To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Sunday, February 23, 2014
ሀበሻ በየመን ክፍል አንድ
በድጋሚ የተሻሻለ
ጥቁሯ ቦርሳዬ የያዘቻቸው ነገሮች ብዙ እና የሚገርሙ ናቸው ልናወራ ጀምረናልን እና እነሆ በረከት ልል እየተንደረደርኩ ነው…ሰላምታዬን ላቅርብ…. ለመሆኑ እንዴት ናችሁ? አቀማመጣችሁን አላልኩም። አቀማመጣችሁማ ወንበረችሁ ላይ ሆናችሁ ኮምፒዩተራችሁ አለያም ሞባይል ስልካችሁ ላይ አፍጥጣችሁ ይመስለኛል የምታነቡት። ካሆነም ልክ አልገመትኩም ማለት ነው፡፡ ሀገር ውስጥ ያላችሁ ቫት ከመብላት እስከ መሽናትእንዴት አደረጋችሁ? እሺ በስደት ያላችሁ..የስደት ኑሮ ቅብብሎሹ እንዴት አድርጓችሁዋል? እንዴ ምነው ተገረማችሁ? ልክ ነኝ እኮ ኑሮ ቅብብሎሽ አይደል እንዴ? ሰኞ ወደ ማክሰኞ ሲጠልዘን፤ ማክሰኞ ተቀብሎ አባብሎ ወደ ረቡዕ ሲወረውረን .. መስከረም ወደ ጥቅምት ሲጠልዘን፤ ጥቅምት ለህዳር፣ ህዳር ለታህሳስ…እያለ ቅብብሎሹ በርትቶ ጥለዛው ደርቶ እዚህ ደርሰን የለ? አሁንም ቅብብሎሹ አንዱ ወደ አንዱ መለጋቱ እንደቀጠለ ነው። ገና እንለጋለን፤ እንጠለዛለን። ስንት አመት ይሆን በቅብብሎሹ ውስጥ የምናሳልፈው?...ማን ያውቃል ከአንድዬ በስተቀር…እድሜ ይስጠን፡፡ ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለአቢይ ፆም መግቢያ አደረሳችሁ…
አቦ ዛሬ ጣፋጭ ወግ (ስደት ላይ ጣፋጭ ነገርን ምን አመጣው እንዳትሉ..) እናውጋ ነው የሚባለው የብሶት ቁስል እንከክ እንበለው? ስለስደት ብናወራ አይመቻችሁም? ከስደትም ስደት አስከፊውን የአረብ ስደት…ከአረብ ሀገርም ስለየመን ስደት እናውራ። ምነው ፊታችሁ ጨፈገገ? የስደት ነገር ሲነሳ ቤተሰብ ትዝ አላችሁ? ከፋችሁ? ወይስ ጎፈነናችሁ?….ወደ እውነታው እንምጣ ከኑሮ ጋር ያለውን ትግል ለማሸነፍ፣ ለመሸነፍም ቢሆን የትግል ሜዳ አድረጋችሁ የመረጣችሁት የመንን ነው እንበል። ምን እንበል ብቻ አልንና እየኖርንነው፡፡ የመንን በሀሳብ ለመቃኘት ተዘጋጁልኝ። የመን ደሞ ጥሩም አለ መጥፎም አለ። ሞቱም፣ ዱላውም፣ መደፈሩም፣ ማግኘት፣ ማጣቱም ሁሉም አለ። ከኋላ ተነስታ ሳዑዲ በጭካኔው እና አደባባይ ወገኖቻችንን ማሰቃየት እና በመግደል ብሔራዊ ውርደት አለበሰችን፡፡ ከሌሎች ሁኔታዎች የከፋ ሁኔታ አለ…
የመንም ይኖራል። ለጉድ!!..ይኖራል። ኑሮ ከተባለ ሀበሻ በየመንም እየኖረ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ስደት ነው። ወደ ተሻለው ሳይሆን ስደታችን…ብዙ ብዙ እውነት የማይመስሉ እውነቶች የተሰገጡበት ህይወት ነው በየመን ያለው። ኑሮ ካሉት ፍሪጅም ይሞቃል ኮካኮላን ያስተረተው በየመን ያለ ሀበሻን ኑሮ ታይቶ ነው ማለት ይቻላል። አይደለም ካላችሁም አሁን እኔ ብያለሁ። ማነው የሚከራከረኝ? ከየመን በከፋ ሁኔታ ላይ ሶማሊያ የሚኖሩ መኖራቸውን ሳትረሱ ማለት ነው። አትቸኩሉ እኔው እነሱንም አሳያችኋለሁ።
ችግር የማይነቅለው የለም። ኢየሱስ ክርስቶስም ተሰዷል። ነብዩም መሀመድም ተሰደዋል። አረ ቆራጡ እና ተፈጥሮን በቁጥጥር ስራ እናውላለን ያሉት ኮረኔል መንግስቱም ተሰደዋል። በመጽሀፋቸው ሰም ለበስ ቢያደርጉትም….እኛ ለስደት አዲስ አደለንም። አለም ለስደት አዲስ እንዳልሆነ ሁሉ እኛም እየተሰደድን ነው። ተሰደናልም ገናም እንሰደዳለን:: ግን የእኛው በዛ..
ሀበሻ በየመን እጅጉን አሰልቺ የሆነ ደግሞም ያልሆነ ዝብርቅርቅ ህይወት..ከጥሩ ጎኑ መጥፎው ያመዘነበት ኑሮ መሀል ተሰንጎ ነው የሚኖረው። በጥሩ እና መጥፎ ህይወት መካከል የተሰነግን (ሳንዱች የሆንን) ነን፡፡ ሀበሻ እርስ በእርስ የጎሪጥ መተያየት፣ እርስ በእርስ መባላት፣ ጥርጣሬ.. የበዛበት ነው ህይወቱ። መሰደብ.. <<ያ-ሀበሺ..ሸቃላ..ኦሪያ..ያ ሶማሌ..ያ አስወድ(ጥቁር)..>> የዘውትር መጠሪያ ኤጭ!..ድሮስ ክብር በሀገር አይደል? ነው እንጂ። ክብር በሌለበት ተንቆ፣ ተዋርዶ መኖር ያውም ከራስ ባልተሻለ ሰው። የመን ያለ የሀበሻ ቁጥር እንዲህ በዋዛ የሚሰላ አይደለም። በህጋዊ መንገድ ያለውና ህጋዊ ያልሆነው ከ70- 80 ይደርሳል ተብሎ ይገመታል። ታዲያ ይገመታል ነው። ይበልጣል እንጂ አያንስም። ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጓዡም ቀላል ተብሎ የሚጠራ አይደለም። አሁንም ከችግሩ በኋላ ጉዞው አንሰራርቶ ተጀምሯል፡፡
በእናታቸው፣ በአባታቸው፣ አልፎም በአያታቸው ኢትዮጵያ የሆኑ…ግማሽ ጎናቸው የመናዊ ትውልደ ሀበሻ 6.000.000/ ስድስት ሚሊዮን/ በላይ አሉ። ይህ የሚያሳየው የየመንና ኢትዮጵያ ትስስር የደም፣ ጥንት መሆኑን ነው። በፊት የመኒዎች በችግር ወደ ሀገራችን ይሰደዱ ነበር። ዛሬ ነገር ተገልብጦ እኛ ወደ እነሱ ሆኗል። አሁንም ቢሆን ግን ኢትዮጵያ ያለው የመናዊ ቁጥር በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ነው። ከዚህ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሳይሆን አይቀርም የመን ከአረቢኛው ቀጥሎ አማርኛ በሰፊው ይነገራል። አንድ ታክሲላይ ወጥተው ዘና ብለው ሰሚ የለም በማለት በአማርኛ ምስጢር ማውራት አይቻልም፡፡
<<ገንዘብ ካለ…>> ሁሉም የመናዊያን የሚያውቋት ተረት ናት። <<እወዲሻሎ..ኢንደሚኖ…አንቺ..>> በሁሉም ዘንድ የተለመደች ቃል ነች። ልክ እኛ ጋር ማዘር፣ ፋዘር..እንደተለመደ ሁሉ። ጫት ሲነሳ ሐረርን የማያነሳ የመናዊ የለም።
የዛሬዋ የመን ጥንት ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ <<ሀገረ ናግራን>> እንደምትባል ታሪክ ያስረዳል። እነሱ ግን ይህን መስማትም አይፈቅዱ በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ያለው <<ኤደን>> ደግሞ <<አደን>> ተብሎ መለወጡን አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዋና ከተማዋ ሰነዓ ጥንታዊነቷን ለማስረገጥ ከንግስት ሳባ የንግስና ዘመን ጋር ቁርኝት እንዳላት ይጠቀሳል። የመናዊያን ንግስት ሳባ ኢትዮጵያዊ ሳትሆን የመናዊ ነች ብለው ያምናሉ። ግብጾች የእኛ ናት እንደሚሉት ማለት ነው። ሳባ የመን ውስጥ ማሪብ የተባለ ቦታ ቤተ-መንግስት አላት። ምክምያታቸው ይህ ብቻ ነው። አባቷ ማነው? እንዴት ንግስት ሆነች ምላሽ የላቸውም። ምሁሮቻቸውም ሳባ ኢትዮጵያን አስተዳድራለች እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለችም ሲሉ ሽንጣቸውን ገትረው…ሽንጥ አላቸው እንዴ? አሀ!..አላቸው ግን ሽንጥ ይገተራል እንዴ? እንጃ!.. ብቻ ለአባባሉም ቢሆን እንበለውና ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ።
በአንድ ወቅት ፋጡማ ሁሬቢ… ከተባለች እንጋፋ የየመን ጋዜጠኛ ጋር የጦፈ ክርክር አድርገናል።
<<ለመሆኑ ኢትዮጵያ በውጭ ንጉስም ይሁን ንግስት የተዳደረችበት አጋጣሚ አለ ወይ? እንደዚህ አይነት ታሪክ አንብበሽስ ታውቂያለሽ? ካልሆነ ግን ድንገት አለም ያላወቀው ታሪክ ልናገኝ ነው ማለት ነው እና ማስረጃውን ስጭኝ?....>> አልኳት። <<እምቢኝ!...ያባ ቢላዋ ልጅ ለማን ተገዛንና የመንን የእኛ ንጉሶች ማስተዳደራቸውን እንጂ እኛ በየመናዊያን ስለመተዳደራችን ማን ተናገረና ያለ መረጃ ልቀበል? እምቢኝ……የአባት፣ አያቴን ታሪክ መድገም ቢያቅተኝ ጠብቄ እኖራለሁ …>> እያለ ውስጤ ፉከራ ይሁን ቀረርቶ ብጤ ፎካከረ። ከሌሎች ጋርም እንዲሁ ተከራክሬያለሁ። እነሱን ለመርታት ከመሞከር ይልቅ ድንጋይ መፍለጥ ይቀላልና በእንጥልጥል እተወዋለሁ።
ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ575 ዓ.ም ጀምሮ ንጉስ አብርሃ ለ50 ዓመታት ልጆቹ 20 አመት የመንን ባስተዳደሩበት ወቅት አሁን ያለንባት ሰነዓ ከተማ ለአቢሲኒያ ዋና ከተማ ሆና አገልግላለች የሚል አፈ ታሪክ አለ። በዛ ዘመን የተገነቡ ቤቶች ዛሬ ባብል የመን /የየመን በር/ በሚባለው ኦልድ ሰነዓ አካባቢ አሉ። የየመን ዋና የቱሪስት መስህብም ነው። በፎቶው ላይ የምታዩት ማለት ነው። ከአንድ ሺህ አመት በላይ ያስቆጠሩ 14000 ቤቶች አካባቢ አሉ። ሌላው ስለየመን አንስቶ ሳይወሳ የማይታለፍ የእርሻ ዘዴያቸው ነው። ለም አፈር የወርቅ ያህል ውድ ነው። ከመሬቱ ደረቃማነት የተነሳ የሚታዩትን አትክልቶች፣ የእህል አይነቶች ሲያዩ የመናዊያን ምን ያህል ጠንካራ እንደሆኑ ምስክሮች ናቸው። ለም የሆነውን አፈር ከሩቅ ቦታ ፈልገው ጭነው ያመጣሉ፣ ውሀ ከመሬት ለማውጣት እስከ 300 ሜትር ይቆፍራሉ።ያወጡትን ያጠጡታል፣ የፈለጉትን ይዘሩበታል። ያ- ደረቅ ድንጋያማ መሬት ህዝቡን አጥግቦ ያድራል።
ሌላም ስለየመን ሲነሳ ሳይወሳ የማይታለፍ አለ።
ጫት…….ጫት የህዝቡ መንቀሳቀሻ የደም ሴል ነው ማለት ይቻላል። ያለ ጫት ህይወት ያለ የማይመስላቸው ያገኙትን ሁሉ ለጫት የሚያውሉ ጥርሳቸው አልቆ ተፈጭቶላቸው በማንኪያ ሁሉ የሚወስዱ አሉ። በቀን ከ25000 ሺህ ሪያል በላይ /ከመቶ አስር ዶላር በላይ/ ለጫት ወጪ የሚያደርግ ቤተሰብ በብዛት እንዳለ በአንድ ወቅት የመን ታይምስ ለንባብ ያበቃ መሆኑን አስታውሳለሁ።
የመን ያለ ሀበሻ ባህሪውን፣ አብሮነቱን፣ መተሳሰቡን፣ ፍቅሩን፣ መተዛዘኑን፣ መደጋገፉን፣ መነቃቀፉን፣ ወሬ መውደዱን፣ ተንኮሉን፣ አብሮ መብላት መጠጣቱን፣ ሀሜቱን፣ በነገር መነቋቆሩን…ይዞ ነው የተሰደደው። ሀበሻ እርስ በእርሱ ፍቅር አለውም የለውምም የሚያሰኙ ብዙ እንከኖች አሉት። እዚህ ያለ ሀበሻ የወሬ ፍቅር አለው።
ወሬ ይወዳል።
የምን ወሬ ይወዳል ብቻ ነው? ወሬ በልቶ ወሬ ጠጥቶ፤ ወሬ ቀዶ ወሬ ሰፍቶ ነው የሚኖረው ያሰኛል። የመን ውስጥ ሀበሻ በገንዘብ እና ዕቃ ስርቆት አይደለም የሚታወቀው። ብዙም አይጠረጠርም። ስልክ ሰርቆ በመደወል ግን የሚያህለው የለም። ሱሱ ወሬ ነዋ!! ያማል ያሳማል።
ኧረ!..ብዙ ያስብላ፡፡
እመለስበታለሁ

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! – ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።
Read in PDF: EBAC Meglecha, Feb. 22, 2014 ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ…
Abraha Deboch and Moges Asgedom- Heroes or Egoistic Spy Agents? Post a rep
February 19 marks the massacre of the residents of Finfinne. It was happened 77 years ago on February 1937. The pretext for Italian fascist forces to massacre the resident of Finfinne was the attempt of Abraha Deboch and Moges Asgedom to kill Rodolfo Grazani.
Abraha Deboch and Moges Asgedom were both Eritrean origin and friends. Abraha was an employee of Italian forces in Ethiopia and he was Spy Agent in the Political Bureau of Italian Force in Ethiopia. His friend Moges has no formal and known employment.
On February 19,1937 there was a huge gathering organized by Italian Forces led by Rodolfo Graziani and held in Lidet Aderash found in the now Addis Ababa University Sadist Killo (Main) Campus. The purpose of the gathering was to celebrate the birth of Italian Royal Baby. Many Italians and Ethiopians were in attendance and others were waiting for handouts (alms) outside the hall. The disgruntled staff of Fascist Italian Political Bureau in Ethiopia Abraha Deboch and his accomplice Moges asgedom threw Italian made hand grenade in an attempt to kill Graziani and left Sidist killo using a tax driven by taxi driver named Simon Adefris.
In retaliation, Italian Fascist soldiers immediately opened fire on beggars and poor persons gathered around the hall for the distribution of alms and then extended their attack to other residents of Finfinne. The killing went on for three days and thousands of residents of the city killed. The question is what was the driving factor or motive of Abraha and Moges to take such not well taught action of hurling hand grenade to the persons gathered for a meeting in one room?
Kegnazmach Tesfa Gebreselassie Zebihere Bulga in his interview with Addis Zemen News Paper published on Sene 01, 1987 explained the motive of Abraha and Moges as follows. Abraha Deboch was an spy for Italians. Using his relation with Italians he took the properties of many Ethiopians for himself and helped the Italians to take the properties of many Ethiopians. He was behind the imprisonment and death of many Ethiopians. He was the servant of Fascist Italia forces. Both Abraha and Moges were not known among Ethiopians fighting against Fascist occupation both covertly and openly. The reason why Abraha and his friend and accomplice Moges decided to hurl hand grenade they got while working for Italian forces was their disagreement with Italian soldiers on the sharing of the properties taken from innocent Ethiopians.
After being the cause of the massacre of thousands of Ethiopians, both Abraha and Moges tried to escape the country to Sudan. However, they were not lucky enough to escape. Both were killed in Gojjam while on their way to flee the country. Some consider these former Italian Spy Agents heroes. This is the fact and you can judge for yourself. Read also this brief biography of Abraha and :Moges Asgedom

Saturday, February 22, 2014
ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ተባለ
ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን የድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።
አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።

በህዳር 24/2006 የሱዳኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አህመድ አልቀርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ይህንንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ለስራ ጉብኝት አቅንተዋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐሰን አልበሽር ሁለቱ አገራት በጥበቃ፣በደህንንነት፣ ህገወጥ የሰዉና የ አደንዛዥ እጽ ዝዉዉርን ለመግታት መስማማታቸዉን ገልጸዋል። በሱዳኗ ባሶንዳ የኢትዮጵያዉያን በጅምላ መገደል ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም ሱዳናን ኢትዮጵያ ግድያዉን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት እንዳላደረጉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ያስረዳሉ ።
በየካቲት 11/2006 ህወሃት የተመሰረተበትን 39ኛ አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ልዩ የክብር እንግዳ ሆነዉ መቐሌ ድረስ መምጣታቸዉ ታዉቋል። የሁለቱ አገራት መሪዎች ስለ ቀድሞ ስማእታት ቢናገሩም ወደ ሱዳን በኢኮኖሚ ሳቢያ ተሰደዉ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያዉያን ምንም ያሉት ነገር አልነበረም። በባሶንዳ ሱዳን ኢትዮጵያዉያን ነጥሎ የማጥቃቱ ዘመቻ እንደቀጠለ ነዉ! ኢትዮጵያዉያን ወገን ይድረስልን ሲሉም ይጣራሉ።
ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 14/2006 (ቢቢኤን )
የህክምና ተቋማትን አሠራር የሚወስን አዲስ መመሪያ ወጣ
- መሥፈርቱን የማያሟሉ ከሐምሌ 1 ጀምሮ እርምጃ ይወሰድባቸዋል
- በሥራ ላይ ካሉት ክሊኒኮች መስፈርቱን የሚያሟላ አይኖርም ተብሏል
- የግል ክሊኒኮች ማህበር በቂ የዝግጅት ጊዜ ሊሰጠን ይገባል አለ
የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት አገልግሎትለመስጠት የሚያስችላቸውን መስፈርቶችና ደረጃዎች የሚወስን አዲስ መመሪያ ወጣ፡፡ የጤና ተቋማቱ በአዲሱ መስፈርት መሰረት ራሳቸውን እንዲያደራጁ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጊዜ የተሰጣቸው ሲሆን ከሐምሌ 1 ጀምሮ መሥፈርቱን ባላሟሉት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ቁጥጥር ባለስልጣን ያወጣውና በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም የመንግስትና የግል የጤና ተቋማት ይመለከታል የተባለው አዲስ መመሪያ፤ ተቋማቱ ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ መመሪያ ላይ እንደተገለፀው፤ ሆስፒታሎች የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ አጠቃላይ ሆስፒታልና ስፔሻላይዝይድ ሆስፒታል ተብለው በ3 መደቦች የሚከፈሉ ሲሆን የጤና ማዕከላት፣ የጤና ጣቢያዎችና ልዩ ማዕከላትም በዘርፉ እንደሚጠቃለሉ ተጠቅሷል፡፡

መመሪያው ሆስፒታሎች እንደየደረጃቸው የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚገባቸው በዝርዘር የገለፀ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ቢያንስ 35 አልጋዎች፣ አጠቃላይ ሆስፒታሎች 50 አልጋዎች እንዲሁም ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ከ300 የማያንሱ አልጋዎች እንዲኖራቸው ያስገድዳል። ሁሉም የጤና ተቋማት የማዋለድ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው የገለፀው መመሪያው፤ በክሊኒኮች ውስጥ አልጋ በማዘጋጀት ህሙማንን በመደበኛነት አስተኝቶ ማከም እንደማይቻልና መካከለኛ ክሊኒኮች ለድንገተኛ ህመምና ለማዋለድ አገልግሎት የሚሆኑ 10 አልጋዎች ብቻ ሊኖራቸው እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡ ክሊኒኮችን በስም መሰየም እንደማይፈቀድም በዚሁ መመሪያ ላይ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የህክምና መሣሪያዎች ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የቁጥጥር አስተባባሪ ሲስተር የሺአለም በቀለ መመሪያውን ማውጣት ያስፈለገበትን ምክንያት ሲናገሩ፤ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በጤናው ዘርፍ ተሰማርተው ለህዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የጤና ተቋማትን ለመቆጣጠርና ተቋማቱ በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ባለመቻሉ፣ ይህንን ችግር በማስወገድ ተቋማቱ የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግና ህብረተሰቡን ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ለማስወገድ ነው ብለዋል። በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ህገወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር ለህብረተሰቡ ብቃት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እንደሆነም አክለው ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ የጤና ተቋማቱ የሚተዳደሩበትን መመሪያና መስፈርት ህግ አድርጎ ከማፅደቁ በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጉን የጠቆሙት ሲስተር የሺዓለም፤ በመመሪያው ላይ የተካተቱና ለአሰራር እንቅፋት ይሆናሉ የሚባሉ ጉዳዮች ካሉ ማሻሻያዎችን ለማድረግ እንደሚቻል በተደጋጋሚ መገለፁን አስታውሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ መመሪያው ሊያሰራን አይችልም የሚል ሃሳብ ከየትኛውም ወገን ባለመነሳቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ድርጅቶቻቸውን በመመሪያው መሰረት እንዲያደራጁ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ጊዜ እንደተሰጣቸውና የጊዜ ገደቡ ሲጠናቀቅ ባለስልጣን መ/ቤቱ የራሱን እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ የግል ክሊኒኮች ባለቤቶችና አሰሪዎች ማህበር ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበበ ያለው በበኩላቸው፤ መመሪያው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበና በዘርፉ የተሰማሩ በርካታ ባለሙያዎችን ከስራ ውጪ የሚያደርግ በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል፡፡ ህብረተሰቡ ጥራት ያለው የህክምና አገልገሎት እንዲያገኝና ዘርፉም ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲል ታስቦ የወጣውን መመሪያ እንደማይቃወሙ ምክትል ሊቀመንበሩ ገልፀው፤ሆኖም በአገሪቱ የተሰማሩ የጤና ተቋማትን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበና ምንም የመፍትሔ ሃሳብ ያላቀረበ በመሆኑ ብዙዎችን ከስራ የሚያፈናቅል ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከ500 በላይ አባላት ያሉት ማህበሩ፤ አዲሱን ህግና መመሪያ ተከትሎ በመስፈርቱ መሰረት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት ይቻላል ብለው እንደማያስቡ ገልፀው መንግስት በቂ የዝግጅት ጊዜና የጤና ተቋም መገንቢያ ቦታ ሊሰጠንና የብድር አገልግሎት ሊያመቻችልን ይገባልም ብለዋል፡፡ “እንደዚያ ካልሆነ የምንሰራው ከግለሰቦች በተከራየናቸው ክሊኒኮች በመሆኑ መስፈርቱ የሚጠይቀውን ለማሟላት ስንል ማፍረስም ሆነ መቀየር አንችልም” ሲሉ ችግራቸውን ጠቁመዋል፡፡ መስፈርቱን ካላሟላችሁ መስራት አትችሉም ከተባለ ግን በርካታ ባለሙያዎች ከስራ እንደሚፈናቀሉና ህብረተሰቡም በቂ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚቸገር መታወቅ ይገባዋል ብለዋል።
ሲስተር የሺዓለም በቀለ በበኩላቸው፤“በአገሪቱ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው አገልግሎት ከሚሰጡ የጤና ተቋማት መካከል አዲሱን መስፈርት በበቂ ሁኔታ የሚያሟሉ ተቋማት ስለመኖራቸው አፍን ሞልቶ መናገር አይቻልም” ይላሉ፡፡

Source/www.addisadmas.com
አንጋፋ ታጋዮች ስለ ህወኃት ይናገራሉ “ታጋዮች የተሰውለት ዓላማ ተረግጧል
“ታጋዮች የተሰውለት ዓላማ ተረግጧል”
ህወኀት የተመሰረተበት 39ኛ ዓመት በዓል ባለፈው ማክሰኞ በመቀሌ ከተማ በደማቅ ስነ-ስርአት አክብሯል፡፡ በዚህ በአል ላይ በትግሉ ወቅት የተሰው ቀደምት ታጋዮች የታወሱ ሲሆን የህወኀት ታሪክም በተለያዩ የፓርቲው አባላት ተነግሯል፡፡ ከህወኅት ምስረታ ጀምሮ በትግሉ ውስጥ የቆዩና በተለያዩ ጊዜያት ከፓርቲው የተለዩ አንጋፋ ታጋዮች ግን ህወኃት አላማውን ስቷል ሲሉ ይተቻሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኞች አበባየሁ ገበያው እና አለማየሁ አንበሴ ከእነዚህ አንጋፋ ታጋዮች መካከል አቶ ገብሩ አስራት እና አቶ አሰግደ ገ/ሥላሴን በህወኀት የትግል ዓላማ ዙርያ አነጋግረዋቸዋል፡፡

አቶ ገብሩ አስራት (የህወኀት አንጋፋ ታጋይ እና የአረና ፓርቲ መስራች)
መነሻው ላይ የህወኀት አላማ ምን ነበር?
በሃገሪቱ ላይ የሰፈነውን ጭቆና ማስወገድ ነበር፡፡ በወቅቱ የነበረው ስርዓት የግለሰብና የቡድን መብትን የማያከብር በመሆኑ የሃይማኖት መብትን ጨምሮ እነዚህን ሰብአዊ መብቶች ማረጋገጥ ነበር ዓላማው። መብቱ ብሄሮች እስከ መገንጠል የሚያደርሳቸው ጥያቄ ካለም መገንጠል ይችላሉ የሚል ሆኖ፣ ወሳኙ ግን ነፃነት የሚለው ነበር፡፡ የትግሉ ርዕዮተ ዓለም ማርክሲዝም ቢሆንም ማጠንጠኛው ነፃነትና የሰው ልጆች መብቶችን ማረጋገጥ ነበር፡፡
ትግሉ የትግራይ ሪፐብሊክን የመመስረት አላማ እንደነበረው ይነገራል፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የህወሃት ታጋዮች ግን ይሄ ዓላማ አልነበረም ይላሉ። እውነቱ የትኛው ነው?
ህወኀት ለአንድ ዓመት ያህል የተፃፈ አላማና ፕሮግራም አልነበረውም፡፡ በኋላ ግን አንድ ማኒፌስቶ ተዘጋጀ፡፡ በዚህ ማኒፌስቶ የትግራይ ሪፐብሊክን የማቋቋም አላማ ተቀምጦ ነበር፤ ነገር ግን በጉባኤ አልፀደቀም፡፡ በወቅቱ የነበሩ አመራሮች አፅፈው ያሰራጩት ሲሆን በታጋዮች ዘንድ ግን ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ተቃውሞ ስላጋጠመውም ለስድስት ወር ብቻ ነው በስራ ላይ የዋለው፡፡ “ይሄ ትክክል አይደለም፤ ከኢትዮጵያ መገንጠል እንደመብት እንጂ እንደ አላማ መቀመጥ የለበትም” የሚል ተቃውሞ ከቀረበበት በኋላ የሪፐብሊክ ምስረታ አላማ ውድቅ ተደረገ፡፡
እርስዎ ለየካቲት 11 የሚሰጡት ትርጉም ምንድነው? አላማውንስ አሳክቷል?
