Saturday, February 8, 2014

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራር ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !


saudi ethio13


በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራር ኮሚቴ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በታደሙ አባላት እና የአምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ በሚታወቁት የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ደጋፊዎች መሃከል ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት አምርቶ እንደነበር ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል።
የስብሰባውን ታዳሚ ግራ ያጋባው ይህ ግጭት መነሻው የቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሼክ ሙሰጠፋ ሁሴን ለምን ከስልጣኔ ተነሳሁ በሚል በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ላይ ቡጢ መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሼክ ሙስጠፋ ከስብሰባው በፊት ሲያስተባብሯቸው የነበሩ ከ 50 የሚበልጡ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት ሁከት የመስብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ማምሸቱን ጠቅሰዋል።
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ በአካባቢው የተፈጠረውን አለመረጋጋት የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባውን ለሌላ ቀን ለማስተላለፍ መገደዱን የሚገልጹት ምንጮች የሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች ጩቤ ታጥቀው ወደ አዳራሹ ገብተው እንደነበር ቢገልጹም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ውስጥ ዛሬ በተነሳው አምባጓሮ የተጎዳ ሰው እንደሌለ አረጋግጠዋል። ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ቀደም ሲል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር እንደነበሩ እና ምንጩ በግልጽ የማይታወቅ ሁለት ሚልዮን ሪያል በግል ካዝናቸው ተገኝቶ በሳውዲ መንግስት የደህነንት ሃይሎች ታስረው መክረማቸውን ተከትሎ የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በማህበሩ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መስረት የስልጣን ሽግሸግ ለማድረግ በመገደዱ ግለስቡን ከሃላፊነታቸው ማስወገዱን ይናገራል። ዛሬ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ተከስተ በተባለው ሁከት በሳውዲ የኢትዮጵያው አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን እጅ እንዳለበት የሚገልጹ ወገኖች ሃገር እና ህዝብን ወክሎ ከተቀመጠ አምባሳደር የሚጠበቅ እንዳልሆነ በማውሳት ድርጊቱን አውግዘዋል።
ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ የአምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ዝምድናን መከታ በማድረግ በኤምባሲው ማህተም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጀቶች ገንዘብ በመሰብሰብ ከአምባሳደሩ ጋር ለግልጥቅማቸው ሲያውሉ የነበሩ መሆናቸውን የሚያወጉ የሪያድ ነዋሪዎች ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ኢትዮጵያ ውስጥ በከፈቷቸው 2 ኤጀንሲዎቻቸው በመታገዝ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እስከ 7 መቶ ዶላር በመሰብሰብ በእህቶቻችን ህይወት ሲነግዱ የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ በህገወጥ የሃላ ንግድ ተሰማርተው ከቀርብ ግዜ ወዲህ የከበሩ ሃብታም ነጋዴ እና የአምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ባለውለታ መሆናቸው ይናገራል ።
ዛሬ ተቀሰቀሰ በተባለው ግጨት ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ የዲያስፖራውን ሃላፊ ለማነገጋር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን ከህወኒ መውጣት እና እጃቸው ላይ ተይዞ ስለነበረው 2 ሚሊዮን ሪያል «10 ሚልዮን ብር » የደረሱንን መረጃዎች ወደፊት አጠናቅረን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፤
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት
http://www.goolgule.com/

No comments:

Post a Comment