሱ ነው። ሌሎች አጠገቡ እንዳይደርሱ ሲያደርግ፣ በሚዲያው ስማቸው እንዳይነሳ ሲያዝዝ ራሱም እየሸሻቸው መሆኑን ያሳብቅበታል።

ብሎ ብሎ የሁሉም ሰው ሥጋት ኢህአዴግ ሕገ-መንግሥቱን እንዳይሸሸው ብቻ ነው። ሕገ-መንግሥቱን ያወጣውም ያጸደቀውም ያንቆለጳጳሰውም ራሱ ነው። አሁን ግን ተቃዋሚውም ዜጎችም ሕገ-መንግሥቱ የሰጠን መብት ተጣሰ እያሉት ነው። ሕገ-መንግሥቱን ትሸራርፋለህ ብለው እየወቀሱት ነው። ሕገ-መንግሥቱን ራስህ አውጥተህ ራስህ ነፍገሃል ብለው እያሙት ነው። ቢወቀስ ቢከሰስ ሁሌም በሕገ-መንግሥቱ አፈጻጸም ጉዳይ ላይ ሆኗልና ቃሉን የፈራው መስሏል። ቀስ በቀስ ሕገ-መንግሥት የሚለው ቃል በሚዲያ እንዳይነገር፣ በኢህአዴግ ስብሰባ እንዳይጠራ፣ ስሙ እንዳይነሳ ሊያደርግ ይችላል። ይህን ሁሉ ነገር ሸሽቶ አሁን በሕገ-መንግሥቱ ጉዳይ ላይ ሲመጡበት ምን እንደሚያደርግ አልለየለትም። ብቻ ሕገ-መንግሥቱንም እንዳይሸሸው ሰጋን።

እስቲ አንድ ሆነን እንነሳ ,አንድነት እኮ ሃይል ነው !!!


አገራችን ከ መችውም ጊዜ በላይ የእኛ እርዳታ ያስፈልጋታል.. እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልህ ስፍራ የለም:: አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ የሚኖረን በመሆኑ ሁላችንም በተገቢው መጠን በሃገራችን ፖለቲካ ላይ አውንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር የምንቸገር ሊሆን ይችላል ...  
ለጋሸ አገራት የሚያወጧቸው ሃሰተኛ ጸረ አፍሪካ ሪፖርቶች በተለይ የምስራቅ አፍሪካን ተገን አድርጎ የተመቻቸው የብሄራዊ ጥቅማቸው ፎርሙላ ስኬት የአምባገነኖችን እድሜ በማስረዘም ህዝብ እንዲጭበረበር የህዝብ ጥያቄዎች እንዲደናቀፉ ለገዢዎቻችን የልብ ልብ ሰቷቸዋል:: ለብሄራዊ ጥቅም አስጊ ይሆናሉ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን እስከማጨማደድ ከተቻለም አንዲጠፋ በማድረግ እና በእጅ አዙር ህዝባዊ ጥያቄዎች እንዲታፈኑ እየተደረገ አምባገነናዊ አገዛዝን አፍልተውብናል, ምን ይደረግ ተረጅ መሆን በራሱ የሚያመጣው ሳንካ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም:: 
እርስ በርሳቸው የሚላተሙ አንድ ኣቁዋም እና ኣንድ አላማ ይዘው የማይግባቡ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በላም አለኝ በሰማይ ተስፋ ህዝባችንን አረንቋ ውስጥ እየጨመሩት ነው: በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ መሆኑ ግልፅ ሆኖ, አንድ አላማ ይዘው የማይግባቡ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የህዝባችንን የመታገል ስሜት አሉታዊ በሆነ መልኩ ማዳከማቸው አሳዛኝ ነው ::

መሰረታዊ ፍላጎቶች እና የአገልግሎት ፍጆታችን በበቂ ሁኔታ ባልተሟላበት አገር መንግስት ፕሮጀክት ለመጨረስ የገንዘብ እጥረት ገጠመኝ በሚልበት አገር ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ የለኝም በሚልበት እና የመንግስት ካዝና ባዶ ሆኖ በዕቃ ግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ለቱጃሮች መንግስት ያለምንም ማስያዣ ገንዘብ በሚበደርባት አገር ጥቂት ፖለቲካው የወለዳቸው ሃብታሞች እና እጅግ ብዙ የኢኮኖሚ ድቀት ያፈራቸው ደሃዎች በፈሉበት አገር ምን አይነት የኢኮኖሚ እድገት እንደተመዘገበ እራሱ ወያኔ  ቢያብራራው የተሻለ ይሆናል ::ለጋሽ አገሮች ከእኛ የሚያገኙት ብሄራዊ ጥቅም ሞቅ ባለ ቁጥር ኢኮኖሚያችሁ በመቶ ይህን ያህል አድጓል ይሉናል::  በሃገሪቱ ውስጥ ያለው የሃብት ክፍፍል ጤናማ ያለመሆኑን ሁላችንም  የምንገነዘበው ግልፅ የሆነ የአደባባይ  ሚስጥር ነው .ለጋሽ አገሮች ከእኛ ስለሚያገኙት ብሄራዊ ጥቅም ኢኮኖሚያችሁ በመቶ እጥፍ ይህን ያህል አድጓል ቢሉ እንኩዋን ትውልዱ ያለውን እውነታ መጋፍጥ ይኖርበታል ኮ .... እስከመቼ የአምባገነኖችን ደጋፊዎች ዉሸት ተሸክመን እንዘልቃለን ? በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ ነው:: 
ወያኔም ማን እንደወከላት አይታወቅ ፖለቲካዊ ማጭበርበር እና ኢኮኖሚያዊ ደላልነትን አፋፍማዋለች ,ታዲያ እኛ ቢያንስ በዚ ጊዜ እንኩዋን ምናለበት  ቢያንስ  ያለንን ልዩነት አጥብበን  በአንድ ልብ በጋራ ጠላታችን ላይ መዝመት ብንችል ,ኣንድነት ሃይል ነው የተባለው እውነት ይመስለኛል . 

መታሰቢያ ታደሰ
እግዚአብሄር  ኢትዮጲያን ይባርክ 

በተፈጥሮ የታደልነውን ውሃ በፖለቲካ ሹማምንት ልፍስፍስነት ልንጠቀምበት አልቻልንም

የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መብራት ጠፍቶ ሲመጣ መብራት መጣ ብሎ መጮህ ነው ተብሎ በሰው ሃገር ጋዜጦች እስኪቀለድብን ድረስ ወያኔ በህዝብ ጭንቅላት ጢባጢቦ እየተጫወተች ነው::መብራት ውሃ ስልክ ሀገሪቷ ተሰርቶ እና ተበድራ ሳይሆን በተፈጥሮ የታደለችው ጸጋዋ እንደሆነም ያለን ሃብት ይመሰክራል ህዝቡ ያለውን ቴክኖሎጂ ከተፈጥሮ ሃብቱ ጋር አደባልቆ እንዳይጠቀም እኛ እናውቅላቹዋለን የሚሉ የወያኔ አውሬዎች ቀፍድደው ይዘውታል:: በቀላል ሊፈታ የሚችል ችግርን በፖለቲካዋ ሳንካ መተብተብ ምንም የሚጠቅም ስላልሆነ ህዝቡ አስፈላጊውን የአገልግሎቶች አቅርቦት እንዲያገኝ መደረግ አለበት ብለን ካሁን በፊት ብንጮህም ከቀድሞ በባሰ መልኩ ብሶበት ይገኛል::

በአለማችን በረሃ በተባሉት አገሮች የውሃ አቅርቦት በሰፊው ለህዝባቸው እየሰጡ ሲሆን የተጣሩ ውሃዎች ሳይቀር በርካሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው::በኢትዮጵያችን ግን በተፈጥሮ የታደልነውን ውሃ በፖለቲካ ሹማምንት ልፍስፍስነት ልንጠቀምበት አልቻልንም ትልልቅ እና ገባር እንዲሁም ትንንሽ ወንዞች እና የተፈጥሮ ውሃ ምንጮች በሞሉባት ሃገራችን ህዝብ ውሃ ተጠማሁ ሲል መመልከት አስደንጋጭ ነው::ሃገሪቱ በውሃ ችግር ተውጣልች::የውሃ እጥረት ኖሮን ሳይሆን በአግባቡ አለመጠቀም እና ችግሩን የመፍታት ባህል ስላሌለን ነው::ለጎረቤት አገሮች ውሃ እንሰጣለን እየተባለ ባለበት የፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ እኛ በጥማት ማለቃችን አሳፋሪ ነው::

ወድ መብራት ስንመጣ ደሞ መንግስት ያለ እንኳን ተደርጎ ማሰብ ይከብዳል:: የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መብራት ጠፍቶ ሲመጣ መብራት መጣ ብሎ መጮህ ነው ተብሎ በሰው ሃገር ጋዜጦች እስኪቀለድብን ድረስ ወያኔ በህዝብ ጭንቅላት ጢባጢቦ እየተጫወተች ነው::ይህ እንደገጠመኝ እና እድል የሚታየው የመብራት እቃቃ ጨዋታ በአግባቡ መፍታት እየተቻለ ችግሩንም ማድረቅ እየተቻለ ለምን መዘናጋት እንደሚፈጠር ማስረዳት የሚችል ባለስልጣን አልተገኘም::በኤሌክትሪክ መጥፋትና ሥርዓት አልበኝነት ምክንያት በርካታ ኢንዱስትሪዎች ሥራቸውን እያቆሙ ናቸው፡፡ በርካታ ማሽኖች ከጥቅም ውጭ እየሆኑ ናቸው፡፡ በመኖሪያ ቤቶች ቴሌቪዥኖች፣ ፍሪጆችና ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እየፈነዱና እየተቃጠሉ ነው፡፡ በመብራት መጥፋት ምክንያትም የየዕለቱ ኑሮ ይዘቱም ገጽታውም እየተበላሸ ነው፡፡ ከመኖሪያ ቤቶች አልፎ ካፌዎችም በመብራት መጥፋት ምክንያት ‹‹ተረኛ መድኃኒት ቤት›› እየመሰሉ ነው፡፡ ሻይ ታዞ ‹‹ይቅርታ መብራት የለም›› የሚል መልስ መስማት የተለመደ እየሆነ ነው፡፡ እውነት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ፣ ለኢንዱስትሪዎቿም ሆነ ለሁሉም ዓይነት እንቅስቃሴዎቿ የሚሆን በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል የላትም? አይኖራትም? አላትም ይኖራታልም፡፡ በቂ የውኃ ኃይል ማመንጫዎች የንፋስ የኃይል ማመንጫዎች የፀሐይ የኃይል ማመንጫ አቅም የጂኦ ተርማል የኃይል ማመንጫ አቅምም አለን እየተባለ ይደሰኮራል:: እንኳን ለራስዋ ለሌሎች አገሮችም የሚሆን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ዕምቅ ሀብት እንዳለን ይነገረናል:: ሆኖም ግን በአግባቡ የሚያዳርስ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተቷት ህዝቧ አስፈላጊውን የአገልግሎት መብቶች እና አቅርቦቶች ሊያገኝ አልቻለም::በሃይል ግንባታ ሰበብ በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ ነው::

ወደ ስልክ እና ኢንተርኔት ኔትወርክ ስንመጣ በጸሎች የሚገኝ ያውም ተለቅሶ መፍትሄም የጠፋለት ጉዳይ ከሆነ ቆይቷል:: በአለማችን በስፋት ይህን የኔትዎርክ ችግር ተቀርፎ ባለበት ሰአት የወያኔ ባለስልጣናት ግን በአደናባሪዎቻቸው በኩል በፋይበር ቅንጠሳ እና በህንጻ መብዛት ቢያሳስቡም ከነሱ ቀድሞ ንቃተ ህሊናው ያደገውን ህዝብ ግን ሊሸውዱት አልቻሉም:: ያው እንደለመዱት በጠበንጃ እና ሽብር በመንዛት ዝም አሰኝተውታል:: የወያኔ መንግስት የህዝብን የአገልግሎት አቅርቦት ጥያቄዎች መፍታት እየቻለ እንዳይፈቱ በማድረግ በሚፈጸም አሻጥር እራሱ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሊገነዘበው አልደፈረም:: የመልካም አስተዳደር ብልሃት የሞላበት አመራር ህግ አክባሪ እና አስከባሪ ባለስልጣንትን ለማግኘት ሁላችንም በትግሉ ላይ እንረባረብ ::