ትልቁ ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ በዘንድሮው አከባበር ላይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሳይቀሩ ስለጠላቶች ነው የሚያወሩት፡፡ የትኞቹ ጠላቶች እንደሆኑ አልገባኝም፡፡ አካሄዳቸውን የሚቃወመውን፣ መብቴ ተነክቷል ወይም ሙስና ተንሰራፍቷል እያለ የመልካም አስተዳደር ችግሩን የሚተቸውን ሁሉ በጠላትነት እየፈረጁት ነው ማለት ነው? ይሄ የየካቲት 11 አላማ አይደለም፤ መስተካከል አለበት። አሁን ያሉት አመራሮች ከስልጣናቸው በላይ የሚያሳስባቸው ምንም ነገር የለም፡፡ ሃሳባቸው እሱ ብቻ ነው፡፡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ህይወታቸውን የገበሩለት ዓላማ አሁን በቦታው አለ ብዬ አላምንም፡፡
የህወኀት ትግል ያመጣው ውጤት እንዴት ይገመገማል?
ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ውስጥ ህወኀት ብቻ ሳይሆን በርካቶች ታግለዋል፡፡ ኢህአፓ አለ፤ ሌሎችም እንደዚያው፡፡ ስለዚህ ህወኀት ብቻ ውጤታማ ነበር ማለት አይቻልም፡፡ ማንኛውም ፍትህና እኩልነትን አመጣለሁ ብሎ መስዋዕትነት የከፈለ ሁሉ የራሱ ቦታ አለው ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ረገድ ደርግን መጣሉ አስፈላጊ ነበር፤ ነገር ግን ሰዎች የተሰውለት አላማ ተረግጧል፡፡ በተለይ በትግራይ የተቃውሞ ፖለቲካ ነውር ሆኗል፡፡ መውጫና መግቢያ ታጥቷል፡፡ ስብሰባ ማካሄድ አልተቻለም። የካቲት 11 ደግሞ ስልጣን ላይ ለመቆየት ህዝቡን ማስፈራሪያ ነው የሆነው፡፡ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ብቻ እየዋለ ነው፡፡ በሰማዕታትና በተሰውት ታጋዮች ስም እየተነገደ ነው፡፡
የህወኀት የትግል ታሪክ በትክክል ለትውልድ የሚተላለፍበት መንገድ ተመቻችቷል ይላሉ?
በእርግጥ ብዙ የታሪክ መዛግብቶች አሉ። በትግሉ የነበሩና ዛሬ ወደ ጎን የተገፉ ወገኖችም ይህን ታሪክ የማረቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ አሁን ታሪክ እየተቀለበሠ ነው፡፡ እንደውም ታሪኩ እየተነገረ ያለው ትግሉን በማያውቁ፣ ታሪኩን ባልተረዱ ግለሰቦች ነው፡፡ ሺዎች የተሰዉለትን መራር ትግል ተረት እያደረጉት ነው፡፡ እንደተረት ውሸት እየቀላቀሉ እያወሩት ነው፡፡ በአሁን ጊዜ ይህን መሰል የታሪክ ቅልበሳ እየፈፀመ ያለው ጉልበት እና ገንዘብ ያለው ገዥው ፓርቲ ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የዚህ ታሪክ ብቸኛ ባለቤት እያደረገ ነው፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ ታጋዮች በትግሉ ወቅት ያበረከቱት አስተዋፅኦ እንኳ አይነገርም፡፡ ጭራሽ ሺዎች የተሰዉበት ታሪክ ወደ አንድ ሰው እየተጠቃለለ ነው፡፡ መለስ እና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት እኩል እንኳ እየታዩ አይደለም፡፡ ይሄ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል፡፡
ከ1983 በኋላስ ህወኀትን እንዴት ይገመግሙታል?
ይሄ በአጭሩ መገለፅ የሚችል አይደለም፤ የራሱ ትንታኔ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡
ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ በህወኀት ላይ የታዩ ለውጦች አሉ?
አይ የለም! ዋናው ጥንስሱ ያለው የፓርቲው ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ነው፡፡ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚለው ነገር ዜጎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ማህበረሰቦችን ሁሉ ይፈርጃቸዋል፡፡ እሱን የሚያገለግሉትን ወዳጅ ሲላቸው፣ በተቃራኒው የተሰለፉትን ጠላት ሲል ይፈርጃቸዋል፡፡ ስለዚህ መሰረታዊ ችግሩ ርዕዮተ ዓለሙ ላይ ነው፡፡ በዚህ ርዕዮተ ዓለም የተዋቀረ መንግሥት ፀረ-ዲሞክራሲ ነው የሚሆነው፡፡ መጀመሪያ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ ፕሬሶች ነፃነት ተሰጥቷቸው ተቋቁመው ነበር፤ ከጊዜ በኋላ ግን ይሄን መፍቀዱ ለስልጣናቸው አስጊ ሆኖ ስላገኙት ይበልጥ አምባገነንና ጨቋኝ ስርአት መገንባትን አማራጭ አድርገዋል፡፡ “ቀይ መስመር”፣ “ፈንጂ ወረዳ” በሚል እነዚህ መብቶች ተሸራርፈው ቀዳሚው ትኩረት ስልጣንን ማስጠበቅ ሆኗል፡፡
የዘውድ ስርአቱ ካከተመ 40 ዓመት ተቆጥሯል። በእነዚህ ጊዜያት በተደረጉት የተለያዩ ትግሎች የተገኙት አንኳር ለውጦች ምንድን ናቸው?
የ1966 አብዮት ያመጣቸው መሰረታዊ ለውጦች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ማህበረሰባዊ ለውጦች ተካሂደዋል፡፡ የፊውዳል ስርአት ተሰብሯል፡፡ የመሬት ስሪቱ አዲስ አቅጣጫ እንዲይዝ ተደርጓል፤ አዲስ ማህበራዊ ኃይል ተፈጥሯል፡፡ ገበሬዎች አዲስ ማህበራዊ ኃይል ነበሩ፤ ነገር ግን በደርግ ታንቀዋል። ይሄ ባይሆን ኖሮ በደርግ የ17 ዓመት የስልጣን ዘመን ብዙ ለውጥ ይመጣ ነበር ብዬ አምናለሁ። ኢህአዴግ ከመጣ በኋላ በኢኮኖሚ ፖሊሲው ትንሽ የተሻለ ነገር ታይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከጥቅም አንፃር ስለሚያየው እንደገና ኢኮኖሚውን ሁሉ የመቆጣጠር ፍላጎት እያሳየ ነው፡፡ በእርግጥ አንዳንድ የኢኮኖሚ ለውጦች መኖራቸው የማይካድ ነው፤ ይሁን እንጂ ለውጡ በጠንካራ ፖሊሲዎች የተደገፈ አይደለም። ፓርቲው ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር አባዜ ስለተጠናወተው በእድገቱ ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ እያሳረፈ ነው፡፡
አሁን ስላለው የፖለቲካ ትግል የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ቻርተር፣ በአለማቀፍ ደረጃ ዜጎች መብታቸውን ለማስከበር ማንኛውንም አይነት መንገድ መጠቀም እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ ጨቋኝ ስርአትን መታገል ተገቢ ነው፡፡ እኛ በደርግ ጭቆና ጊዜ የነበረን አማራጭ ትጥቅ ስለነበረ በዚያ መንገድ ሄደናል። አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ስንመለከተው ግን ይሄ አካሄድ ወይም በጠመንጃ የመጣ ስልጣን ዲሞክራሲን ያሰፍናል ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ፡፡ መንግስት መቀየር ይችላል ነገር ግን ዲሞክራሲያዊ ስርአትን ማምጣት የተለየ ነገር ይፈልጋል፡፡ ጠመንጃ ያነሳ ወገን፣ መብት ሁሉ ለሱ ብቻ እንደሚገባ ነው የሚያስበው፡፡ እኛ ከሌላው ይበልጥ ሞተንለታል የሚል ትምክህት ውስጥ ነው የሚከተው፡፡ አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የትጥቅ ትግልን የሚፈቅድ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ የሰላማዊ ትግሉ መቀጠል አለበት፡፡ ድሮ “የፖለቲካ ስልጣን ከጠመንጃ አፈ ሙዝ ይመነጫል” ነበር የሚባለው፤ አሁን ግን የተገላቢጦሽ መሆን አለበት፡፡ የጠመንጃ አፈሙዝ በፖለቲካ ተገዢ መሆን ነው ያለበት፡፡

addisadmas
የትግራይ ህዝብ የኤፈርት ባለቤትነቱ ባስቸኩዋይ ይረጋገጥ፡፡
የትግራይ ህዝብ የኤፈርት ባለቤትነቱ ባስቸኩዋይ ይረጋገጥ፡፡
ሕወሓት ኤፈርት በባዶው የህዝብ ነው ትለናለች፡፡ በተግባር ግን ለትግራይ ህዝብ ያደረገችለት አንዳችም ነገር የለም፡፡አሁንም ጥያቄያችን ይመለስ፤ ኤፈርት የማን ነው እውነት የትግራይ ህዝብ ከሆነ በተግባር በሚታይ ሁኔታ አሳዪን፡፡
ኤፈርት ለትግራይ ህዝብ የጤና ችግር መፍትሔ ካልሆነ፤
ኤፈርት ለትግራይ ህዝብ የዉሃ ችግር መፍትሔ ካልሆነ፤
ኤፈርት ለትግራይ ህዝብ የትምህርት ጥራት ችግር መፍትሔ ካልሆነ፤
ኤፈርት ለትግራይ ወጣቶች የስራ አጥነት ችግር መፍትሔ ካልሆነ፤
.........................................የኤፈርት ሕዝባዊነት ከምኑ ላይ ነው፡፡የትግራይ ህዝብ ከችግሬ ያወጡኛል በሚል ተስፋ ጥሎባቸው የነበሩትን ተቁዋማት ከችግሩ ሊያወጡት ይቅርና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኩዋን አያቅም፡፡ እነዚህ ተቁዋማት የችግራችን መፍትሔ እንጂ በተቃራኒው የጎን ዉጋት ሊሆኑብን አይገባም፡፡
እናም እላለው፡- የትግራይ ህዝብ የኤፈርት ባለቤትነቱ ባስቸኩዋይ ይረጋገጥ፡፡

የብአዴኑ አቶ አለምነው ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ ለፍርድ መቅረብ አለበት
ብስራት ወልደሚካኤል
የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን በግልፅ እመራዋለሁ የሚለውን ህዝብ በመሳደቡ ያለምንም ማንገራገርና ማምታታት ይቅርታ ጠይቆ እራሱን ለፍርድ ማቅረብ አለበት፣ ማስተዋሉ ካለው፡፡ በርግጥ የኢህአዴግ መሪዎች የህዝብና የሀገር ክብር እንደሌላቸው ግልፅ ነው፡፡ ያው በትዕቢትና በጠመንጃ እንጂ አንዳቸውም ህዝባዊ ፈቃድና ይሁንታ አግኝተው እንደማይመሩ እራሳቸውም ያውቁታል፡፡
ነገር ግን እንደ አቶ አለምነው መኮንን በቆሸሸ አስተሳሰብ ህዝብን ያህል ነገር ባለጌ ስድብ የሚሳደብ አይደለም ህዝብን ቤተሰቡን የመምራት ብቃት አለው ብሎ ማመን ይቸግራል፤ ይበልጥ ለቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ አዘንኩላቸው፡፡
ብአዴን/ኢህአዴግም ቢሆን ምንም እንኳ ለህዝብ ክብር ኖሮት ባያውቅም አቶ አለምነው መኮንንን በአደባባይ ፍርድ በማቅረብና ከስራ በማሰናበት ተገቢውን ፍርድ ሰጥቶ ተፈፃሚ ማድረግ አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ አቶ አለምነውን እከላከላለሁ ብሎ የሚል ከሆነ እራሱ ብአዴን ህዝብን የመምራት ሞራል እንደሌለው አምኖ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከዚህ በኋላ ህዝብን የመምራት፣ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ፣….የሞራል ብቃቱ የለውም፡፡ ሰውዬው የሰደበው የአማራውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገራችንን ህዝብ ነውና፡፡ ህዝብን የሚንቅና የሚሳደብ በህገመንግስቱም ቢሆን ቅጣቱ ከባድ ነው፣ ህግ የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓት ባይኖረንም፡፡
ስለዚህ የእሁዱ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከህግም ሆነ ከማህበራዊ እሴት አንፃር ተገቢም ትክክልም ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉ የአካባቢው ሰው በሰልፉ ላይ በመታደም እንዲህ ዓይነት ትዕቢተኛ መሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ የሞራል የበላይነት በመሆኑ አስተባባሪዎቹን ቀጥሉበት ቢባል የሚበዛ አይሆንም፡፡
ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ግን በባህርዳር ከተማ ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ምክንያቱም አቶ አለምነው መኮንን ላይ ገዥው ስርዓት እራሱ በግልፅ የእርምት እርምጃም ሆነ የይቅርታ ማስተባበያ ባለመስጠቱ ሁሉም ገዥውች ተመሳሳይ ንቀትና ትዕቢት እንዳላቸው የሚያመላክት ነውና፡፡ ህዝብን የናቀና የሚሳደብ ሰው ለሰከንድም ቢሆን ሊመራ አይገባም፣የሞራል ብቃቱም የለውም፡፡
የብአዴንን አመራር ለመቃወም ቅስቀሳው ጫማ በማውለቅ በባዶ እግር ታጅቦ ቀጥሏል ፤ፖሊስ ቅስቀሳውን ሊያስቆም ቢሞክር...
አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፈሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
የአዲስአበባ አስተዳደር ጋዜጠኞች ለአባይ ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀሩ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ለአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ በድጋሚ እንዲያዋጡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
የአስተዳደሩ ሹማምንትና ካድሬዎች ከሁለት ዓመት በፊት ሠራተኛውን ካወያዩ በኃላ በራሳቸው ውሳኔ ሠራተኛው የአንድ ወር ደመወዙን በአንድ ዓመት ከፍሎ ለማጠናቀቅ እንደፈቀደ አድርገው በመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ሰፊውን ሠራተኛ በማስቆጣቱ ወዲያውኑ ስብሰባ እንዲጠራለት በመጠየቅ ተቃውሞውን ገልጾአል፡፡ በዚህ ተቃውሞ መሰረት በአንድ ዓመት ይቆረጣል የተባለው የአንድ ወር ደመወዝ መዋጮ ወደሁለት ዓመት ሊሸጋገር ችሎአል፡፡
ሰራተኛው በሁለት ዓመት የከፈለው የአንድ ወር ደመወዝ መዋጮ በሀምሌ ወር 2005 ዓ.ም ከተጠናቀቀ በሃላ እንደገና መዋጮው እንዲቀጥል የአስተዳደሩ ካድሬዎች በተደጋጋሚ ሰራተኛውን ለማግባባት ሙከራ ያደረጉ ቢሆኑም አብዛኛው ሰራተኞች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ሊሳካ አለመቻሉ ምንጫችን ጠቁሞአል፡፡
አንድ የመገናኛ ብዙሃን ባልደረባ ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን እንደተናገረው ሠራተኛው ወርሃዊ ገቢው ከእጅ ወደአፍ መሆኑን፣ አዳዲስ ምሩቃኖች ደግሞ ዩኒቨርሲቲ የተማሩበትን ዋጋ ክፍያ ለመክፈል የሚቆረጥባቸው በመሆኑ ምክንያት መዋጮውን ለማዋጣት አቅም እንዳጠራቸው ገልጸው ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ ነገር ግን ካድሬዎቹ ከሌሎች ቢሮዎች እንዴት እንለያለን በሚል በተደጋጋሚ ስብሰባ በመጥራት ለማግባባትና ለማስፈራራት የሞከሩ ቢሆንም በሰራተኛው አቋም ምክንያት ሊሳካላቸው ሳይችል ቀርቶአል፡፡
በመጨረሻም ሰራተኛው በራሱ ፈቃደኝነት መስጠት የሚፈልገውን መቶኛ ያሳውቅ በሚል አንድ ቅጽ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል፡፡
ይህ ቅጽ እያንዳንዱ ሰራተኛ የሚያዋጣውን መቶኛ በመጻፍ በፊርማው አረጋግጦ እንዲመልስ የተደረገ
ሲሆን በዚህ ሒደት ሰራተኛውን በመከፋፈል ብዙዎቹ እንዲያዋጡ ለማድረግ ይቻላል በሚል ስሌት የተገባበት እንደነበር ታውቋል፡፡ ቅጹን አንዳንድ የፈሩ ሰራተኞች ከአንድ ወር ደመወዛቸው 30 በመቶና ከዚያ በታች የሆነ መጠን በሁለት ዓመት እንዲቆረጥባቸው ተስማምተው የሞሉ ሲሆን ብዙዎቹ አሁንም ቅጹን ለመሙላት ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው በተለይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን እንዳስደነገጠ ታውቋል፡፡ የመስተዳድሩን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
Thursday, February 20, 2014
የኢትዮጵያ መንግሥት፡- በኮምፕዩተር ስለላ ተከሰሰ፤ እንዲህ ዓይነቱን ውንጀላ አስተባበለ
የኢትዮጵያ መንግሥት የተራቀቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን እየለቀቀባቸው የኮምፕዩተሮቻቸውን ይዘት እንደሚሠርቅ እና የግል ግንኙነቶቻቸውንም እንደሚከታተል በውጭ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስሞታዎችን እያሰሙ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡
አንድ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነዋሪ በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ክሥ መመሥረታቸው፤ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ለእንግሊዝ ፖሊስ አቤቱታ ማስገባታቸው ታውቋል፡፡
ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ በሚገኝ አንድ ፌደራል ችሎት የተከፈተ ዶሴ ከዚህ የስለላ አድራጎት ጀርባ ያለችው ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠቁሞ ከሣሹ የአሥር ሺህ ዶላር የጉዳት ካሣ እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡
የኢንተርኔት ሰበራ፣ ዘረፋ፣ ስለላ፣ ሌብነት፣ ጥፋት
እንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ላይ በቀረበ ሌላ ክሥ እዚያ በስደት የሚኖሩትና የግንቦት ሰባት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን የተናገሩት ታደሰ ኬርስሞ ሰኞ ዕለት ባስገቡት ማመልከቻ ፊንፊሸር የሚባለውን ሶፍትዌር የሚቀምረው ዋና ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ውስጥ የሆነ ጋማ ግሩፕ እንዲመረመርላቸው ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከእንዲህ ዓይነቱ የኢንተርኔት ስለላ ጋር የሚያያይዙ ማስረጃዎች የተሰባሰቡትና የተደራጁት ካናዳ ውስጥ በሚገኝ ሲቲዘን ላብ በሚባል ድርጅት ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምፕዩተር ጠለፋ ወይም የስለላ ተግባር አያካሂድም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ተጨማሪና ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡ http://realaudio.rferl.org/voa/AMHA/2014/02/20/22b19b28-f438-4981-a5c6-0002c3d18133.mp3
የኢትዮጵያ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች መደፈር?
