Wednesday, February 12, 2014

የአቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ ተደበደበ


  • digg
  • 571
     
    Share
1507855_406582846154533_728831923_n
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንጠቆሙት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 1 እና የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም(ቅዳሜና እሁድ) ለሊት በተደጋጋሚ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ መደብደቡን ተከትሎ ቤታቸው ቀንና ለሊት በፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡
አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ የሚያዋርድና የሚዘልፍ ንግግር ሲያደርጉ የተቀዳ ድምፅ ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በብአዴን ውስጥ የንትርክ ምክንያት መሆናቸው አይአነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment