Sunday, February 2, 2014

State Minister of Ethiopian Federal Affairs defects – የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከአገር ኮበለሉ



 The Ex-President of the Gambella Regional Administration of Ethiopia and the current State Minister of Ethiopian Federal Affairs, Omod Obong has defected. The Addis Abeba based weekly Amharic Newspaper, Addis Admas, reported today that Omod had left the country on an unofficial travel and has not re...turned to his post since. The Paper stated that the State Minister had told his colleagues in Ethiopia that he would not be returned back to Ethiopia. The Newspaper did not disclose to which Country Omod had left for.

አበባየሁ ገበያው

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ አቶ ኡመድ ኡባንግ፤ ከአገር መኮብለላቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡
አቶ ኡመድ ኡባንግ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከሃገር መውጣታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱ ለሚቀርቧቸው ሰዎች መናገራቸውን አመልክተዋል።
የሚኒስትር ዴኤታውን መኮብለል በተመለከተ የጠየቅናቸው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም፤ አቶ ኡመድ በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን
ገልፀው መስሪያ ቤታቸው ለተለየ ተልዕኮ እንዳላሰማራቸውና ፈቃድ ሳይጠይቁ ከስራ ገበታቸው እንደቀሩ ተናግረዋል፡፡ ሚ/ር መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡ አቶ ኡመድ ከጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱት በክልል መንግስቱ የስራ አፈፃፀም ላይ ለአንድ ሳምንት ከዘለቀ ግምገማ በኋላ ሲሆን፤ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናትም በዚሁ ግምገማ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡

Source : አዲስ አድማስ

No comments:

Post a Comment