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የይስሙላ የፍትህ ስርዓት (ባሜርካኖች አባባል የካንጋሩ ወይም ባማርኛ የዝንጀሮ የፍርድ ስርዓት) መስርቷል እያልኩ ሁልጊዜ ስጮህ የቆየሁበትን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ማስረጃ የሚሆን ድርጊት በመፈጸሙ እያዘንኩም ቢሆን በመጠኑ ፈገግታ ሰጥቶኛል፡፡ የኢትዮጵያ “ፍርድ ” ቤቶች “በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ/Tigrian Peoples Liberation Front” የፖለቲካ ባላባቶችና ጌቶች የሚዘወሩ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ናቸው፣ በዚህም መሰረት ለዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እያልኩ ስናገር ቆያቻለሁ:: ባለፈው ሳምንት “ፍርድ ቤትን ዘልፈዋል ደፍረዋል” በሚል ሰበብ የአንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ የቀድሞው ዋና ጸሐፊ የነበሩትን አቶ አስራት ጣሴን ወደ ዘብጥያ ማውረድ በአገሪቱ ባሉ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች በተደጋጋሚ የሚፈጸሙትን የስህተት ኮሜዲዎች (የቀልድ ትእይንቶች) እና የፍትህ ስርዓቱን ሽባ መሆን በተጨባጭ የሚያመላክት ትኩስ ማስረጃ ነው፡፡
አቶ አስራት ጣሴ በስልጣን ላይ ተፈናጥጠው ለሚገኙት እውነትን በመናገራቸው፣ ወይም ደግሞ በግልጽ ለማስቀመጥ የውሸት የፍትህ ካባ ደርበው የፖለቲካ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የዜጎችን መብቶች ለሚደፍሩ ለሚደፈጥጡ እና ስልጣናቸውን አላግባብ ለሚጠቀሙ ባለስልጣኖች እውነትን ደፍረው በመናገራቸው “ወንጀል” ተደርጎ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ አቶ አስራት በየሳምንቱ በአማርኛ ቋንቋ እየተዘጋጀ በሚወጣው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ በህግ በተያዘ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት እየሰራ ያለው “ዘጋቢ ፊልም” የድርጅታቸውን ስም የሚያጠፋ እና የውደፊት ህልውና የሚጎዳ መሆኑን በማስመልከት ሀሳባቸውን በመግለጻቸው “ፍርድ ቤትን ዘልፈዋል ደፍረዋል ” የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ አቶ አስራት እንዲህ በማለት ነበር ሀሳባቸውን በጽሁፍ ያሰፈሩት፣ “በአሁኑ ጊዜ የአኬልዳማ ተውኔት በቴሌቪዥን በመታየት ላይ ይገኛል፡፡ ይህም እየተከናወነ ያለው የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) የህግ ሂደት ጉዳይ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ በሚገኘበት እና አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ከዘጋቢ ፊልሙ ጋር በተያያዘ መልኩ ኢሬቴድ የስም ማጥፋት በደል አድርሶብኛል በማለት ክስ መስርቶ ባለበት ጊዜ ነው፡፡ በኢሬቴድ ላይ በመሰረትነው ክስ ፍትህ እናገኛለን የሚል ግምት ስለሌለን ለታሪክ ሰነድ በማስረጃነት እንዲቀመጥ በሚል ነው፡፡“
እ.ኤ.አ በታህሳስ 2011 “ኢትዮጵያ፡ የደም መሬት ወይስ የሙስና መሬት?“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ “አኬልዳማ“ የሚል የውሸት ዘጋቢ ፊልም በመፈብረክ በቅርቡ ያረፉትን አቶ መለስ ዜናዊን መላዕክ አድርጎ ለማቅረብ እና መንግስታዊ አስተዳደራቸውን የሚቃወሙትን ተቃዋሚዎች ጥላሸት ለመቀባትና አፍ ለመድፈን የተተወነ እርባና ቢስ ዘጋቢ ፊልም መሆኑን ባቀረብኩት ትንታኒዬ ሀሳቤን አካፍዬ ነበር፡፡ መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነበር፡፡
‘አኬልዳማ‘ የሞራል ዝቅጠት የታጨቀበት በስሜታዊነት የተሞላ ዘጋቢ ተውኔት ድራማ ነው፡፡ በጨለማ ውሰጥ ተደብቀው እያደቡ በመቆየት ታጥቀው የተዘጋጁ እና በአደጋ ጊዜ ጦራቸውን ሰብቀው ጭራቃዊ አሸባሪዎችን ለመውጋት ብቅ የሚሉ በትልቅ የስልጣን ቦታ ላይ የተኮፈሱ ጀግና አሉት፣ አምባገነን መለስ ዜናዊ፡፡ በትልቅ የአደጋ ድባብ ስር የወደቀች ወይዘሪት ኢትዮጵያ የምትባል ወጣት አለች፡፡ የጭራቆች፣ የሸፍጠኞች፣ የበጥባጮች፣ መንግስትን በኃይል ገልባጮች፣ የውጭ ተባባሪዎች እና በእርግጥም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን፣ አመጸኞችን እና ትችት አቅራቢዎችን በሚረዱ አገሮች የሚደረጉ ሙሉ በሙሉ ሚስጥራዊ የሆኑ ሸፍጦች፣ በዲያስፖራ የተቃዋሚ አባላት የሚደረጉ መሰሪ ተግባራት፣ በአማጺዎች እና በአገር ውስጥ ከሃዲ ተባባሪዎች እና በእርግጥም ሽብርተኝነት የሚፈጸሙ ስሜታዊነት እና አስደንጋጭ ሁኔታዎች አሉ፡፡በመጨረሻ ደግነት በጭራቃዊነት ላይ ድልን መጎናጸፉ የማይቀር ተፈጥሯዊ ክስተት ነው፡፡ ጌታው አቶ መለስ ዜናዊ የአስደናቂ ሀሳብ አፍላቂነት ባለቤቱ፣ የፖለቲካ ልሂቁ፣ ቀስት በደጋን አነጣጥረው ተኳሹ፣ እና በጎራዴ ውጊያ የተለየ ስጦታ ባለቤቱ ከጭራቁ እና ጭራቃዊነት ስሜት ካለው ከአልቃይዳ፣ ከአልሻባብ እና ከእነርሱ አሽከሮች እና ሎሌዎች ማለትም ከኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ አመጸኞች እና ትችት አቅራቢዎች መዳፍ ስር ፈልቅቀው በማውጣት ወይዘሪት ኢትዮጵያን ይወልዳሉ፡፡ የሆሊዉድ መጥፎ አስፈሪው ሲኒማ አንክዎን an አንደ “አኬልዳማ” አያስጠይፍም፡፡
“የአኬልዳማ” ዘጋቢ ፊልም ተውኔት መታየትን ተከትሎ ገዥው አካል የእስላማዊ ጽንፈኞች እና አሸባሪዎች በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት በማሰብ ቅዱስ ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ገልጾ ይህንኑ ለማጋለጥ በሚል ሰበብ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2013 “ጅሀዳዊ ሃራካት” (“የቅዱስ ጦርነት ንቅናቄ”) በሚል ርዕስ በቴሌቪዥን ለአየር አብቅቷል፡፡ ያንን እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም “የፍርሃት እና ጥላሸት የመቀባት ፖለቲካ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ሀተታ አቅርቤ ነበር፣
‘ጅሃዳዊ ሃራካት’ በቅርጽ እና በይዘት ‘ከአኬልዳማ’ ተውኔት ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው፡፡ ዋናው ልዩነታቸው ‘ጅሃዳዊ ሃራካት’ የሙስሊሙን ማህበረሰብ በማሰቃየት እና በማዋረድ ዒላማ ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲጠበቁ እና መንግስት በእምነት ጉዳያቸው ላይ ጣልቃ ከመግባት እንዲታቀብ ከመጠየቅ ያለፈ ነገር ያላነሱ መሆናቸው እየታወቀ ደም ከጠማቸው አሸባሪ ቡድኖች እንደ ቦኮሃራም (ናይጀሪያ)፣ አንሳር አል ዲን (ማሊ)፣ አል ቃይዳ፣ አል ሻባብ፣ ሃማስ… ጋር በማገናኘት የአገር ውስጥ ወኪሎች ናቸው በማለት ሞግቷል:: ዘጋቢ ፊልሙ ጥቂት አሸባሪዎች ከእስልምና እምነት በስተጀርባ በመሆን በኢትዮጵያ ላይ የሽብር አደጋ ይፈጽማሉ በማለት የይስሙላ ኃላፊነት ቢወስድም የሚለው አባባል ለዚህ “ዘጋቢ ፊልም” ይፋ መንግስታዊ የኃይማኖት አለመቻቻል እና ማሰቃየት በአፍሪካ ከስንት አንድ ጊዜ ብቻ ሊከሰት የሚችል ለመንግስት መጥፎ መገለጫ ሆኗል፡፡
አቶ አስራት “ስለአኬልዳማ” ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ወደ ዘብጥያ መወርወራቸው ገዥው አካል በእርሳቸው እና በአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ላይ እየፈጸመ ያለውን ሚስጥራዊ እና ታማኝነት የጎደለው አካሄድ ስለዚያ እርባየለሽ ዘጋቢ ፊልም በድፍረት “በፍርድ ቤት” በመሞገታቸው ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገዥው አካል ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ አቶ አስራት ጣሴን በቁጥጥር ስር በማዋል በጉዳዩ ላይ የተያዘውን የስም ማጥፋት ክስ አቅል በማሳጣት የህዝቡን አመለካከት አቅጣጫ ለማስቀየስ የታለመ ነው፡፡ አቶ አስራት በይስሙላው ፍርድ ቤት ፊት ቆመው እነርሱን ተጠያቂ ማድረጋቸው ገዥውን አካል የበለጠ እንዲበሳጭ ያደረገው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ ማንም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ወይም በኢፍትሀዊነት ላይ የሚነሳ አመጸኛ ከገዥው አካል ከይስሙላው ፍርድ ቤት ፍትህን አይጠብቅም፡፡ ይኸ ያፈጠጠና ያገጠጠ እውነታ በአቶ አስራት ለገዥው አካል የተገለጸ የመጀመሪያ ጊዜ ኩነት ነውን?
