Thursday, February 20, 2014

ወያኔን የሚጠላ ብቻ እየተመረጠ የሚያብድባት ሀገር


ከተወልደ በየነ(ተቦርነ) የካቲት 19 2014
በአንድ ወቅት የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፈን ወደ አንድ የአእምሮ ህመምተኞች ሆስፒታል ለመጎብኝት ያመራሉ:: በመጀመሪያ ያገኛቸው የአእምሮ ህመምተኛ አቀባበል ያደረገላቸው እንዲህ በሚል ነበር
“የባለቤትዎን የ22 ዓመት የስራ ውጤት ለመጎብኘት እንኳን ደህና መጡ::” መራር እውነት ያለው ቀልድ::
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወያኔ የተባለው የስብስብ ቡድን በአመራሩ ተማረው ከህዝብ ወግነው ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር ብለውጥያቄና ተቃውሞ የሚያነሱ የህዝብ ወገኖችን በተለያዩ መንገድአሳንሶ ለማየት የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች እየተጋለጡና እያሳጡት ከመጡ ሰነባበቱ:: የቅርብ ጊዜውን እንኳን ብናስታውስ የመምህር የኔሰው ገብሬን ሰላማዊ የተቃውሞ መስዋዕትነት አጣጥሎና አሳንሶ ለማየት በአእምሮ ህመምተኝነት በተለያዩ እፅች ተጠቃሚነት መወንጀሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ያለውን የአፈናና የጭቆና ስርዓት በሞያው መስዋእትነት ከፍሎ ለአለም ያሳወቀውን ጀግና ረዳት ካፒቴን ሀይለመድህን አበራ የጤንነት ችግር እንዳለበት ተደርጎ እህቱ ነኝ በምትል ግለሰብ በተለያዩ ድረ ገፆች የሀሰት አሉባልታዎች ማናፈስ ጀምረዋል::
እኔ ለእነዚህ ፈጣን የአሉባልታ አናፋሽ ባለሞያዎችና ቤተሰብነን ባዮች 3 ጥያቄዎችን ማንሳት እወዳለሁ::
ጥያቄ 1:- እንደዚህ በፍጥነት የረዳት አብራሪውን የጤንነት ችግር ለማሳወቅ የፈጠናችሁትና የጣራችሁትን ያህል ምነው ስለ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አሟሟትና የህመም አይነት ለመናገር ጊዜ ወሰደባችሁ? ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቆርቋሪ ቤተሰብና አጣሪ ባለሞያ የላቸውም?
ጥያቄ 2:- የህውሃት ነባር የኪነት ቡድን አባላት የነበሩ ዘጠኝ ታጋዮች ወደ ሱዳን በጉዞ ላይ ሳሉ በበሬና አሞራ ጣምራ ስህተት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል ታዲያ እንዲህ ችግሮች ሲፈጥሩ አጣርቶ ውጤቱንና ምክንያቱን የሚሳውቅ ፈጣንየባለሞያ ስብስብ ካለ የነዛ ታጋዮች ገዳይ የሆኑት የአሞራውና የበሬው ጤንነት ተጣርቶ ለምን እንደ አሁን ፈጥኖ አልተነገረንም ነበር?
ጥያቄ 3:- የመጨራሻው ጥያቄዬ የህወሀትን የትግልና የጀግንነት ገድል በሚተርከው ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ መፅሀፍ ላይ የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ስዩም መስፍን ታሪክ የሚዘክረው ቦታ ለይ በአንድ ወቅት አቶ ስዩም መስፍን በጠላት እጅ ወድቀው ለማምለጥ የተጠቀሙት ዘዴ እብድ መሆንን እንደነበር ማንበቤን አስታውሳለሁ::
ታዲያ አቶ ስዩም ለአላማቸው ሲሉ ያደረጉትን እብደት የኛው መምህር የኔሰው ገብሬና ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ለዓላማቸወ ሲሉ ቢያደርጉትስ ምን ያስገርማል?

ቸር እንሰንብት

No comments:

Post a Comment