ኢትዮጵያ - የመብት ህጎች እና ድንጋጌዎች የተቆለሉባት ግን የቤት ስራዋ የደቆሳት ሃገር

#Ethiopia @hrw #EPRDF @amnesty #UDJ #EHRC #BlueParty 

ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::#MinilikSalsawi
ምንሊክ ሳልሳዊ :-ታዋቂነታችን በድርቅ በድህነት ብሎም በጭፍጨፋ ደሞ በሰብኣዊ መብት ጥሰት
የሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰባዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እና ድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌን ከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለም አቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋር እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የቀድሞ መንግስትን ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭራሽ ብሶበት ቁጭ አለ፡፡ የሕወሓት ወንበሩን መቆጣጠር ተንተርሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የወያኔን ጁንታ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች አቤቱታ ማሰማታቸውን አላቆሙም፡፡ ጋዜጠኞችን የሃሳብ ነጻነት ከሚገድብ ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ የመብት አስከባሪ ድርጅቶችም ወያኔ በሚፈጥረው ከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል::የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው ወያኔን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ይከሰዋል፡፡ ባሁን ወቅትየእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብቶች በመጣስና በማፈን ወደር የሌላት አገር እንደሆነች ዓለም እንዲረዳው እያደረጉ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅና ረሃብ ለመታወቅ እንደበቃችው ሁሉ ወያኔ የዜጎችን መብቶች በመጣስና በማፈን እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጽመው ወንጀል በዓለም ላይ ታዋቂነትን እያተረፈ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም;ወያኔ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን መብቶች ለመጣስ ስለሚጠቀምባቸው ዘደዎች የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና ማብራሪዎች እጅግ ዘግናኝ ናቸው፡፡የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ተቀናቃኖችን ለማዳከም ሲሉ ንፁኃንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ዘዴዎችን ሥራ ላይ እንደሚያውሉ በተለያዩ ይፋዊ ሪፖርቶች ላይ ሁሉ ከነማስረጃው እየተነገረ ይገኛል::

የህ የሰብኣዊ መብጥ ጥሰት እየተባባሰ የሚሄድበት ምክንያት ወይኔ በአብዛኛው ካድሬዎች ዘንድ በስፋት ሰርጾ እንዲገባ ያደረገው የተቃዋሚዎች ጥላቻ እና እንዲሁም የተቃዋሚው ቡድን የትግል አቅጣጫው በተመሳሳይ መልኩ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ነው::ተቃዋሚዎች የታጠቁ ሃይላት ባለመሆናቸው የመርሃቸው እንቅስቃሴ የተገደበ እና ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ፍጆታ የዋለ ተዳፍኖ የሚገኝ ሲሆን የወያኔው ግን በታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና በፖለቲካ ማጭበርበሮች ላይ ስለተመረኮዘ ካድሬዎቹ በተሰጣቸው የጥላቻ ተግዳሮት እና ወያኔያዊ ስልቶች የፈጠሩትን ጥቅማጥቅሞች ጠብቀው ለማቆየት ሲባል ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::

ይህ ፍርሃት እና ጥላቻ በወያኔ ከትልቅ እስከ ትንሽ ካድሬዎች አናት ውስጥ ስር ለስር በመስደድ የፈጠረው ነገር ቢኖር ማንኛውም ዜጋ ተቃውሞ ካሰማ በወንጀለኛነት በመፈረጅ በማሳደድ በማጥፋት እረፍት ለማግኘት እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲራወጡ የህዝብን የበላይነት አፈር ከተውታል::ማእከላዊ የወያኔ ጁንታ በዲሞክራሲ ባለመወቀጣቸው የህጎችን የበላይነት ማረጋገጥ ካለመቻሉም በተጨማሪ በህዝብ እና በዲሞክራሲ ላይ በደሎችን የሚያደርሱ ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሃገሪቱ የበላይ ህጎች ሳይሆን በወያኔያዊ የፓርቲ መመሪያዎች በመሆኑ በጥቅም መተሳሰር በፈጠርው ዝግ መንገድ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተብራከቱም ከመሆኑ አልፎ የእለት ተእለት ተግባራት አካል ሆነዋል:

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

mekabir 1


mekabir
ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸውን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እንዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡ በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች) በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡
በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል። በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት ሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህne ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል። በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው።
Ze-Habesha

Monday, December 30, 2013

ጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው *ኢቴቪና ፌዴራል ፖሊስም ይከሰሳሉ


በዘሪሁን ሙሉጌታ

በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ከተላለፈው ‘‘ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የወንጀልና የፍትሃብሔር ክስ ሊመሰረት ነው። ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሻገር በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) እና በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ ክስ ይመሰረትባቸዋል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናቱ እና የተጠቀሱት ተቋማት ላይ ክስ የሚመሰረተው ሰሞኑን ‘‘ጃሃዳዊ ሃራካት’’ በሚል በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ተጠርጣሪዎች መብት ሲጣስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀማቸው፣ በሕዝብ ሐብት ያለአግባብ በመገልገላቸው፣ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ባለመወጣታቸውና በሃይማኖት ጣልቃ በመግባታቸው የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ ይመሰረትባቸዋል። ክሱን የሚመሰርቱት በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ባሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቆች አማካኝነት ሲሆን ክሱም በሁለት ደረጃ ተከፍሎ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል።
ክሱን እያዘጋጁ ከሚገኙት ጠበቆች አንዱ የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ክሱን በማስመልከት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚመሰረተው ክስ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባል ብለዋል። በኢቲቪ ላይ የሚመሰረተው የፕሬስ ክስ ቀጥታ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን ክሱም ከሞራል ጉዳት ጋር እንደሚያያዝ ጠበቃው አስታውቀዋል።
‘‘መጀመሪያ ክርክራችን ዘጋቢ ፊልሙ እንዳይተላለፍ ነበር። ከተላለፈ በኋላ ግን ይግባኝ ማለት ሳይጠበቅብን ይሄንን ጉዳት ባደረሱ አካላት ማለትም ፊልሙን በሰሩት፣ ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች ጨማምረን ክሱ እንመሰርታለን’’ ያሉት ጠበቃ ተማም በፕሬስ ህጉ መሰረትም ዘጋቢ ፊልሙ በተላለፈ በሦስት ወራት ውስጥ ክስ መመስረት እንደሚያስችልም አያይዘው ገልፀዋል።
በኢቲቪ በተላለፈው ዘጋቢ ፊልም ላይ በሚመሰረተው ክስ እስከ 100ሺህ ብር የሞራል ካሳ እንደሚጠየቅ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ክስ ደግሞ በሌላ መዝገብ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሚመሰረተው ክስ ለደንበኞቻችን የሞራል ካሳ እንዲካሱ፣ ደንበኞቻችን ይቅርታ እንዲጠየቁ፣ በተመሳሳይ የአየር ጊዜ ተሰጥቷቸው ደንበኞቻችን የራሳቸውን ኀሳብ እንዲሰጡ፣ በሃይማኖት ውስጥ በተደረገ ጣልቃ ገብነት ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚያደርግ ክስ ነው ብለዋል።
‘‘ክሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማያካትትበት ምክንያት የለም። የሀገሪቱ መሪ እሳቸው ናቸው። ፖሊስም እያደረገ ላለው ነገር ለምሳሌ ተጠርጣሪዎችን ቶርች በማድረግ ጭምር እንከሳለን። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዘጋቢ ፊልሙ ያግዱ፣ አያግዱ የሚለውን አጣርተን የሚመለከታቸውን አካላት ለይተን ክሱን ለመመስረት ተዘጋጅተናል። ክሱን ለማዘጋጀት አስፈላጊ መረጃዎችን እየሰበሰብን ነው። በቅርቡም ክሱን እንመሰርታለን’’ ሲሉ ጠበቃ ተማም ጨምረው ገልፀዋል።
ደንበኞቻችን እራሳቸውን በማይከላከሉበት ሁኔታ ታስረው፣ መልስ እንዲሰጡ ባልተደረገበት ሁኔታ ስማቸው እንዲጠፋ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን የጠቀሱት ጠበቃው ዘጋቢ ፊልሙ የደንበኞቻችንን መልካም ባህሪ የገደለ (Character assination) ነው ብለዋል።
መንግስት በሽብርተኝነትና ከህገ-መንግስቱ በተቃራኒ ሃይማኖታዊ መንግስት ለማቋቋም ሲያሴሩ አግኝቻቸዋለሁ፤ በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰውና ከአለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን አልቃይዳ ጋር ከሚንቀሳቀሰው አል-ሻባብ ጋር ተመሳጥረው ሲሰሩ አግኝቻቸዋለሁ ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡ ይታወሳል።
ፊልሙ ከመተላለፉ በፊት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የእግድ ትእዛዝ ቢያስተላልፍም ፊልሙ ለሕዝብ አይታ መቅረቡ አይዘነጋም፤ ፊልሙ ለተመልካቾች ከቀረበ በኋላም አነጋጋሪ ሁኔታ መፈጠሩም ይታወቃል። ሠንደቅ ጋዜጣ

የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው!


December 30, 2013
የማለዳ ወግ
ነቢዩ ሲራክ
Ethiopians in Saudi Arabia suffering, December 2013ሰሞኑን ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ፣ ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ ፕሮፊሰር ይስሐቅ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በየአይነቱ ሰማን ። ይህ ሁሉ ታዲያ በፈረንጆች አመት በዋዜማው ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?
ባለሁበት የሳውዲ ምድር በአለም እንደ ጨው የተበተንን የዚያች ሃገር ዜጎችን ትኩረት ሳቢ ብቻም ሳይሆን አስጨናቂ ቀንን ተፋጦ ማወጫ ያጣ ወገን ጩኸት ደምቆ እንዳይሰማ የእኛ ነገር አልተመቸውም ! ሌላው ቀርቶ ጥቂት “ያገባናል” ያልን መረጃን በቀላሉ እየተለዋወጥን በምንገኝባቸው ማህበራዊ ገጾች ከአንድ የአለም ጫፍ ወደ ሌላው የአለም ጫፍ በብርሃን ፍጥነት የሚሰራጨው የጥላቻ ፖለቲካ የመረጃ ቅብብል መተንፈሻ ፣ ጉዳታችን ለአለም መንገሪያ ሜዳችን እንዳያጨልምብን ሰጋሁ ! ከሁሉም የሚያሳዝነው የምንወዳቸውና የምናከብራቸው የተማሩ የተመራመሩት ወገኖቻችን ሳይቀሩ በዝብሪቱ አዙሪት ተጠልፈው መግባታቸውን እየታዘብን ነው ። …አዋቂዎች እንዳላዋቂ በማህበራዊ ገጾች የተበተነውን የጥላቻ መረጃ ከስርጭቱ ባህር እየጨለፉ ይረጩት ፣ እየተቀባበሉ ያጎኑት ይዘዋል ። እንዲህ እየሆነ …አንዱ ያሰራጨውን እነርሱም ተቀባብለው የታላቅነታቸው መገለጫ የሆነች አስተያየታቸውን ሞነጫጭረው አሳለፈው ይለጥፉ የጥላቻውን መርዝ ይነሰንሱት ይዘዋል ! የማይጠቅም የማይበጀንን … አይ …የእኛ ነገር!
ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ያለው ወገናችን ወገናቸው ዛሬም አደጋ ላይ መሆኑን የረሱት ይመስላል ። በጅዳ የሽሜሲ መጠለያ ፣ በጅዳ አየር መንገድ ፣Ethiopians suffering in Saudi Arabia በጅዳ፣ በጀዛን እና በሪያድ እስር ቤቶች በወህኒው እንግልት ፣ በኮንትራት መጥተው በአረብ አሰሪዎቻቸው ገወፍ የሚፈጸምባቸው ፣ ወደ ሃገር እንዳይገቡም ሆነ የፈለጉትን እንዳያደርጉ እንደ ግዞት የተያዙ በርካታ የጨነቃቸው ወገኖች ፣ የአረብ ቤት አጽድተው ባጠራቀሟት ገንዘብ ወደ ሃገር የላኩት እቃ በአንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ካርጎ ለበርካታ ወራት ከሳውዲ ግልጋሎት መስጠት መቋረጥ የተበላሸባቸው ለኪሳራ የዳረጋቸው፣ ከአስርት አመታት በላይ በስደት ቆይተው ወደ ሃገር ሲገቡ የተገለገሉበትን እቃም ሆነ መደራጃ የምትሆን እቃ ይዘው ለመግባት የተቸገሩት እና በመሳሰሉት በድንገተኛ የስደት ኑሮ ውጣ ውረድ ድቀት ማዕበል የተመቱ ወገኖች ጩኸት እዚህም እዚያም ተበራክቷል … ! ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ከባቢ ያለን ወገኖች ከአፍንጫችን ስር ያሉትን ወገኖቻችን በሰላም ወደ ሃገር የሚገቡበትን መንገድ ከማፈላለግ ባለፈ አነሰም በዛ በዚህ ክፉ ቀን በወገን ድጋፍ የተሰማሩ ወገኖችን ስም እያነሳን ከመደቆስ ፣ የክፋት ፣ የጥላቻ መርዛችን በመርጨት ብቻ ሳይወሰን በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን ስራ ባላስፈታው የጥላቻ ፖለቲካ ተጠልፈናል ። የዝብሪቱን መረጃ እየተቀባበልን የመረጃ መቀበያ ማህበራዊ ገጻችን ማጉደፍ ይዘናል ! አይ ! የእኛ ነገር …
የእኛ ነገር እንዲህ ቢሆንም ፣ እንዲህ ሆኖ መቀጠል የለበትም ! ዛሬ ፋታ የማይሰጥ የወገን ጭንቀት ሊያስጨንቀን ፣ ህመሙ ሊያመን ፣ ቁስሉ ቁስላችን ፣ ሞቱ ሞታችን ሊሆን ይገባል ! ይህን ማድረግ ባይቻለንና በእውን ያሰብነው ተሳክቶ ፣ ግፉኡን ወገን ልንታደገው ባይቻለን ጩኸቱ እንዳይሰማ ግርዶሽ የሚሆነንን የጥላቻ ፖለቲካ አንከተል ! የክፊዎች ጭራ አንሁን ! እየተረጨ ያለውን ሰሞነኛ ዝብሪቱን እኛም ተቀብለን ትንታኔ ፣ ወግ እያሳመርን መርዙን መረጃ እያሽከረከርን የደማችን ከፋይ የወገናችን ጩኸቱን አናፍነው ! የወገናችን ጩኸቱን አንቀማው !
ሌላ ምን እላለሁ …
እስኪ እሱ ይታረቀን !