ገዥው አካል ፍርድ ቤቶችን ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማዋል ከህግ አግባብ ውጭ እና በማን አለብኝነት መልኩ ስልጣኑን በመጠቀም ላይ መሆኑን በማስመልከት ከብዙ ጊዜ ጀምሬ ስገልጽ እና መረጃ ሳሰባስብ ቆይቻለሁ፡፡ አ.ኤ.አ በ2007 “የዝንጀሮ የህግ ሂደት በይስሙላው ፍርድ ቤት” በሚል ርዕስ ገዥው አካል በኢፍትሀዊነት ላይ የሚነሱ አመጾችን ለመጨፍለቅ እና ትችቶችን ለማፈን ሲል ፍርድ ቤቶችን ከሰውነት በወረደ እና በተወሳሰበ መልኩ እየተጠቀመባቸው መሆኑን ጽፌ ነበር፡፡ ተቃዋሚዎች ምንም ዓይነት ስህተት ሳይሰሩ በገዥው አካል በቁጥጥር ስር ይውሉ ነበር፡፡ ስለህግ ሂደቱ ማንኛውም ነገር ሚስጥራዊ ነው…ስለክሶች፣ ስለፍርድ ቤት የችሎት ስነስርዓቶች እና ስለዳኞች፡፡ ምንም ዓይነት የህግ ዕውቀቱ የሌላቸው ዳኞች የማይታዩ አሻንጉሊት ጌቶቻቸው የሚያቀርቡላቸውን ኢፍትሃዊነት ድርጊት ለመፈጸም በችሎት ፊት ይሰየማሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ዳኞች በአዕምሯቸው አውጥተው አውርደው ፍትሃዊ ነው ብለው የሚያምኑበትን ብይን ለመስጠት ማሰብ ጊዜው ያለፈበት ውሳኔ ነው፡፡ የፍትህ መጨንገፍ በገሃድ እየተስተዋለ ነው፡፡ በወንጀለኛው የይስሙላ ፍርድ ቤት የተሰጠው የዘለፋ ብይን ያሰደነቀኝ ቢሆንም በአቶ አስራት ላይ በተሰጠው ኢፍትሃዊ ብይን አልደነቅም:: አንደዉም የኢትዮጵያ ብልህ ዳኞች በፌዝ የሚነገርላቸው የማይናገሩ ዱዳዎች የማይሰሙ ደንቆሮዎች የማያዩ አዉር ዝንጀሮችን ያስታዉሱኛል:: አቶ አስራት በባለ ሶስት ቀለበት የፍትህ ተውኔት ለቀረበባቸው የሸፍጥ “የዘለፋ” ክስ በአቋማቸው እንደጸኑ የተቃውሞ የክርክር ጭብጣቸውን በመያዛቸው ባርኔጣዬን በእጀ ከፍ አድርጌ በመያዝ ጎንበስ በማለት የተሰማኝን አድናቆት ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡
የህግ ዘለፋና ድፍረት በኢትዮጵያ የይስሙላው ፍርድ ቤት
በመጽሄት ላይ አስተያየት አዘል ጽሁፍ መጻፍ እና በአንድ በቴሌቪዥን ለአየር በበቃ ዘጋቢ ፊልም (ያውም ፍጹም እርባና የለሽ በሆነ ፊልም) ላይ የሰላ ትችትን ማቅረብ የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር ሊሆን ይችላልን? ገዥው አካል በፍርድ ሂደቱ ላይ እያካሄደ ያለውን ጣልቃገብነት እንዲያቆም ትችት ማቅረብ የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር ነውን? በጥብቅ ፖለቲካዊ ይዘት በተላበሰው የፍርድ ሂደት ውስጥ ተክክለኛ እና ፍትሃዊ ብይን የማግኘቱ ሁኔታ ጥርጣሬ እና አሳሳቢነት ላይ ተመርኩዞ ሀሳብን መግለጽ የፍርደ ቤት ዘለፋ መድፈር ሊባል ይገባልን? አንድ ሰው በፖለቲካ እና በህግ ጉዳይ ላይ ያለውን አስተያየት በማቅረቡ ምክንያት የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር ሊሆን ይችላልን? አንድ ሰው ህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም ነጻ ሀሳቡን በመግለጹ ምክንያት የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር ተብሎ ዘብጥያ ያስወርዳልን? አንድ ሰው ስለ የህግ ልዕልና እና የፍትህ እጦት አሳስቦት ቅሬታውን በማሰማቱ ምክንያት የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር በማለት ለእስር የሚያበቃ ሊሆን ይገባልን? አካፋን አካፋ ማለት የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር ተብሎ በእስር የሚያማቅቅ ሊሆን ይገባልን? እውነትን እና እውነትን ብቻ መናገር የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር ተብሎ ዘብጥያ ሊያስወርድ ይገባልን?
በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፌዴራል እና የክልላዊ ግዛት ፍርድ ቤቶች “የፍርድ ቤት ኃላፊ” ሆኘ የምሰራ ከመሆኔ አንጻር ዘለፋን አስመልክቶ በፍርድ ቤቶች መርሆዎች ላይ ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ የህግ ሂደቶች ብቸኛ እና በሚገባ ታስቦባቸው የሚከናወኑ ስርዓቶች ስለሆኑ ማንኛቸውም በዚህ ሂደት ውስጥ በመግባት የሚሳተፉ ሰዎች ሁሉ ከልብ ሊያከብሯቸው ይገባል፡፡ ፍርድ ቤቱ የህግ ሂደቱን እያከናወነ ባለበት ጊዜ ሁሉ ሙሉ ክብሩ ሁልጊዜ ሊከበርለት ይገባል፡፡ በህግ ሂደቱ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገታዊ የግንፍልተኝነት ስሜቶች፣ እና ሌሎች የፍትህ ሂደቱን ሊያውኩ የሚችሉ ነገሮች እንዲሁም የፍርድ ቤቱን ክብር ሊያጎድፉ የሚችሉ ባህሪዎች ሲንጸባረቁ እና ከፍርድ ቤቱ ውጭም ቢሆን ተገቢ የሆነውን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ የሚጻረሩ ነገሮች በተፈጸሙ ጊዜ የህግ ዘለፋ ተብለው በህግ አግባብበ ብቻ መስተናገድ እንዳለባቸው በህግ ማዕቀፉ በሚገባ ተደራጅተው ተቀምጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ጊዜን ያስቆጠረ ቢሆንም ምንም ዓይነት ለውጥ ወይም መሻሻል ሳያደርግ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ፍርድ ቤትን መዘለፍ መድፈር በሚል የተጣሉት ቅጣቶች “የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ስንሰራት” በሚል በንጉሱ ዘመን (በአዋጅ ቁጥር 185 በ1996 የተሸሻለው) በአንቀጽ 443 ስር ገና ቀድሞውኑ የተካተቱ ህጎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ የዚህ ህግ የመጀመሪያው ቋንቋ በቀጣይነት “በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ” (አዋጅ ቁጥር 414/2004) በአንቀጽ 449 ቃል በቃል እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የፍርድ ቤት ሂደቱ እየተካሄደ ባለበት ጊዜ አንድ ሰው በፍርድ ቤቱ ላይ ዘለፋ መድፈር ቢያካሂድ ይህንን በማስመልከት አንቀጽ 449 ለፍርድ ቤቶች የሚከተለውን ስልጣን ይሰጣል፣“በፍርድሂደቱጊዜፍርድቤቱበመጠየቅላይእንዳለ፣ የፍርድ ሂደቱ በመካሄድ ላይ እንዳለ ወይም ደግሞ ፍርድ ቤቱ የክስ ጉዳዩን በመስማት ላይ እንዳለ፣ በማንኛውም መንገድ የስድብ ዘለፋ የሰነዘረ፣ የማፌዝ ድርጊት የፈጸመ፣ የማስፈራራት ድርጊት የፈጸመ እና የፍርድ ሂደቱ እየተካሄደ ባለበት ሁኔታ ላይ ፍርድቤቱወይምዳኛው ተግባራቸውንበመወጣትላይእንዳሉ ሁከት የፈጠረ …“ (የተሰመሩት አጽንኦ ለመስጠት የተደረጉ ናቸው)
የዘለፋ ቅጣቶች ተፈጻሚነት የሚኖራቸው አንድ ሰው “ፍርድ ቤቱ ቀርቦ በፍርድ ሂደት ሆኖ ጥያቄ በማቅረብ ላይ እንዳለ፣ በክስ ሂደቱ ላይ ወይም ክስ በመስማት ላይ እያለ” አንድ ሰው ስነምግባር በጎደለው መልክ ህጉን በሚጻረር ሁኔታ ከተንቀሳቀሰ/ች ብቻ ነው፡፡ በፍርድ ቤቱ የፍትህ ሂደቱ ከሚከናወንበት ቢሮ ውጭ ከሆነ ግልጽ የሆነ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን በመቃወም ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆን እምቢተኝነት ካልተንጸባረቀ በስተቀር ይኸ ቅጣት ተፈጸሚነት አይኖረውም፡፡ አቶ አስራት “ከህግ የፍትህ ሂደት ጥያቄ ወይም ከፍትህ ሂደቱ” ውጭ በጻፉት ማንኛውም ዓይነት ጽሁፍ የፍርድ ቤት ዘለፋ መድፈር በሚል ሰበብ ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በይበልጥም ደግሞ የእርሳቸው ትችት በምንም ዓይነት መልኩ በአንቀጽ 449 ስር በተደነገገው መሰረት “የፍርድ ቤት ዘለፋ” ተብሎ ሊፈረጅ አይችልም፣ ምክንያቱም አቶ አስራት “ፍርድ ቤቱ የፍርድ ሂደቱን እያከናወነ ባለበት ጊዜ አልተሳደቡም፣ አላፌዙም፣ አላስፈራሩም፣ ወይም ደግሞ በፍርድ ቤቱ ወይም በዳኛው ላይ ስራ ሊያደናቅፍ የሚያስችል ሁከት አልፈጠሩም…“ ጉዳዩን በተናጠል እና ከሁኔታዎች ጋር አስተሳስረን ስንመለከተው የአቶ አስራት ትችቶች ያነጣጠሩት በፍርድ ቤቱ ላይ አልነበረም፣ ሆኖም ግን በተጨባጭ ትችታቸው ያነጣጠረው በስርዓቱ ቁንጮዎች ላይ ሆኖ ገዥው አካል ከፍትህ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ መልኩ እያካሄደ ያለውን አጧዥነት፣ ጣልቃገብነት፣ እና በአጠቃላይ በፍትህ ስርዓቱ ላይ እያደረገ ያለውን ብልሹነት የተንሰራፋበት ስርዓት ለመሸንቆጥ ነበር፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ አቶ አስራት ከፍርድ ቤት የቢሮ ስነስርዓት ማዕቀፍ ውጭ ሆነው የፍትህ ስርዓቱ በፖለቲካው ጣልቃገብነት ተተብትቦ ያለ መሆኑን በአንድ መጽሄት ላይ የሚሰማቸውን ሀሳባቸውን ገለጹ እንጅ ሌላ የፈጸሙት ነገር የለም፡፡
