Saturday, February 15, 2014

ሴቶች ላገራችን ነፃነት ነገ ዛሬ ሳንል መነሳት ይኖርብናል...!!!

ገራችን በታሪክ ዘመኗ የብዙ ታላላቅ ሰዎችና የጀግኖች እናት እንደሆነች ታሪክ አበክሮ ይዘክራል ።                                            ከነዚህ ታላላቅና  ጀግኖች ቶቻችን በስተ ጀርባ ጠንካራነታችው፣ብልህነታቸው ከምንም በላይገር ወዳድነታቸው ሁሌም ልናስታውሳቸው የሚገባን ጠንካራ እናቶች እንደነበሩ ታሪክአስቀምጦልናልየታሪካችን አመጣጥና የጀግኖቻችንን ዋነኛው ምክንያት አገራችን ከመውደድእንዴውም ላገራችን ካላቸው ትልቅ አክብሮትና ፍቅር የመጣ መሆኑን ሁላችንም ልብ ልንንይገባል።
                     ለቀባሪው አረዱት አይሁንብኝና !!
               ሰለ ውብ ታሪካችን ትንሽ አወጋችዋለው!!
  የታሪካችን አመጣጥ እጅግ  ማራኪ መላውን  ዓለም ያስደመመ  ሲሆን ፣ባለን ባህል እጅግ የምንኮራከባእድ የወረስነው ሳይሆን  ከራሳችንን የመነጨ ቱባ ባህል ያለን ድንግል መሬታችን  ከኛ  አልፎ ለሌላው  ጥጋብ  ሊሆን የሚችል አንጡራ ሃብት ያለን ከዚህም በላይ ተሳስበው እና ተከባብረውየሚኖሩ  ሃይማኖቶችየተለያዩ  ቋንቋ ተናጋሪ ብሄር ቤረሰቦች ያሉባት  ታላቅ ገር ናት 
ኢትዩጽያ ያከበራትን እጅግ የምታከብር ስትሆን ለተነኮሳት እና ሊከፋፍላት አስቦ ለመጣ ግን አዋርዶየመመለስ አቅም ያላቸውና ለሃገራቸው ከወንድ የማይተናነሱ ብልህ ሴቶች እንዳሏት የሞሶሎኒውርደት አብይ ምሳሌን ነው
 ስለ ራችን ሴት ጀግኖች ሲነሳ ዛሬ በሙሉ ልብ ጀግንነታቸውን፣አገር ወዳድነታቸውን ፣ብልህነታቸውን ከምንም በላይ አይበገሬ ነታቸው መናገር እንድንችል ታሪክ አስቀምጦልናል  አገርማለት ህዝብ ነው የሚለውን መርሆ ይዘው በመነሳት ሃገራቸውን እና ዝባቸውን አክብረውናከጠላት ጠብቀው ለትውልድ ካስተላለፉ ከጀግኖች አባቶቻችን በተዳኝ ልጅን ከመንከባከብ እናከማጀት ስራው  ጎን ለጎን ጀግና እንስቶች እንዳሉ ታሪክ ካስቀመጠልን ላገራቸው ያላቸውን ፍቅር በጀግንነት ካሳዩት መካከል ንደ ምሳሌ ጣይቱን ልንወስድ አንችላለ
    የዓገራችንን ጀግና አናቶች ታሪክ በመከተል ዛሬ እኛምባለንበት ዘመን አገር ማለት ህዝብ መሆኑን የሚያምኑህዝብ ከሌለ አገር እንደሌለ ተገንዝበው ወገኖቻቸውንሲዋረዱ፣ሲጨቆኑ ፣ሲራቡ ሰብአዊ  መብታቸውሲገፈፍ፣የመናገር መብታቸው ሲገደብ፣ በየቦታውእሬሳቸው  የአሞራ ሲሳይ ሲሆን፣ድምጻቸውሲታፈን ፣ነፃነታቸው ሲነጠቅ ማየት ያላስቻላቸውናየወገኖቻቸው መንገላታት የእግር እሳት የሆነባቸውየህዝባችን ህመም ያመናል፣ስቃያቸው ስቃያችን ነው፣እውነት መታፈን የለባትም 
ብለው የወገኖቻቸውን ድምጽ በማስማታቸው እና ለእውነት ወግነውበመቆማቸው ብቻ ኢሰባዊ ድርጊትና ከፍተኛ ስቃይ እንዲሁም የሴትልጅ  እርግዝና አመቺ በሆነበት ቦታ ላይ እንን እጅግ ፈታኝ  በሆነበትሁኔታ ለነፃነታቸው በመቆማቸው ብቻ ጊዜ ዓቸውን  አስከፊ  በሆነውስር ቤት  ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲወጡት ታይቷል። 
ኢትዮጽያ ላይ እንደ ወረርሽ  በመነሳት በህዝቦች እና በሃይማኖቶችመካከል የቆየ አብሮ የመኖር ,የመተሳሰብ እና የመቻቻል ድንቅ የሆነየአኗኗር ዘይቤአችንን  ለማጥፋት  ሆን  ብሎ የተነሳው አምባገነኑ የህወሃትመንግስት የንጹሃንን ደም በማን አለብኝነት አፍስሷል ። 
የህወሃት ቡድን ብቻ የሚወክሉት  ፍጹምየኢትዮጵያዊነት ገፅታ በሌላቸው እንደመዥገር በኢትዮጵያዊያን አካልላይ ተጣብቀው ደም በመምጠጥ የሀገሪቱን ግብአተ መሬት ለማስፈጸም  እና ለብዙ ወገኖቻችን እንደቅጠልመርገፍ ፣መንከራተት ፣ መዋረድና  መበታተን ፣ በአሰቃቂ  ሁኔታ መሞት  በተለይም ለሴት ህቶቻችን ከዓገራቸው እርቀው ንዲሰቃዩና ለእይታ በሚከብድ ሁኔታ እንዲደፈሩ ፣ እንዲንገላቱ ፣እንዲሁም  ለተለያዩ ችግርና ስቃይ እንዲዳረጉ ሌት ተቀን የሚሰሩ  የወሮበላ ቡድን የሆነው የህወሃት  ለዚ ድርጊቱ ተጠያቂነውይህ ብ  ፈርጀ ብዙውን ኢትዮጵያዊ ደለም ከጉያው ለወጡት የትግራይን  ህዝብ  እንኳን የማይወክል ጠባብ  እና ጎሰኛ  ቡድን ነው።

ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁም ነው እና
ከቀድሞ ታሪካችን ምሳሌ በመውሰድ በዚዘመን ጀግና እንስቶች  እንዳሉንና አገራችን በባንዳ ስትታፈን አናይም ብለው መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ዛሬ  ቤተሰቦቻቸውን በትነው ክፉ ና ደጉን መለየት ያልቻሉ ልጆቻቸውን በዚህ  አፋኝ መንግስት ምክንያት ለማየትና ለማቀፍ ያልታደሉ በእስር የሚገኙ ለመብታቸው እና ለሃገራቸው ከቆሙት ኢትዮጽያዊያን መካከል በዋነኝነት ሊጠቀሱ የሚገባ ሴት ጀግና ኢትዮጽያዊያን ዛሬ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

በኛም ዘመን ጀግና ጣይቱ፣ጀግና ዘውዲቱ...ወ.ዘ.ተ እንዳሉን በማወቅ እኛም ከነሱ ምሳሌ በመውስድ ላገራችን በመቆም የመናገር መብታችንን በመጠቀም የወገኖቻችንን አይን እና ጆሮ  የሆነውን ኢሳትን በመርዳት እኛም እንደ ሴት ጀግኖች ወገኖቻችን ለሃገራችን በመቆም ሃገራችንን እና ህዝቧዋ ትከሻ ላይ ተቀምጦ አልወርድ ካላት ከዚህ  ክፉ መንግስት ለማላቀቅ የሴትነት ብልሃታችንን  እንደ ጥንት እንስት ጀግኖቻችን በመጠቀም ለሃገራችን ነፃነት ነገ ዛሬ ሳንል መነሳት ይኖርብናል።
ራሄል ኤፍሬም

No comments:

Post a Comment