በተቀነባበረ የመብራት ሀይል ሙስና ኢትዮጵያ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ተደረገ


December 30/2013

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት ሃይል የቦርድ ሰብሰባ የሆኑት  ዶ/ር ደብረ ጸዮን ገብረሚካኤል ስለአቶ ደበበ ምህረት ከሃላፊነት መነሳት  ” እሱም የሚመሰገነውን ያክል ጉድለትም እንደነበረበት ይረዳል። ከሃላፊነቱ ሲነሳም አልደነገጠም።” በማለት መናገራቸው ይታወቃል።  ምንም እንኳ ዶ/ር ደብረጺዮን አቶ ደበበ በብቃት ችግር እንደተነሱ አድርገው ለመገናኛ ብዙሀን ቢገልጹም፣ አቶ ምህረት ደበበ ግን በህወሃት ባለስልጣናት ስውር እጅ ሲቀነባበር የነበረውንና ኢትዮጵያን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ያደረገውን ከፍተኛ ሙስና ሲቃወሙ እንደነበር ለጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበው እና ለኢሳት የደረሰው የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ያስረዳል።
በ1999 እና በ2000 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ የሚረዱ ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ካወጣቸው አለም አቀፍ ጨረታዎች ጋር ተያይዞ በጨረታዎቹ ሂደት ላይ ግልጽነትና ኃላፊነት የጎደለው አሰራር መከሰቱንና ይህም የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን  ምርመራ በማድረግ የምርመራ ውጤቱን በወቅቱ በስልጣን ላይ ለነበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትት መለስ ዜናዊ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን  አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፕሮግራምን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛሉ በማለት የሥርጭት (Distribution) ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ሁለት ዓለም አቀፍ ጨረታዎችን ለማውጣት ዝግጅት ጀመረ። ጨረታዎቹ በኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎችና በጨረታ ገምጋሚ የኮሚቴ አባላት ይሁንታ አግኝተው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በሁዋላ  የመጀመሪያው ጨረታ በ1999 ዓ.ም፣ ሁለተኛው ጨረታ ደግሞ በ2000 ዓ.ም እንዲወጡ ተደረገ፡፡የጨረታዎቹን መውጣት ተከትሎም መረጃው የደረሳቸው ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በጨረታው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡  በተለያየ ጊዜ ተደረጉትን ጨረታዎችም  “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ” የተሰኘ  የሕንድ ኩባንያ አሸናፊ መሆኑ በወቅቱ በይፋ ተነገረ።
ኩባንያው የጨረታው አሸናፊ ተብሎ ይለይ እንጅ ባቀረበው ሰነድ ላይ የገለጸው የትራንስፎርመር ዓይነት ኮርፖሬሽኑ በጨረታው ሰነድ ላይ ሊገዛው ካሰበው ዓይነት ጋር የሚመሳሰል ሆኖ ሳይገኝ ቀረ፡፡ ይህ አልተጠበቀ ክስተት ደግሞ በግዥ ሂደቱ ውስጥ ገና ከጅምሩ የሙስና ወንጀል ድርጊት የተጠነሰሰ መሆኑን አመላከተ፡፡ ኮርፖሬሽኑ  በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ያስቀመጠው የትራንስፎርመር ዓይነት “ሄርማቲካሊ ሲልድ” የሚል ሲሆን  የጨረታው አሸናፊ ኩባንያ  ባቀረበው የውል ማቅረብያ ሰነድ (ኦፈር) ላይ “ትራንስፎርመር ዊዝ ኮንሰርቫቶር ዩኒት” የተባለ ነው።
“ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ” ያቀረባቸው ሰነዶች ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ያወጣውን መስፈረት እንደማያሟሉ ሲታወቅ ፣ የነበረው የመፍትሄ አማራጭ ጨረታዎቹን አሸንፏል ተብሎ የተለየው ኩባንያ ያቀረበው ትራንስፎርመር በኮርፖሬሽኑ የጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠው መስፈርት (ሰፔስፊኬሽን) አያሟላም በሚል በአሰራሩ መሰረት በቴክኒክ ግምገማ ውድቅ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ላይ አቶ ምሀረት ደበበ ተቃውሞ ያሰማሉ፤ ይሁን እንጅ የኮሚቴ አባላቱ ተቃውሞውን ወደ ጎን በመተውና አዲስ ቃለ ጉበኤ በመያዝ ኩባንያው ትክክለኛ የትራንስፎርመ ዓይነት ይዘው ለውድድር ከቀረቡ ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር እንዲወዳደር በማድረግ በህገወጥ መንገድ ቀጣዩን የ ፋይናንስ ግምገማ ሥርዓት እንዲያልፍ አድረጉ፡፡ በዚህ አግባብ ኮርፖሬሽኑን ወክለው በጨረታው የተሳተፉ አካላትም ሆነ ጨረታውን አሸነፈ የተባለው ኩባንያ ባለቤት በኪራይ ሰብሳቢነት ስሌት ያልተገባ ጥቅም ለመቀራመት እየተንደረደሩ መሆኑን የሚያሳይ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበላቸው።
የጨረታው ሂደት ቀጥሎ ኮርፖሬሽኑ እና የጨረታው አሸናፊ ኩባንያ በሚቀርቡ የትራንስፎርመሮች መጠንና በገንዘብ ጉዳይ ላይ ውል የሚዋዋሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ።  ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ያወጣቸውን ሁለቱን ጨረታዎች የተመለከተ የውል ሰነድ ተዘጋጅቶም በሁለቱም ወገኖች ተፈረመ።  የጨረታዎቹ አሸናፊ ነው የተባለው “ጉድላክ
እስቲል ቲዩብስ ሊምትድ” ኩባንያም ትራንስፎርመሮቹን በሰፕላየርስ ክሬዲት (supplier credit) እንደሚያቀርብ ተስማማ፡፡ በውሉ መሰረት ኩባንያው በአንደኛው ጨረታ ብዛታቸው 1950 የሆኑ የስርጭት ትራንስፎርመሮችን ወለዱን ጨምሮ በ8 411,946 የአሜሪካ ዶላር፤ በሌላኛው ጨረታ ደግሞ ብዛታቸው 3520 የሆኑ ትራንሰስፎርመሮችን ከነወለዱ በ17,695,686 የአሜሪካ ዶላር፤ በድምሩ ብዛታቸው 5470 የሆኑ ትራንስፎርመሮችን ወለዱን ጨምሮ በ 26 107 632 የአሜርካ ዶላር ለማቅረብ ስምምነቱ ተፈረመ።፡
የሁለቱ ጨረታዎች የመጀመሪያ ውሎች በዚህ መልክ በኮርፖሬሽኑና በጨረታው አሸናፊ ኩባንያ መካከል ይፈረሙ እንጅ በኩባንያው በኩል ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው መዘግየት የሚጠበቁ ውጤቶች ሊታዩ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ኩባንያው ገንዘቡን በራሱ ማቅረብ እንዳማይችልም ግልጽ እየሆነ መጣ፡፡  ይህን የተረዱ የጨረታው ኮሚቴ አባላትና የኩባንያው ባለቤት መፍትሄ ይሆናል ብለው ያሰቡትን አማራጭ ማፈላለግ ጀመሩ፡፡ አውጥተው ካወረዱ በኋላም ሌላ አዲስ ውል ቢኖር የፋይናንስ ችግሩን ይቀርፋል በሚል ሀሳብ ተስማሙ፡፡  በአዲሱ ሀሳብ ላይ ተቃውሞአቸውን የገለጹት አቶ ምህረት ደበበ እራሳቸውን ለማግለል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቀጥታ በውሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በጠ/ሚሩ ጽ/ቤት በኩል ትዕዛዝ ደረሳቸው።  ኩባንያው መጀመሪያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈራረመው ውል በአዲሱ ውል እንዲተካም ተደረገ፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የተፈረመው የዚህ የአዲሱ ውል ዋና ፍሬ ሀሳብም የመጀመሪያው ውል ተቀይሮ ግዥውን ፋይናንስ የሚያደርግ ሌላ ሶስተኛ ወገን በውሉ ውስጥ እንዲገባ ማድረግ የሚል ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ቢዝነስ እንደሚሰራ የሚነገርለት “ኮብራ ኢንስታሌሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር”  ግዥውን በገንዘብ አቅርቦት የሚደግፍ ተባባሪ (ፋይናንሲንግ አሶሺዬት)፣ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የትራንስፎርመሮቹ አቅራቢ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ደግሞ የትራንስፎርመሮቹ ገዢ በመሆን የሶስትዮሽ ውል እንደገና እንዲፈረም ተደረገ፡፡
ይሁን እንጅ ሌላ አዲስ ውል በሕንድ ኩባንያዎች መካከል መፈረሙም ታወቀ፡፡ ዉሉ በ“ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ”፤በ“ኮብራ ኢንስታሌሽንስ” እና ሌላ በሕንድ አገር ከሚገኘ የትራንስፎርመር አምራች የሆነ “ናሽናል ኤሌክትሪክ ኢክዩፕመንት ኮርፖሬሽን” በተሰኘው ኩባንያ መካከል የተፈረመ የሦስትዮሽ ውል ነበር፡፡ ኩባንያዎቹ ይህን ውል ሲፈራረሙ በኮርፖሬሽኑ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም እና የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ሥ/አስፈፃሚዎች የነበሩ ግለሰቦች በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ቢሆንም ከኮርፖሬሽኑ እውቅና ውጭ መሆኑ ግን በምርመራው ተደርሶበታል፡፡ ከምርመራው ውጤት ለመረዳት እንደተቻለው ይህ ሁሉ አካሄድና ቀና ደፋ ደግሞ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የተባለውን ኩባንያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሦስትዮሽ ከተፈራረመው ውል ማውጣት ነውና ይህም ተሳካለቸው፡፡ ስለሆነም “ኮብራ ኢንስታሌሽንስ” የተባለው ኩባንያ ከፋይናንሲንግ አሶሺዬት ወደ አቅራቢነት የውል ተቀባይ ወገን ተቀየረ፡፡
የኮርፖሽኑ የቀድሞው የስራ ሃላፊ አቶ ምህረት ደበበ  ከኮርፖሬሸኑ እውቅና ውጭ የተደረገው ውል ያለአግባብ መሆኑን በመገንዘብ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የተባለ ኩባንያ ከውሉ መውጣት እንደማይገባውና ቀደም ሲል ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈረመው የሦስትዮሽ ውሉ ጽንቶ መቆየት አለበት በሚል ማሳሰቢያም ጭምር ለመስጠት ጥረት አድርጓል፡፡ ይሁን እንጅ በአቶ ምህረት ደበበ የተሰጠውን ማሳሰቢያ የሚሰማ ጆሮ አልተገኘም፡፡ ይልቁንም ምርመራው እንዳረጋገጠው
ተጠርጣሪ የኮርፖሬሽ የሥራ ኃላፊዎች “ኮብራ” የተሰኘው ኩባንያ ትራንስፎርመሮቹን የማቅረብ የሕግ መሰረትና አቅሙ ሳይገመገም እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ይሁንታ ሳያገኝ በሚያዚያ ወር ም ለ“ሪዘርቭ ባንክ ኦፍ ኢንዲያ” በጻፉት ደብዳቤ ኩባንያዎቹ ከኮርፖሬሽኑ እውቅና ውጭ ለተፈራረሙት ውል ማረጋገጫ በመስጠት ኩባንያው ሕግን ባልተከተለ መንገድ የትራንስፎርመሮቹ አቅራቢ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ትራንስፎርመሮቹን የሚያቀርብ ኩባንያ ለመለየት የተጀመረው ድራማ በዚህ መልኩ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ የሚሆነው ደግሞ የግዥ አፈጻጸም ተግባራትን ማከናወን ነው፡፡ በዚህ የግዥ አፈጻጸም ተግባር ውስጥ በኮርፖሬሽኑ የሲስተምና የደንበኞች አገልግሎት ድጋፍ ክፍል ኃላፊ እና የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ፕሮግራም ኢንጂነሪነግ ፕሮሰስ የስራ ሂደት ተወካይ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊ በዋናነት ተሳታፊዎች ናቸው።
በአሁኑ ወቅት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች የትራንስፎርመሮቹን ግዥ አፈጻጸም በተመለከተ “ኮብራ” የተሰኘው ኩባንያ ባለቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካኝነት ለኮርፖሬሽኑ ያቀረበውን የአፈፃፀም ዋስትና ተከትሎ ዋስትናው ውሉ በሚያዘው ፎርማት (ቅፅ) መሰረት ያልተዘጋጀ መሆኑን እያወቁ ሕጉ ከሚያዘው አሰራር ውጭ ኩባንያው እንዲያልፍ ረድተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሁለቱም ጨረታዎች በቀረቡ የአፈፃፀም ዋስትናዎች ላይ “… በግዥው አፈጻጸም ውስጥ የባንክ ዋስትና ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በዋስትና ሰጪው ባንክ የገንዘብ መጠየቂያ ደብዳቤ በሕንድ መንግስት ባንክ የሚሰጥ ሆኖ ፓሪስ በሚገኘው የናቲክሲስ የማድሪድ ቅርንጫፍ ባንክ ተቀባይነት ካገኘበት ቀን በኋላ ብቻ ነው” የሚል ይዘት ያለው ቅድመ ሁኔታ የሰፈረ መሆኑን እያወቁ እንዲሁም የኩባንያው ባለቤት ግዴታውን በውሉ መሰረት ሳይፈፅም ቢቀር ኮርፖሬሽኑ ወዲያውኑ የአፈፃፀም ዋስትናውን መውረስ የሚያስችለው መሆኑን እየተረዱ ይህን ሁኔታ ለሚመለከተው የኮርፖሬሽኑ አካል ሳያሳውቁ እንደ ዋዛ አልፈውታል፡፡
“ኮብራ” የተባለው ኩባንያ በበኩሉ ትራንስፎርመሮቹን ለማቅረብ “ጉድላክ” ከተባለው ኩባንያ ላይ የተረከበውን ኃላፊነት ሳይወጣ ጊዜ ነጎደ፡፡ ኮርፖሬሽኑም ትራንስፎርመሮቹ በወቅቱ መቅረብ እንዳልቻሉና ኩባንያው በውሉ መሰረት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንዳልሆነ መገንዘብ ችሏል፡፡ መገንዘብ ብቻም ሳይሆን ኩባንያው በዉሉ መሰረት ግዴታውን ሳይፈጽም ቢቀር የአፈፃፀም ዋስትናውን ለመውረስ የሚያስችለውን መብትም ለመጠቀም ሲባል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብዳቤ አቅርቧል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ያቀረበው የአፈፃፀም ዋስትና ውርስ ጥያቄ በባንኩ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፡፡ ለዚህ በዋና ምክንያትነት የሚጠቀሰው ደግሞ የአፈጻጸም ዋስትናው በቅድመ ሁኔታ የተገደበ መሆኑ ነው፡፡
በዚህ አግባብ ኮርፖሬሽኑ የግዥ አፈጻጸም ዋስትናውን መውረስ የማይችልበት ሁኔታ ስለተፈጠረ ለኪሳራ ከሚዳረግ ይልቅ የሚቀርብለትን የትራንስርፎርመር ዓይነት ለመቀበል አጣብቅኝ ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በእርግጥ ኮርፖሬሽኑ
ሊገዛ ያቀዳው የትራንስፎርመር ዓይነት ቀርቦለት፣ የአፈጻጸም ዋስትናውን መውረሱ ቀርቶ ትራንስፎርመሩን በተገኘ ጊዜ ለመቀበል ቢችል እንኳ ባልከፋ ነበር፡፡ አሁን ኮርፖሬሽኑ ከሁለት ያጣ እንደሚባለው ሆኗል፡፡ ወይ ገንዘቡን አሊያም በጨረታ ሰነዱ የገለጸውን የትራንስፎርመሮች ዓይነት ለማግኘት አልቻለም። የምርመራው ውጤት እንዳመለከተው በድርጊቱ ውስጥ ተሳታፊዎች የነበሩ በቁጥር ሰባት የሚደርሱ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የጨረታው ገምጋሚ ኮሚቴ አባልትን ጨምሮ የ“ጉድላክ” እና የ“ኮብራ” ኩባንያዎች ባለቤቶች በአንጻሩ የማይገባቸውን ጥቅም ለመቀራመት የወጠኑትን ውጥን ከዳር ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
እነዚህ በሁለቱም ጎራ በጨረታው ላይ የተካፈሉ አካላት የጨረታውን ሂደት ፍትሃዊነት በማሳጣትና ግባቸውን ያልተገባ ጥቅም መቀራመት አደርገው በመንቀሳቀስ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ውሎች ውስጥ ኮርፖሬሽኑ ሊገዛ ካሰባቸው የትራንስፎርመር ዓይነቶች ውጭ እንዲቀርብ ሁኔታዎችን የማድበስበስ ተግባራትን መፈፀም ቀጠሉ፤ ቀደም ሲል በሁለቱም የጨረታ ሰነዶች ላይ የሰፈረውና ኮርፖሬሽኑ ሊገዛ ያሰበው የትራንስፎርመሮች ዓይነት “ሄርማቲካሊ ሲልድ” የሚለው ሲሆን ከዚህ መስፈርት ውጭ ከአቅራቢዎች ጎራ ሌላ ዓይነት መስፈርት ከመቅረቡም በተጨማሪ ኮርፖሬሽኑ አዲስ፣ ያላገለገሉ እና የቅርብ ስሪት የሆኑ የትራንስፎርመሮች ዓይነት እንዲቀርብለት ያስቀመጠውን መስፈርት ወይም ስፔስፊኬሽን ኩባንያዎቹ ባቀረቡት ሰነድ ላይ ሳይካተት ታልፏል፡፡
እነዚህ ተግባራት ተደማምረው ሕገ-ወጥ የግዥ አሰራር የበላይነትን ይዞ የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የኩባንያዎቹ ባለቤቶች የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ማሳለጫ መንገድ እንደሆናቸው የምርመራው ውጤት ያስረዳል፡፡ የኩባንያዎቹ ባለቤቶችም ከጨረታው ገምጋሚ ኮሚቴ አባላትና በጨረታው ተሳታፊ ከነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ያመቻቹትን ይህን ሕገ-ወጥ አካሄድ በመጠቀም ኮርፖሬሽኑ የማይፈልጋቸው የትራንስፎርመሮች ዓይነት ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማደረጋቸውንም ምርመራው ያሳየናል፡፡
በጨረታው ተሳታፊ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከትራንስፎርመሮቹ ጥራት ጋር በተያያዘ ጎልተው የታዩ ችግሮችን ለመሸፋፈን የተለያዩ እርምጃዎች ወስደዋል፡፡ ከዚህ አኳያም ትራንስፎርመሮቹ በሙያተኞች እንዲፈተሽ አድርገዋል፡፡ በውጤቱም የዛጉና የዘይት መንጠባጠብ የሚታይባቸው፣ የሲሊካ ጄል እና ከፍተኛ የመብረቅ መከላከያ የሌላቸው፣ የታፕ ቼንጀር ማስሪያ ብሎኖች የሌሏቸውና የተሰበሩ ትራንስፎርመሮች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ትራንስፎርመሮቹ ኮርፖሬሽኑ ከሚፈልጋቸው ዓይነት ውጭ ከመሆናቸው በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው በተደረገው ምርመራ ግልጽ ሆኗል፡፡ ከዚህም በመነሳት በጨረታው ሂደት ውስጥ በዋናነት ተሳታፊ የነበሩ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ስራ አስፈፃሚ፣ የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ሥ/አስፈፃሚ እንዲሁም የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም የቴክኒክ ክፍል ቡድን መሪ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ለ“ጉድላክ” እና “ኮብራ” ኩባንያ ባለቤቶች ደብዳቤዎችን ፅፈው ነበር፡፡ ውስጥ ለኩባንያዎቹ የጻፉዋቸው ደብዳቤዎች ይዘት ትራንስፎርመሮቹ በውሉ መሰረት ያልቀረቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ሲሆን በነዚህ ደብዳቤዎች መሰረት የሥራ ኃላፊዎቹ ለኮርፖሬሽኑ ጥቅም ውግንና ያሳዩ ይመስላል፡፡
ይሁን እንጅ የምርመራ ውጤቱ እንደሚጠቁመው እነዚህ የሥራ ኃላፊዎች ለኮርፖሬሽኑ ያሳዩ የሚመስለው ውግንና ዘለቄታ አልነበረውም፡፡ ከ2001 ዓ.ም በኋላ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከኩባንያዎች ጋር በተጻጻፉት ደብዳቤዎች መሰረት ትራንስፎርመሮቹ እንዲቀየሩ ከማድረግ ይልቅ በኩባንያዎቹ የቀረበላቸውን የጥገና መርሃ ግብር ተቀብለውና አፅድቀውት በመላክ ትራንስፎርመሮቹ ያለአግባብ እንዲጠገኑ አድርገዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በኮርፖሬሽኑ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የኢንጂነሪንግ ክፍል እና የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የሳፕላይ ቼይን የሥራ ኃላፊዎች ትራንስፎርመሮቹ ብልሽት ያለባቸው ሆነው እያሉ ሙሉ በሙሉ እንደተጠገኑና ስራ ላይ እንደዋሉ በመግለፅ፣ አንድ ጊዜ እንዲጠገኑ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንዲተኩ በሚል ያለ በቂ ሙያዊ ፍተሻ ተገቢ ያልሆነ የውሳኔ ሃሳብ በመስጠትና የውስጥ ማስታወሻዎችን በመጻጻፍ ትራንስፎርመሮቹ በአዲስ እንዳይተኩ በማድረግ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በግዥው ሂደት ውስጥ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘትና ለኩባንያዎቹ ባለቤቶች ለማስገኘት በማሰብ በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ተካፋይነት በሚፈፀም ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በድርጊቱ ውስጥም በስልጣን ያለአግባብ መገልገል፣ የመንግስት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት እና ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ድርጊቶች የተፈጸሙ መሆናቸው ታይቷል፡፡ በዚህ አግባብ በተፈጸሙ ብልሹ አሰራሮች ሳቢያ በአገር ጥቅም ላይ ከ26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱም ተጠቅሷል፡፡  ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሰባት የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ በአራት የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የ“ጉድላክ” እና የ“ኮብራ” ኩባንያ ባለቤቶች ላይ ተገቢውን ማስረጃዎች አሰባስቦ በሁለት የክስ መዝገቦችና በስድስት ክሶች በማጠናቀር ጉዳዩን ለመጀመሪያ ጊዜ ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቀርቧል፡፡ የአቶ ምህረት ደበበ የስልጣን ዝውውር የጀርባ ፍጥጫ ሌላው የግምገማ ታሪክ ይህን ሲመስል፣ በተፈጠረው አለመግባባት ስራውን በአግባቡ እንድመራው በወጣው ህግ እና ደንብ መመራት አልቻልኩም ሲሉ ያቀረቡት መልቀቂያ ጥያቄ በዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ተቀባይነት አግኝቶ ምንም በቂ ሃላፊነት ወደ ሌላው የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል።
አቶ ምህረት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ እና የሙስናውን ድራማ ከጀርባ ሆነው ሲመሩት የነበሩት ከፍተኛ ተጠቃሚ የሆኑት የህወሀት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ሳይውሉ፣ በመካከለና የአመራር ቦታ ላይ ያሉ የተወሰኑ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። በቅርቡ  አንድ የህንድ ኩባንያ የኤልክትሪክ ኮርፖሬሽንን ማኔጅመንት ለመምራት ውል መዋዋሉ ይታወቃል።

ሳይቃጠል … በቅጠል (ሙሉጌታ አሻግሬ)


ሙሉጌታ አሻግሬ
mulugetaashagre@yahoo.com
‘ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ’  ነበር ነገሩ። ዓመቱ የሆነ አግራሞት ሳይፈጥር አያልፍም ለማለት የተባለ ነው። የፈረንጆቹ 2013 ዓመት ከመገባደዱ በፊት በኢትዮጵያ ህልውና ላይ ጉድ እየሰማን ነው።
አጤ ምኒሊክ በነገሱበት ዘመን ኢትዮጵያን ለማነፅና ህልውናዋን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመጣል ዘመኑ በፈቀደላቸው የእውቀት ደረጃ የበኩላቸውን ሰርተዋል። በዚህ ኢትዮጵያን የማነፅ ሂደት ውስጥ ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ነበር ብሎ የሚደመድም ጤናማ ግለሰብ አይኖርም።  ግዜውና ስርዓቱ የአፄ ከመሆኑም አንፃር ‘የአገር ማቅናት’  ሂደቱ በጠረጴዛ ዙሪያ፣ በድምፅ ብልጫ፣ በውይይት ነበር ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቆም የነበረው ሂደት አብዛኛው የዓለም አገር በተመሰረተበት መንገድ የኃይል አጠቃቀም እንደነበረበት  ግልፅ ነው።
ለዘመናት በዓለማችን በርካታ ጦርነቶች ተደርገዋል። ከጦርነት መለስም በህዝቦች መካከል የተለያዩ አንባጓሮዎች በየአካባቢው ይከሰቱ ነበር። ከዚህም ሌላ ከባህልና እምነት ጋር ተያይዞ በግለሰቦች መካከል በደል ይደርሳል። በእነዚህ ሽኩቻዎች ውስጥ በየትኛውም ደረጃ የተለያዩ ግፍ እና እጅግ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈፀማሉ። ይህን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦችም ሆኑ ህዝቦች ሰለባ ሆነዋል።
ስለዚህም በአጤው የጦር እንስቃሴ ውስጥ ችግር እንደነበር እሙን ነው። ምን ያህል ጦር ዘመተ? ፤ የደረሰው ጥፋት ምን ይመስላል? መቼ እና እንዴት ተከናወነ? የሚሉትን መረጃዎች ከታሪክ ድርሳናት ለማጣቀስ የሚቻልበት መንገድ አለ። ነገር ግን ከሳሽ ወገኖች ደርሶብናል (አፄ ምኒሊክ አድርሰውብናል) ብለው ያቀረቡትን ድርጊት በሙሉ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ተመዝግቦ ለማግኘት ያለመቻሉ ምስጢር ሁኔታውን አጠራጣሪ ያደርገዋል።  በርካታ ወገኖች የሚከራከሩበት ነጥብ በደሉ አልደረሰም ሳይሆን፤ ችግሩን የተወሰኑ ቡድኖች ለራሳቸው ፍላጎት ለመጠቀም በመፈለግ አጋነውና ጠምዝዘው ያቀርቡታል የሚል ነው። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ያገባኛል ያለው ዲያስፖራ እሰጥ እገባ ውስጥ ይገኛል። የችግሩ መነሻም ተበዳይ ነኝ ባዮቹ ‘ እኛ የምንናገረውን አፈታሪክ እውነት ነው በሎ ያልተቀበለ የድርጊቱ ፈፃሚ ተከታይ ነው ’የሚል ፍፁም ኢዲሞክራሲያዊ አቋም ነው።
ይህ ማለት ግን ሁሉንም በኢትዮጵያ ዙሪያ የተፃፉ መረጃዎችና ታሪኮች በጠቅላላ ጠንቅቄ አንብቢያለሁ የሚል ድምዳሜ ለመውሰድ አይደለም። ስለዚህ የዚህ ፅሑፍ ዓላማ ትክክለኛው መረጃ እና ማስረጃ አለኝ የሚል ማንኛውም ሃላፊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ መረጃውን ለሌሎች በማካፈል ሁኔታውን በሚዛናዊነት መርምሮ በመረዳት የጠራ አቋም ለመያዝ እንዲቻል የመነሻ ፅሁፍ ማቅረብ ነው።
 (በዚህ ፅሁፍ ተፈፅሟል የተባለውን ድርጊት መጥቀሱ ባልተረጋገጠ ጉዳይ ላይ እውቅና መስጠት ስለሆነ ቃላቱን መግለፅ አስፈላጊ አይደለም። ይህን አቋም መውሰድ ያስፈለገበት ምክንያት የዚህ አስተያየት ፀሃፊ ይህን ሁኔታ በተመለከተ የተፃፈ መረጃ ለማግኘት ባለመቻሉ ነው።)
በተቃራኒ የቆመው ኃይል ደግሞ ይህ አካሄድ ማስረጃ ያለቀረበበት ከመሆኑም አንጻር ጥያቄውን የሚያራግቡት ግለሰቦች በፖለቲካ  መድረክ ላይ ሪከርድ ያላቸው ስለሆነ ጥያቄውን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ነው  የሚል ውዝግብ ነው።
የሚቀርበውን በደል የጥፋት ልክ በሚዛናዊነትና ያለወገንተኝነት ለመመርመር እንዲቻል የተወሰኑ ተበድለናል ባይ ግለሰቦችን በግል ለማግባባት ተሞክሯል።  ነገር ግን እነዚህ ከሳሾች ችግሩን ለመተንተን የሚያስችል ማስረጃ አያቀርቡም። እንደምክንያት ከሚያቀርቧቸው ምክንያቶች መካከል ፣
  1. ይህን ጥፋት ለመመዝገብ ግዜው አይፈቅድም የሚል ‘ የሞኝ ብልጠት ’  ነው።  ከዚህም ባለፈ ድርጊቱ በአፈ ታሪክ የተነገረን ነው በማለት መረጃውን የማይዳሰስና የማይጨበጥ አፈተረት ያደርጉታል። ነገር ግን የኢትዮጵያን ታሪክ ፅፈዋል የተባሉ አውሮፓውያንና ኢትዮጵያውያን ከአፄ ምኒሊክ ዘመን በፊት የነበረውን የአገሪቱ ታሪክ በስፋት ጽፈውታል። ምንም እንኳን እነዚህ ወገኖች የአገራችንን ታሪክ ፀሃፍያን ‘ደብተሮች ’ ብለው የተለየ ትርጉም ለመስጠት በመሞከር ታሪካችንን ቢያጣጥሉትም፤ እነርሱ የሚቀበሏቸው አውሮፓውያንም ቢሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የጠቀሱት ነገር አለመኖሩ ድርጊቱን ኢተዓማኒ ያደርገዋል።

  1. ከአፄ ምኒሊክ ዘመነመንግስት ሦስት ክፍለ ዘመን (ሦስት መቶ ዓመታት) በፊት ተነስቶ ስለነበረው በተለምዶ አጠራር ግራኝ አህመድ በመባል የሚታወቀውን የኣዳሉን አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ታሪክ በማመላከት የቆዩ የህዝቦች መካከል የተፈጠረ ችግር በታሪክ ተቀምጧል ለሚለውም የመከራከርያ ነጥብ፤  ሁኔታውን ከሃይማኖት ጋር በማጋጨት ወደማይፈለግ መንገድ ይከቱታል። ስለዚህ በዚያ በኩል የሚደረገው አካሄድ ሁኔታው የሃይማኖት ቅርፅ እንዲይዝ ስለሚያደርጉት በፖለቲካ መስመር አሊያም ከሃይማኖት በራቀ መልኩ ለመነጋገር አዳጋች ይሆናል።
  2. ግለሰቦቹ ተፈፅሟል የተባለው ክፉ ተግባር ላይ መረጃ ያለመገኘቱን ምስጢር ለማስረዳት የሚሞክሩበት መንገድ የተለየ ነው። እነርሱ እንደሚሉት በምኒሊክ ዙሪያ የተፃፉት ታሪኮች በሙሉ ቅዱስ የሆኑት የአፄው ተግባራት ብቻ ናቸው፤ የአፄዎች ክፉ ድርጊት አይፃፍም የሚል ነው። ነገር ግን ታሪክ እንደሚነግረን ከምኒሊክ በፊት የነበሩት የአፄ ቴዎድሮስ ከልጅነት እስከ እውቀት ብሎም ሞት ድረስ ያለው የሽፍትነት፣ የጦርነት፣ የወረራ ፣ ብሎም በንግስና ዘመን አገርን ለመከላከል ከእንግሊዞች ጋር የተደረገው ጦርነት በግልፅ ተፅፏል።  በተረጋጋ መንፈስ የአፄ ቴዎድሮስን ታሪክ ስንመለከት አሉታዊ ጎኑ የሚያመዝን ሆኖ እናገኘዋለን። ከመሳፍንት አና የሃይማኖት አባቶች ጭምር የነበረው ውዝግብ በግልፅ ተቀምጧል።  ስለዚሀ ‘ የአፄዎች ክፉ ነገር አይፃፍም ‘ የሚለውን ነጥብ ውድቅ ስለሚያደርገው እንደምክንያት ለመቀበል አስቸጋሪ ነው።
ከእነዚህ ወገኖች ጋር የተደረገው ውይይት መቋጫ በሁለት አማራጥ የታጠረ ነው። አንድ ድርጊቱን በእርስዎ መጀን ስልት በድፍኑ መቀበል ካልሆነ ደግሞ የአጤ ምኒሊክ ባለሟል ተደርጎ መቆጠር ነው።
ሁኔታው እንዲህ ከሆነ ባልተረጋገጠ ነገር ላይ ያለማስረጃ መነጋገር ምን ይጠቅማል?
ግለሰቦቹ እንደሚሉት የአፄ ምኒሊክን ጥፋት ለማስታወስ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አንድ ሙዚየም እየተሰራ ይገኛል። በጦርነት ለሚደርሱ ጉዳቶች በርካታ ሙዚየሞች በዓለማችን ቆመዋል። የእነዚህ ሙዚየሞች ተቀዳሚ ዓላማ ያለፈውን የጥፋት ድርጊት በመረጃ ለመጪው ትውልድ በማሳየት ችግሩ እንዳይደገም ማስተማር ነው። ወደ እኛው ሁኔታ ስንመጣ በሙዚየሙ አቅራቢያ እንዲቆም ያደረጉት ሃውልት አለ። የሃውልቱ ይዘት የሚያሳየው ግለሰቦቹ ደረሰብን የሚሉትን በደል ነው፤ …እንደእነርሱ አባባል። ነገር ግን ሁኔታው በዝርዝር ሳይነገረው ሃውልቱን የማየት አጋጣሚ ያገኘ ማንኛውም ሰው በራሱ አእምሮ የሚሰጠው ትርጓሜ ይኖረዋል እንጂ እነሱ እንዳሰቡትና እንደሚዘረዝሩት ተፈፅሞብናል የሚሉትን መልዕክት ሃውልቱ በራሱ አያስተላልፍም።
ቁምነገሩ ግን የሃውልት መቆምና አለመቆም፣ ቅርጽና ውበት አይደለም። ችግሩ የሚመጣው እነዚህ ወገኖች በደሉን ለሶሰተኛ ወገን የሚገልፁበት መንገድ ነው። ሃውልት የቆመለትና ተፈፀመ የሚሉት በደል ፖለቲካቸውን ለማጦዝና ለማስፈፀሚያነት በእነዚህ ግለሰቦች ጭንቅላት ውስጥ አስርተ ዓመታትን አስቆጥሯል። የሃውልቱ አጠያያቂነት የሚጀምረው እነዚህ ግለሰቦች በደሉ የተፈፀመው (የተፈፀመ  እንኳን ቢሆን) በምኒሊክ እና በአማራው ነው የሚል ሃላፊነት የጎደለው ጭፍን ፍረጃ መሆኑ ነው። ስለዚህ አጤ ምኒሊክ በሌሉበት ዘመን ሁሉ አማራው በጉዳዩ ተጠያቂ እንደሆነ ይቀጥላል ማለት ነው። በመሆኑም ይህን ቂም በመያዝ በ1980ዎቹ በበደኖ ፣ አርባ ጉጉ ፣ አሶሳ እና ሌሎችም አካባቢዎች ዘግናኝ ጥፋት አድርሰዋል።  ይህ የሆነው እነርሱ በደለኛ ብለው በመደቡት አንድ ህዝብ ላይ ነው። ይህ የአማራው ህዝብ ነው። እነዚህ ሰዎች የአጤ ምኒሊክን ጥፋት መካስ ያለበት አማራው ነው ብለው የጨለማ ጉዞ ከተያያዙ በርካታ ዓመታት አስቆጥረዋል።  ስለዚህ አጤ ምኒሊክ ሰው ይሁን መልአክ፤ አለቃ ይሁን ምንዝር ፤ ነጭ ይሁን ጥቁር ለይተው የማያውቁ እድሜያቸው አስር እንኳን የማይደርስ ህፃናት የአጤው በደል ብድር ከፋይ ተደርገው በመቆጠር በህይወታቸው እንዳሉ ወደገደል እንዲወረወሩ ፤ በርካቶች ደግሞ ቤት ተቆልፎባቸው በእሳት እንዲቃጠሉ ተደርጓል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ መንግስት ተብዬው አካል የሃውልቱን ስራና ተያያዥ ጉዳዮች ችላ በማለት ህዝቦች እርስ በእርስ በዘላቂነት እንዲቃቃሩና ለመጠፋፋት የሚያስችል የመጨካከን ደረጃ ላይ እንዲደርሱ በግዴለሽነት በመመልከት ምን ያህል ሃላፊነት የጎደለው ተቋም እየሆነ እንደመጣ እያሳየን ነው።
ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሳይበር ንትርክ እንዲጀመር የመንግስት እጅ ከጀርባ እንዳለበት ነው። አንደኛው ምክንያት የሃውልቱ መሰራት በህዝቦች መካከል ሊያስከትል የሚችለውን ችግር የተረዱ ‘ቅን’ የስርዓቱ ግለሰቦች ያነሱትን ጥያቄ ወደ ዲያስፖራው በመወርወር፤ በዲያስፖራው መካከል በሚደረገው ንትርክ የማሳመን ስራ ለመስራትና በውስጥም በውጭም የሃውልቱን አስፈላጊነት ማሳየት ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ኢትዮጵያውያን በአረቡ ዓለም በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ዲያስፖራው ባልተጠበቀ ሁኔታና ሌሎች ህዝቦች ባልፈፀሙት መንገድ በመላው ዓለም አንድ ሆኖ መውጣቱ ነው። በዚህ የኢትዮጵያውያኖች ሞገድ ገዥው ወያኔ ለአርባ ዓመታት የሰራው የመከፋፈል ስራ መፈረካከሱና ለስርዓቱም አደጋ መሆኑ ነው። ይህን ኃይል ወደ ነበረበት የእርስ በእርስ መጠራጠር ደረጃ መመለስና ልዩነቱን የማስፋት ስራ መሰራት ነበረበት። ስለዚህ ከአጤ ምኒሊክ ጋር ተያይዞ የመጣውን አጋጣሚ ወያኔ በሰፊው ተጠቀመበት።
ዋናው ቁም ነገር ግን በሁለቱም ምክንያቶች ውስጥ በምዕራቡ አገራት የሚኖሩ የወያኔ አጫፋሪዎች ተበድለናል ባዮቹን ሲካድሙና እሳቱ እንዲፋፋም ሲያራግቡ የመገኘታቸው ምስጢር ነው። ስለዚህ ወያኔ ከችግሩ ጀርባ አርጩሜውን ይዞ እነዚህን ጥቂት ግለሰቦች ወደፈለገው አቅጠጫ እየጋለባቸው ይገኛል።
ከላይ ከተቀመጠው ሁለተኛ ምክንያት ጋር ተያይዞ በቋንቋ የተደራጁ ግለሰቦች ህልውናም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። በቋንቋ የተደራጁት ቡድኖች ወደአንድነት የመጣውን ኢትዮጵያዊ በመበታተን በሚፈልጉት መልኩ ወደ ጉያቸው በመሰብሰብ ወደተለመደው ጎሬ መጥበብ ነበረባቸው። በመሆኑም አንድ ሃይማኖት አንድ ህዝብ ልትሆን ነው፤ የቀደመው በደል ሊደርስብህ ነው፤ ይህን መንገድ ካልተከተልክ ይህን ትሆናለህ፣ ያኛው ይወሰድብሃል፣ ይህ ስም ይሰጥሃል፣ እንዲህ ተደርገህ ነበር የሚለውን የጎጥ መርዝ በመርጨት የሚፈልጉትን አባል መልሶ በማሰባሰብ መጠናከርና ህልውናቸውን ማረጋገጥ ነው።
ማጠቃለያ
በዲያስፖራው የተነሳውን እንኪያ ሰላንቲያ ከተለመደው እኔ እሻል ፖለቲካ በዘለለ፤ እንመራዋለን የሚሉት ድርጅት ግብዓተ መሬቱ ያስፈራቸው ተስፋ የቆረጡ ግለሰቦች ፤ በአልሞት ባይ ተጋዳይ መንፈስ ለጥፋት በሰፊው እየሰሩበት ነው። በህዝቦችና በሃይማኖት ላይ እየሰነዘሩት ያለው የጥፋት አማራጮች እውነትም እነዚህ ግለሰቦች የተሳፈሩበት ባቡር ሃዲዱን እንደሳተ ያሳየናል። በዚህ ፅሁፍ ዘርዝሮ ማቅረብ ባይገባም ከተቀረፁ የድምፅ ክምችቶች ለመረዳት እንደተቻለው አገሪቱ ዳግመኛ አገር ሆና እንዳትቆም ለማድረግ አእምሯቸው የፈቀደውን ጥፋት ሁሉ እንደአማራጭ ይደረድራሉ።
ስለዚህ በፖለቲካው መስመር ይህን አካሄድ ስንቃኘው ማንኛውንም ምክንያት ተደግፎ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚደረግ ጥረት እንዳለ ያሳያል። ስለዚህ ይህች ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ሆና እንድትቆም መሰረት የሆነውን ምኒሊክ ማንነት በማፍረስ አገሪቱን በመበታተን ስራ የተጠመዱ ግለሰቦች ማስቆም ተገቢ ይሆናል።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዚህን ጥያቄ መንስኤ በሰከነ አእምሮ ለመረዳት በመሞከር ተበድለናል የሚሉትን ወገኖች ለማዳመጥ ፍቃደኛ መሆን ያስፈልጋል።  የተባለውንም ችግር በመረጃ አስደግፎ በማጤን የችግሩን ስሜት መጋራት የሚያስፈልግ ነው። ይህም በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመገንባት የምንመኛትን ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ የመቻቻልን ፖለቲካ የምንለማመድበት አንዱ መንገድ ነው። ከዚህ በተለየ የሚቀርበው በግርድፉ ‘አይንህን አውጥተህ ጣል እኔ አይልሃለው’ የሚል እኔ ያልኩህን ብቻ ተቀበል ኋላቀር አካሄድ ተቀባይነት የሚያገኝ አይሆንም። ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ለማሳመን የሚደረገውን ጥረት ድብቅ ዓላማ በመረዳት ሊከተል የሚችለውን ጥፋት መከላከል ያስፈልገናል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመላው ዓለም የተስገመገመው ኢትዮጵያዊነት ወዳጅን በግርምት እጁን በአፉ እንዲጭን፤ ጠላትም ኢትዮጵያ ለካንስ አሁንም አለች ብሎ በፍርሃት እንዲጠነቀቅ አድርጎታል። ይህን ኢትዮያዊነት የሚሸረሽር ማንኛውንም እንቅስቃሴ በእንጭጩ እንከላከል።  አዎ ሳይቃጠል … በቅጠል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Ethiopian journalist sentenced for more than two years in jail


Nairobi, December 30, 2013–An Ethiopian court convicted a journalist on December 25 on the charge of spreading false rumors and sentenced him to two years and nine months in prison, according to local journalists.
The First Instance Court in Hawassa, capital of the state of Southern Nations, Nationalities and Peoples’ Regions, convicted Asfaw Berhanu, former contributor to the private bilingual paper The Reporter, in connection with a September 4 article he wrote for the publication that claimed three state government officials had been removed from their posts, local journalists said.
The officials had not actually been dismissed from their posts, the sources said. The Reporter issued a front-page retraction in its next edition and dismissed Asfaw, Reporter Managing Director Kaleyesus Berkeley said.
Asfaw is being held in Hawassa Prison, local journalists said. He plans to appeal the sentence, the same sources said.
“Asfaw Berhanu should not be jailed for making a mistake, especially after the Reporter apologized and issued a retraction,” said CPJ East Africa Representative Tom Rhodes. “Authorities should release Asfaw from prison immediately.”
On October 10, three policemen visited The Reporter office in Addis Ababa and arrested Managing Editor Melaku Demissie, taking him for questioning in connection with the September 4 news report, according local journalists and news reports. The police commissioner ordered his release the same day, Melaku told CPJ.

ጉድ በል ኦርቶዶክስ ….በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ አምጸዋል!!!


vv
ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::
2013-12-29_015319“ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም::” ብጹእ አቡነ ማትያስ
“ከኦሮሞ እና አማራ ጳጳሳት ጋር ትፈተፍታላችሁ::” አቶ ጸጋዬ በርሄ ..የአፋኝ ደህንነቶች ሹም
በጳጳሳቶች እና በፌዴራሉ ሚኒስትሮች መካከል በስብሰባ ላይ በተነሳው አለመግባባት እና የጳጳሶቹ ድምጽ በደል እና ግፍን በማስተጋባቱ እንዲሁም ለመጣው ችግር ሁሉ ተጠያቂው የኢሕኣዴግ መንግስት ነው:ማለታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ጳጳሱ አሜሪካን ተጉዘው ከመጡ በኋላ የሚያሳዩትን የቁጥብነት ባሕሪ ተከትሎ እንዲሁም በቤተክህነት ውስጥ የሚወስዱትን አስተዳደራዊ እርምጃ ያልጣመው ኢሕኣዴግ በአቶ ጸጋዬ በርሄ የሚመራው የአፈና እና የቶርች ቡድን ብጹእ አቡነ ማትያስን ለ72 ሰአታት በደህንነት ቢሮ በቁጣ እና በስድብ በማስጠንቀቂያ አሰቃይተው እና አንገላተው ወደ መኖሪያቸው እንደመለሱዋቸው ከደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን ገልጸዋል::ጻጻሱ ለ72 ሰአታት ከመኖሪያቸው ሲታጡ በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካድሬ ቄሶች አቡኑ ለህክምና ውጪ አገር ሂደዋል የሚል ወሬ ሲያስወሩ ነበር::
ብጹ አቡነ ማትያስ በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት ከአገሪቱ የመንግስት አካልት ጋር እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የተነገራቸው ሲሆን በዙሪያቸው ያሉ የሲኖዶስ አባላትን ፊት እንዳይሰቷቸው እና አማራ እና ኦሮሞ ጳጳሳቶች እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ከአቡነ መልከጻዲቅ እና ከተቃዋሚ ሃይላት መሆኑ አውቀው ጥንቃቄ እንዲወስዱ እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎችን ለንብረዑድ ኤልያስ አብርሃ እንዲያስረክቡ ተነግሯቸዋል:: ከሳቸው ጋር በረዳትነት አቡነ ሳሙኤል እንዲሰሩ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል::
ብጹእ አቡነ ማቲያስ በደህንነት ቢሮ የአቶ ጸጋዬ በርሄ ቡድን ማስፈራሪያ ሲሰጣቸው ፊታቸውን ቅጭም አድርገው በሃዘን እና በቁጭት ስሜት ያዳምጡ እንደነበር ታይተዋል:: መልስ ሲሰጡ የነበሩት እጅግ ዘግይተው በትካዜ እንደነበር ታውቋል::አሸባሪዎችን መዋጋት አለብዎ ሲባሉ በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም ብለው የመለሱት አቡኑ አብዛኛው መልሶቻቸው “…እስኪ ካላችሁ ይሁን እግዛብሄር እንደፈቀደው…’ የሚል እንደነበር የደህንነት ቢሮ ምንጮች ጠቁመውናል::
በዚህም መሰረት አቡነ ማትያስ የፖለቲካ ፍጆታ በሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ስብሰባ ላይ አይገኙም:: በተገኙበትም ቦታ ደሞ ስለ ልማት ካልሆነ በቀር ስለ አስተዳደራዊ ጉዳይ እና ስለ ብሶት ቀስቃሽ ንግግር እንዳያደርጉ ተነግሯቸዋል:: በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የአገር ውስጥ እንቅስቃሴያቸው በደህንነት አይን ስር ያለ ሲሆን የቁም እስር ላይ ናቸው::
እግዛብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃት

የሚያሣዝነው በዚህ በጐሣ በተከፋፈለ ከለላና አስተዳደር ምክንያት የተፈጠሩት ጥላቻዎች ማርከሻ መድሃኒት ማጣታቸው ነው፡፡


“የራበው ሥራ ፈልጐ ማግኘት የማይችልና ልጆቹን ለማስተማር አቅም ያጣ ሰው ከባርነት ነፃ ነው ማለት አይቻልም፡፡” የሚለው የአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ. ጆንሰን ንግግር እውነትነት አሁን አሁን በጆሮዬ መደወሉ ራሴን እያስገረመኝ መጥቷል፡፡ የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገደማ ደራሲና ጋዜጠኛ አለማየሁ ገላጋይ፤ ስለኑሮ ውድነት ሲጽፍ ብዙዎቻችን እያነበብን ፈገግ ከማለት በቀር ብዙ ልባችን አልተነካም ነበር፡፡ ምናልባትም በጣም አልፎ አልፎ ከምናነባቸው መጣጥፎች ይልቅ መንግስት ስለ ልማት የሚነፋው ጥሩንባ አደናቁሮን ይሆናል፡፡ አሁን አሁን የመንግሥት መዝገበ ቃላት “ልማት” የሚለው ትርጓሜ ግራ እያጋባን መጥቶ ጭራሽ ወደ ብስጭት የተመነዘረብን ብዙ ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ መንግስት ልማት የሚለው ከእኛ አፍ “ቫት” እያለ የሚነጥቃትን ገንዘብ ሰብስቦ ለሌቦች ካጠገበ በኋላ፣ በፍርፋሪዋ የሚሠራትን መንገድና ጤና ጣቢያ ወይም ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ “ኮንደሚኒየም”
እየተባሉ የተሠሩት ቤቶች አካባቢ ያለውን ግድየለሽነት ተመልከቱ፡፡ የውሃ መፍሰሻ ቦዮቹ ገና ተሠርተው ሳያልቁ ይፈርሣሉ። ሕንፃው ውስጥ ያሉትን የግብር ይውጣ ሥራዎች ተውአቸው፡፡ ለመሆኑ ልማትና ዕድገት ምንድነው? ወረቀት ላይ የሃሰት ሪፖርቶችን ከምሮ መቀለድ ነው። ቀልድና ውሸትስ እስከ የት ያዘልቀናል? ከወር ወደ ወር ሰዎች በልተው የማደር አቅማቸውን እያጡ፣ ልጆቻቸውን ማስተማር ተራራ መቧጠጥ እየሆነባቸው ሲመጣ — እንዴት ስለ ዕድገት ይወራል? ጋዜጠኛ መሳይ ካድሬዎች ስለልማትና እድገት ብዙ ቢለፈልፉም ከሕዝቡ የበለጠ ጓዳውን የሚያውቅ ማንም ሊኖር አይችልም፡፡ አለ ቢባልም ከተራ ቀልድነት አያልፍም፡፡ እርግጥ ነው፤ ባለፉት ሃያ ዓመታት ጥቂት ሰዎች በኑሯቸው አድገው ይሆናል፤ ለስላሳ መጠጣት የማይችሉ ዛሬ ቤታቸው ውስኪ ደርድረው የሚመርጡበት ዕድል ደርሷቸው ይሆናል፡፡
ያ ግን ዕድገት አይደለም፡፡ የማሕበረሰብ ሳይንስ ምሁራን የዕድገትና ልማትን ዓላማዎች እንዲህ ያስቀምጡታል – የሕዝቡን የገቢ መጠን በፍጥነት ማሳደግ ለዜጐች የሥራ ዕድልን መፍጠር መሠረታዊ የሆኑ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጐቶችን ማርካት፤ ማህበራዊ ፍትህን ማስፈን ሥራንና የቁጠባ ባህልን በሕብረተሰቡ ማስረጽ መልካም አስተዳደርና አሣታፊ የሆነ የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም ተጨማሪ ነጥቦች የአንዲት ሀገርንና ሕዝብን ዕድገት መንገድ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በሀገራችን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ከዚህ በተቃራኒ የቆመ ይመስላል፡፡ ምናልባት የማይካድ ለውጥ አምጥቷል ብለን የምንወስደው ሕብረተሰቡ በሥራ ላይ ያለውን አመለካከት በመጠኑ መቀየር መቻሉ ነው፡፡ ቁጠባውንም በውድም ሆነ በግድ በየሰበቡ ለማስለመድ የሚደረገው ጥረት የሚናቅ አይደለም፡፡ የፖለቲካው አሣታፊነት ጉዳይ የሕፃን ልጅ ዕቃ ዕቃን የመሰለ ቀልድ ስለሆነ ጉዳዩ ለሰለቸው አንባቢ ይህን አንስቶ እንዲህና እንዲያ ማለት እንደ ደንቆሮ መቁጠር ሊመስልብኝ ይችላል፡፡ ጠቃሚ ባህሎችን ማሳደግ በሚለውም መሥመር እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝብ (በመንግስት መሠረት) ሥነ ጽሑፉንና ባህሉን ማሳደጉን እኔ በግሌ እደግፈዋለሁ፡፡ ልክ ነው ብዬም አምናለሁ፡፡ አንዱ በባህሉ እየኮራ፣ ሌላው እያፈረ የሚደበቅባት ሀገር አሁንም እኩልነት የጐደላት ስለሆነች ያንን ሕልም ማለም ጠባብነት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ የሚያሣዝነው ግን በዚህ በጐሣ በተከፋፈለ ከለላና አስተዳደር ምክንያት የተፈጠሩት ጥላቻዎች ማርከሻ መድሃኒት ማጣታቸው ነው፡፡ መሪዎቻችን በወጣትነት መንፈስ በስሜታዊነት ያደረጉትን ነገር ምራቅ ሲውጡ እንኳን ለማስተካከል ያለመቅናታቸው የሚገርም ነው፡፡ ለዚህ ሃሳብ ዋቢ የሚሆነኝን አንድ ሃሳብ ወደኋላ መለስ ብዬ ሕዳር 18 ቀን፣ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በዶክተር እሸቱ ጮሌ አዳራሽ፣ ለዶ/ር ፋሲል ናሆም (ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ) ያቀረበውን ጥያቄ ልጥቀስ፡፡
ተማሪው የተወለደበትን ክልል ጠቅሶ፣ በክልሉ ዋና ከተማ የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ሀገራቸው እስከማይመስላቸው ድረስ በደል እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ገልፆ፣ መንግስት ለ “minority” ምን መፍትሔ አለው ሲል ጠይቆ ነበር፡፡ በሌላ አንፃር ደግሞ ያ ተማሪ እኖርበታለሁ ወይም ተወልጄበት ግን የዜግነት መብት አላገኘሁም የሚልበት ክልል ተወላጅ የሆነ ሌላ ተማሪ ተነስቶ፣ ችግሩ የሚታየው የቀደመው ተማሪ በጠየቀበት ክልል ብቻ ሣይሆን በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች መሆኑን ጠቅሶ፣ ሥራ ለመቀጠርም ሆነ ለሌላ ጉዳይ ዘር መቁጠር ግድ ስለሆነ፣ ችግሩን መፍታት ያለብን ሁላችንም ነን ብሎ ደመደመ፡፡ እኔ ግን በሁለተኛው ተማሪ ሃሳብ አልስማማም፤ ችግሩን ለመፍታት እኛ ድርሻ ቢኖረንም የአንበሳው ድርሻ ግን የመንግስት ነው፡፡ ስለዚህ መንግስት ለዚህ ነቀርሣ መፍትሔ መፈለግ አለበት፤ ሰው በገዛ ሀገሩ ባዕድ እየሆነና እየተገፋ መኖሩ የሚያመጣው ልማት ፈፅሞ ግልጽ አይደለም፡፡ ለመሆኑ መንግስት ማለትስ የሰዎች ስብስብ አይደለም እንዴ? እንዴት ይህንን ነገር ማሰብ ያቅተዋል? ባለሥልጣን ሲኮን ተከትሎ የሚመጣው አጃቢ ወታደር፣ ያበጠ ወንበር— የነገን ጉዳይ ያዘናጋልና መሪዎቻችንም ሊያስቡበት የሚገባ ይመስለኛል። አብዛኛው ሕዝባችን ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ኑሮ እያቃተው ከመጣ፤ የመኖር ዕድሉ እየጠበበ ከሄደ ሊፈጠር የሚችለው ነገር ምንድነው ብሎም ማሰብ ደግ ይመስለኛል፡፡ የኢሕአዴግ አማካሪዎች ምናልባት እውነት የማይናገሩ አሸርጋጆች እንዳይሆኑ እሠጋለሁ። ሕዝቡ እየተራበ “ጠግቧል”፣ እየተማረረ “ደስተኛ ነው” እያሉ ከሆነ ፍፃሜው አያምርም። በርግጥ እኛ ሥልጣን የሌለን አስበን ምንም አናመጣም፣ ሥልጣን ያላቸው ናቸው ለችግሩ መቋጫ መፍትሄ ሊያበጁለት የሚገባቸው፡፡
አዲሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆኑ ሁልጊዜ የታላቁ መሪያችንን መዝሙር ከመዘመር ይልቅ አዲስ መዝሙርና ራዕይ ለመፍጠር መሞከር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቶማስ ጀፈርሰን፤ ሁሉም ሰው የየራሱ ዘመን አለው፣ በሕይወት የሌለ ሰው በሕያው ሰው ዘመን ሊወስን አይችልም እንደሚል፣ አሁን ያለውን ኑሮና ሕይወት የማያዩት የቀድሞው መሪያችን ራዕይ ሊያዘልቀን ይችላል ብሎ ማመን ያስቸግራል፡፡ ርግጥ ነው ያስጀመሩትን ግድብ ማጠናቀቅ፣ የባቡሩን ሥራ መፈፀም፣ ወዘተ ጥሩ ነው። ግን በጤፍ ዋጋ፣ በስኳርና በትራንስፖርት ጉዳይ ያለውን ጣጣ ዛሬ ቢያዩ፣ እሳቸውም ደንግጠው ጭንቅላታቸውን ይይዙ ነበር፡፡ በዓመት ውስጥ ለአንድ የሆቴል ተመጋቢ ቢያንስ ሦስቴና አራቴ ዋጋ ይጨምርበታል፡፡ ታዲያ ሆዱ ባልጠገበ ሲቪል ሠራተኛ ተሠርቶ፣ ሀገርን ማሳደግ ይቻላል እንዴ? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሕልም ያልሙ እንጂ — አዲስ ራዕይ ያምጡ! የስነ አመራር ምሁሩ ጆን ሲ ማክስዌል እንደፃፉት፤ በየዓመቱ ዶሮዎቹን የክረምት ጐርፍ የሚወስድበት ዶሮ አርቢ፣ ሁልጊዜ በዶሮ ላይ የሙጢኝ ማለት የለበትም፤ ይልቅስ ጐርፉ ላይ ዋኝቶ አልፎ ሀብት የሚሆን ዳክዬ የማርባት ጥበብና ዘዴ ሊኖረው ይገባል። መቼም መንግስታችን ሁልጊዜ በሕይወት በሌሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ መንጠልጠል ያለበት አይመስለኝም፤ እሳቸው በጊዜያቸው የሚሰሩትን ሰርተው አልፈዋል፡፡ አሁን ተራው የሥልጣን ወንበሩ የተሰየሙት ሰውዬ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ. ጆንሰን እንዳሉት፤ ድሀና ሀብታም በጠብደል ግድግዳ ሲለይ ጥሩ አይደለም። ይልቅስ ግድግዳው የመስተዋት ነውና በኋላ የሚያመጣው መዘዝ መጥፎ ነው፡፡ ከፊሉ በሌብነት እየበለፀገ፣ ሌላው በጨዋነት እየተራበ – ለዘላለም – አይኖርምና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ዶክተር መረራ ጉዲና እንደሚሉት፤ የራበው ሕዝብ – መሪውን ለመብላት እንዳይነሣ – ካሁኑ ማሰብ የግድ ይላል፡፡ ጆንሰን – “There are two courses open to us. We can master the problem, or we can leave it to master us” ብለዋል – የኛም ምርጫ ይኸው ነው። አዲዮስ!

ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደት ጥሪ ለሰማያዊ/መኢአድ/መድረክ/አረና/ኢዴፓ አቀረቡ


  ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደት ጥሪ ለሰማያዊ/መኢአድ/መድረክ/አረና/ኢዴፓ አቀረቡየአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ «በመድረክ ዙሪያም ሰፊ ዉይይት ያደረገ ሲሆን፣ አዲሱ ብሄራዊ ምክር ቤት፣ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ፓርቲው ከመድረክና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የጀመረውን ውህደት እልባት እንዲያበጅለት መመሪያ ሰጥቷል» ስንል መዘገባችን ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ አስተያየት ያደረጉት አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ድርጅታቸው ከአሁን በኋላ በግንባርነት እንደማይሰራ ገልጸዋል።
ድርጅቶች ልዩነቶቻቸዉን አጣበው ወደ ዉህደት በመምጣት፣ በጋራ ትግሉን ወደፊት ማራምድ እንዳለባቸው የገለጹት ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደትን ጥቅም አጠንክረው አስምረዉበታል። ለመኢአድ፣ ለመድረክ፣ ለሰማያዊ ፓርቲ፣ ለአረና እንዲሁም በአቶ ልደቱ አያሌዉ ይመራ ለነበረዉ ለኢዴፓም ጥሪ አቅርበዋል።
ዉህደት ማድረግ ካልተቻለ ግን፣ አንድነት ለድርጅቶች እዉቅና ሰጥቶ መተባበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ (እንደ በጋራ ሰልፍ መጠራት የመሳሰሉ) ትብብር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል የሚገልጽ እድምታ ያለው ንግግር ነበር ኢንጂነር ግዛቸው ያቀረቡት።
መኢአድና አረና ከአንድነት ፓርቲ ጋር የመዋሃድ ፍላጎት እንዳላቸው ከዚህ በፊት ማሳወቃቸው፣ በዚህም ረገድ አንዳንድ ንግግሮች እየተደረጉ እንደነበረ ይታወቃል።
የመድረክ አባል ድርጅቶች ከአንድነት ጋር ለበርካታ አመታት አብረው የሰሩ እንደመሆናቸው የጠነከረ መቀራረብ ሊኖራቸው እንደሚችል ቢታወቅም፣ በዉህደቱ አንጻር ግን ምን ያህል ከአንድነት ጋር ለመዋሃድ እንደሚፈልጉ፣ ምን ያህል ያላቸውን መሰረታዊ የፖለቲካ ልዩነቶች ለማጥበብ እንደሚችሉ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም።
ሰማያዊ ፓርቲ ለጊዜዉ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት አዝማሚያ ያለው አይመስልም። ነገር ግን በአንድነት ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ተጨባጭ ለዉጦችን በመመልከት የአቋም ለዉጥ ሊያደርግ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።
የዉህደቱ ጥሪ ለኢዴፓ መቅረቡ ብዙዎችን ሊያነጋገር የሚችል አዲስ ዜና ነው። በአንድነት አካባቢ ከኢዴፓ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት መታየቱ፣ በቅርቡ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ አቶ ልደቱ አያሌው ላቀረቡት በጋራ የመስራት ጥሪ፣ ምላሽ ተደረጎ ሊወስድ የሚችልበት ሁኔታም ሳይሆን እንደማይቀር ነዉ።
ኢንጂነር ግዛቸው ለተቃዋሚ ድርጅቶች የዉህደት ጥሪ በማቅረብ ብቻ አልተወሰኑም። ገዢዊ ፓርቲ ኢሕአዴግ የከረረ አቋሙን ቀይሮ ለእርቅና ሰላም እንዲዘጋጅም አሳስበዋል።

በጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) የተሰጠ መግለጫ


Semayawi Party- Ethiopia's photo.ሆኖም፣ የነዚህን ሀገር ወዳድ ዜጎችና አፍቃሪ-ኢትዮጵያውያን ጥሪና መግለጫዎች ከቁብም ካለመቁጠር፣ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሥውር የሥልጣን ማራዘሚያ ደባዎችን እየሸረበ እንደሚገኝ አጋልጠዋል። ወያኔ ራሱ ያቋቋመው “የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ኮሚቴ” አባላት ራሳቸው በተለያዩ ቃለ-ምልልሶች እንዳጋለጡት፣ ወያኔ በአባቶቻችን ደም ተላቁጦ ለተቦካውና የበርካታ ሰማዕታትን ህይወት ላስከፈለው የኢትዮጵያ ድንበርና የግዛት ሉዓላዊነት ግዴለሽነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊ ግዛትና ድንበር “በጫካ ውሎችና ስምምነቶች” እያመካኘ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
ይህንንም ከፍተኛ የሆነ የሃገር ክህደትና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ለማስተባበል በመገንዘብ፣ የወያኔ-ኢህአዲግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ ላይ በመስከረም 2002 ዓ.ም መጨረሻ ላይ አንድ የማደናገሪያ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከዚህም የማደናገሪያ መግለጫ ውስጥ የሚከተሉትን ሦስት(3) አበይት ጉዳዮች መገንዘብ ይቻላል። እነርሱም፦
1ኛ. የኢትዮጵያና ሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ (Ethio-Sudan Political Committee) ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ አካል መኖሩንና የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) በፖለቲካው ኮሚቴ ሥር እንደሚሠራ አረጋግጧል፤ የዚህ የኮሚቴ መዋቀርና የአሰራር ሂደቱም ለረጅም ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ተደብቆ የቆየ እንደሆነና፣ ወያኔ-ኢህአዲግም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ክትትል መጋለጡን ሲያውቅ ተጨንቆ ያወጣው ምስጢር ነበር።
2ኛ. የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) ከጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 15, 2009) እስከ ግንቦት 2002 ዓ.ም.(May 2010) ድረስ የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይስና ቅኝት እንደሚያደርግም ገልጾ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ ሲጋለጥ ያወጣው ሌላው ምስጢር ሲሆን፣ (ሱዳን ትሪቢውን ያወጣውን ዜና የሚያጎለምስ) እና የሱዳን ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበሩን ለማካለል የሚያደርገውን ዝግጅት የሚያስተጋባ ነው።
3ኛ. የድንበር ክለላው ከግንቦት 2002 ዓ.ም. ( May 2010) በኋላ እንደሚደረግና ከዚህም ጋር አያይዞ ወያኔ-ኢህአዲግ ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት አምነው የተቀበሉት የድንበር ክልል እንዳለ አስምስሎ ለማቅረብም ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ወያኔ-ኢህአዲግ አሁን የሚያካሂደው “የድንበር-ክለላ ሂደት” ዳግም ድንበርን የመከለል ተግባር ( re-demarcation ) እንደሆነ መግለጹ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ይህ ማደናገሪያና ተራ ልፈፋ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማወናበድና ግዛቱን በጫካ ውሎችና ስምምነቶች አማካይነት አሳልፎ ከመስጠት የዘለለ ኢምንት እውነታ የለውም፡፡ ይሄንን በተመለከተም ያጠኑት ሊቃውንትንና በግዛቱ ላይ የሚኖሩትን ዜጎች ምስክርነት ሊያገኝ አልቻለም፤ አይችልምም፡፡
የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት “ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት የተቀበሉት የድንበር ክልል” የሚለው ሀተታ፤ ሜጀር (ሻለቃ) ጉዊን የተባለው የእንግሊዝ ጦር መኮንን በ1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) “አስምሬአለሁ” የሚለውን የወሰን ክልል ነው። ይሁንና አንድ በእንግሊዝ የቅኝ-ገዥነት አባዜ የሰከረ ሻለቃ ያሰመረውን መስመር መሠረት አድርጎ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉዓላዊነትን የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን “ለሱዳን ይገባታል” ብሎ መሟገቱ የፖለቲካ ቅጥፈት እንጂ ታሪካዊ ማስረጃ የለውም፡፡ የሚከተሉትም ታሪካዊ ዳራዎች የወያኔን ሙግት ውድቅ ያደርጉታል፦
1ኛ.ሻለቃ ጉዊን መሬቱን አካልያለሁ ሲልና በወረቀት ሲያሰምር፤ በኢትዮጵያ በኩል አንድም ተወካይ ስለአልነበረ የጉዊን የድንበር ማካለል ተግባር ከቅኝ ገዢዎች ማንአለብኝነት ተለይቶ የማይታይና የውል አፈጻጸም ሥርዓት የማይከተል በመሆኑ የተነሳ ተቀባይነት የለውም፡፡
2ኛ. የ1896 ዓ.ም.(እ.አ.አ.) የአድዋ ጦርነት ድል በቅኝ ገዥዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ መደናገጥ ምክንያት 1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) አካባቢ እንግሊዝና ጣሊያን በጋራ በመመሳጠር የሰሜንና የምዕራብ ኢትዮጵያን ድንበር ለመግፋት የፈፀሙት ሴራ ስለሆነ፣ የሻለቃ ጉዊን ተልዕኮም ከዚያ ሴራ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ስለሆነም ተቀባይነት የለውም፡፡
3ኛ. ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በፊትም ይሁን ከዚያ በኋላ፣ ይህ ሻለቃ ጉዊን ከለለው የሚባለው መሬት ምን ጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይባስ ብሎም፣ በአፄ ቴዎድሮስና በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ግዛት አሁን ሱዳን ተብሎ ከሚጠራው ሃገር በጣም ወደ ውስጥ የገባ ነበር፡፡ ስለሆነም፣ የግዛት ጥያቄ ሲነሳ የይገባኛል ታሪካዊ መሠረት ያላት ኢትዮጵያ መሆኗን ለማስተባበል አዳጋች ነው፡፡
4.አሁን የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት በመጋቢት 22/2006 ዓ.ም ገደማ March 30, 2014 ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ግልጽነትና ተጠያቂነትን መርሆው ያላደረገው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ግን አንዳችም መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያገኝ የተለመደ አፈናውን ገፍቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ በእልፍ-አዕላፍ ድንበር ጠባቂ ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ተጠብቆ የኖረውን ዳር ድንበር፣ ወያኔ በተለመደ “የደጃዝማቾች ፈረስ መጠጫና ጉግዝ መጫወቻ ነው” በሚል ንፍገት አሳልፎ ለሱዳን ሊሰጠው ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሰፊ ውሃ-ገብና ለም ሉዓላዊ መሬት፣ የታሪክ ማስረጃዎችንና የኢትዮጵያውያንን መስዋዕትነት በማናናቅ ለባዕዳን ሊሠጥ አይችልም፡፡
ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ማስረጃዎችና በዓለም-አቀፍ የአሠራር ደንብ መሠረት፤ ወያኔ-ኢህአዲግ ከሱዳን ጋር የሚያደርገው የድንበር ክለላ ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። ከዚህም ባሻገር፤ ከዋናው ባለጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት ይሁን የድንበር ክለላ ተግባር ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም።
ከዚህም ሌላ፣ ወያኔ-ኢህአዲግ የተወሰኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት ቆርሶ በመስጠት ሥልጣኑን በጎረቤት አገር ሱዳን ለማስባረክ ብሎ የሚያደርገው ሽር-ጉድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም፡፡ ውጤቱም “ታግዬላቸዋለሁ የሚላቸውን ብሄሮችና ብሔረሰቦች” ከማዳከምና ብሎም ለማፈራረስ የተጠቀመበተ ዘዴ የቅኝ ገዢዎች ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ ያሰመሩትን የድንበር መስመር በመቀበልና የቅኝ ገዢ ጠበብትን እንደ ምስክር በመጠቀም ነው። ይህም ተግባሩ፣ቀድሞውንም በቋፍ የነበረውን የወያኔ-ኢህአዲግን መንግሥት የፖለቲካ ቅቡልነት የሚያሳጣው መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ አልፎ-ተርፎም በዚህ ተግባሩም ዛሬም የቅጥረኛ ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ህዝቡ እንዲያውቀው እንፈልጋለን፡፡
ይህ የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን ተግባር የሃገራችን ኢትዮጵያን ዓለም-አቀፍአዊ ክብር የሚጎዳ ስለሆነ ከተግባሩ እንዲታቀብ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም፣ ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ዝርዝር መረጃና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበትም ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ ይህን ሳያደርግ ቢቀር ግን፣ ፓርቲያችን የተጣለበትን የአባቶቻችንን ክብርና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መቼም ቢሆን ያለምንም ማወላወል የምንወጣ መሆናችንን ለጉዳዩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ኅዝብ በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡
ሰላም፣ ተስፋ፣ ፍትህና እኩልነት በዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በተከበሩባት ኢትዮጵያ ዕውን ይሆናል!!!