አንዱ ከይስሙላ ፍርድ ቤቶች ጋር በተያያዘ መልኩ ሊጤን እና ግንዛቤ ሊያዝበት የሚገባው ጉዳይ በፖለቲካ እይታ መስፈርት ከማይገባቸው የስልጣን ወንበር ላይ በተቀመጡ “ዳኞች” አማካይነት በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚፈጸመው ከህግ አግባብ ውጭ እና ስልጣንን መከታ በማድረግ ለቡድናዊ የፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል ፍትህን የማጨናገፉ ሁኔታ ነው፡፡ በጥላቻ የተሞላ ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም አቶ አስራትን ዘብጥያ የጣለው “ፍርድ ቤት” አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ እና ገዥው አካል ከፖለቲካ እይታቸው አንጻር ገብተውበት ባለው ውዝግብ ላይ ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ለገዥው አካል ፖለቲካዊ ወገንተኝነት በማሳየት እራሱን ከፖለቲካ ጉዳይ ጋር አዛምዶ ተገኝቷል፡፡ በጨዋ አነጋገር ሆን ብሎ አስቦበት እና በተሰላ ስሌት መሰረት የህግ እና የስነ ምግባር ግዴታዎቹን ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል እና እራሱን ከፖለቲካ ውስጥ የዘፈቀ ፍርድ ቤት እራሱ ፍትህን የዘለፈ ፍርድ ቤት ነው፡፡
ህጋዊ የፍትህ ስልጣን ያለው አካል በቀማኛ ወንጀለኞች ሲጠለፍ ማየት በጣም የሚያስገርም ጉዳይ ነው፡፡ እስቲ አስቡት እብዶች የእብድ ሀኪም ቤቱን ሲያስተዳድሩት፣ እንዲሁም እስቲ አስቡት ወንጀለኞች ፍርድቤቱን በ ኃይል ጠልፈው እንዳሻቸው ሲዳክሩበት፡፡ በኢትዮጵያ የተዘረጋው “የፍትህ” ስርዓት የዘራፊዎች እና የወሮበሎች ዋነኛ መጠቀሚያ መሳሪያ መሆኑን ማንም ያውቃል፡፡ የአቶ አስራትን “ጉዳይ” የያዘው ፍርድ ቤት እውነትን ለማንሸራሸር ፍትህን ለመስጠት አቅም የሌለው ሽባ ነው፡፡ ይልቁንም ይህ ፍርድ ቤት የገዥውን አካል የተቃዋሚ ወገኖች ለማጥቂያነት እየዋለ ያለ የፖለቲካ መሳሪያ ነው፡፡
እስቲ ስለየይስሙላው ፍርድ ቤት “የፍትህ ዘለፋ ድፍረት” ጥቂት እንነጋገር
ስለፍትህ ዘለፋ እስቲ እንነጋገር፡፡ ለሁለት አስርት ዓመታት በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ እና አሁን በስልጣን ላያ ያሉት ተኪዎቻቸው ፍትህን በመዘለፍ በመድፈር ላይ ይገኛሉ፡፡ የፍትህ ስርዓቱን እና ፍርድ ቤቶችን ለፖለቲካ ዓላማቸው ማስፈጸሚያ እና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት እና ለመቅጣት ከህግ አግባብ ውጭ ስልጣናቸውን በመጠቀም ከህግ ውጭ በመንቀሳቀስ ሲጠቀሙባቸው ቆይተዋል፡፡ የአገር ክህደት እና አሸባሪነት በሚል የውሸት ክሶችን በመመስረት የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ለመወንጀያነት ፍርድ ቤቶችን ተጠቅመውባቸዋል፡፡ ከህግ አግባብ ውጭ በርካታ የአገሪቱን ዜጎች በእስር ቤቶች በማጎር በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዜጎች የንብረት ባለቤትነት ዋስትና እንዲያጡ የፍርድ ቤቶችን በመሳሪያነት ይጠቀማሉ፡፡ ከማንኛውም የህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ፍርድ ቤቶችን መደበቂያ ዋሻ አድርገው ይጠቀማሉ፡፡ የሀሰት የሙስና ክስ በመመስረት የዱሮ የመከላከያ ጓዳቸውን ለማግለል እና አቅም ለማሳጣት ፍርድ ቤቶችን ተጠቅመዋል፡፡
እ.ኤ.አ በጥር 2012 በማንኛውም የሰለጠነ የፍትህ ስርዓትን በሚያራምድ የፍትህ አካል ሊሳቅበት እና ሊወረወር በሚገባ የልጆች ጨዋታ “ማስረጃ“ በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ ላይ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ ርዕዮት ለመጽሄት የሚሆን ጽሁፍ በመጻፍ በድረ ገጽ ላይ እንዲታተም አድርጋለች፣ ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር የኢሜል ጽሁፍ ልውውጦች እና የስልክ ግንኙነት አድርጋለች በማለት የውንጀላ ክስ ተመስርቶባታል፡፡ ይህንን በማቀነባበር የ14 ዓመታት የእስር ቅጣት ሲፈረድባት የ33 ሺ ብር ቅጣትም ተጥሎባታል፡፡ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል፣ “[ርዕዮት እና ውብሸት] ጥፋተኛ ሊያሰኝ የሚችል ምንም ዓይነት የወንጀል ድርጊት ለመፈጸማቸው የሚያስረዳ መረጃ የለም፡፡ በመንግስት ላይ ህጋዊ መስመርን በመከተል ትችት በማቅረባቸው ለቅጣት ሰለባነት መዳረጋቸውን እና የህሊና እስረኞች መሆናቸውን ነው የምናምነው፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር መለቀቅ አለባቸው“ በማለት ነጻ ስለመሆናቸው ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ለእስር የተዳረጉት ጋዜጠኞች ነጻ መሆናቸውን ለመግለጽ እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቷል፣ “በቀረበው የክስ መዝገብ መሰረት በዋናነት በተደረጉ ውይይቶች በተለይም በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል መባሉ ከሽብር ተግባራት ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተከላካዮቹ የተከሰሱባቸው ዝርዝር የወንጀል ጉዳዮች በመጀመሪያው ዋናው የክስ መዘገብ ላይ የሚታዩ አይደሉም…“ የርዕዮት እና የውብሸት ውንጀላ ሂደትን መሰረት በማድረግ የተሰጡ ብይኖች የይስሙላውን ፍርድ ቤት የፍትህ ዘለፋ መድፈርያ ማሳያ ማስረጃዎች ናቸው!
አ.ኤ.አ በሰኔ 2012 እስክንድር ነጋ “ዕቅድ በመንድፍ፣ ዕቅዱን ለመፈጸም በመዘጋጀት፣ የዱለታ ስራ በማካሄድ፣ ሁከት ለመፍጠር በመዘጋጀት እና የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም“ በሚል ውንጀላ ተከስሶ 18 ዓመታት የእስር ቅጣት ተፈረደበት:: በእስክንድር ነጋ ላይ የቀረበው የውንጀላ ማስረጃ በትክክል ሊሰማ የማይችል የስልክ ምልልሶች ቅጅ እና ሌሎች አስተያየቶች እንዲሁም በአንድ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በአረብ አገሮች እና በኢትዮጵያ መካከል ያሉትን ልዩነቶች በማብራራት እስክንድር አወያይ ሆኖ ያቀረበውን እና በይፋ በቪዲዮ ተቀርጾ የነበረውን የቪዲዮ ቅጅ ማስረጃ አድርጎ በማቅረብ ነበር፡፡ እስክንድር ለነጻው ፕሬስ መከበር እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት እና ታላቅ ተጋድሎ ከግንዛቤ በማስገባት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ታላላቅ የዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅቶች ታላቅ ክብር ተችሮታል፡፡ እ.ኤ.አ በጃኗሪ 2014 ዓለም አቀፍ የጋዜጦች እና የዜና አሳታሚዎች ማህበር/World Association of Newspapers and News Publishers የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ታዋቂ የሆነውን የ2014 ዓለም አቀፍ ወርቃማ የነጻነት ብዕር/Golden Pen of Freedom ሸልሞታል፡፡ በድረ ገጽ መረብ ሀሳቦቹን የሚያካፍልን ጋዜጠኛ ለ18 ዓመታት እስር ዘብጥያ ማውረድ የይስሙላው ፍርድ ቤት እያደረገ ያለው የፍትህ ዘለፋ ድፍረት ነው፡፡
እ.ኤ.አ በኦክቶበር በ2011 ጆሀን ፔርሶን እና ማርቲን ሽብዬ የተባሉ የስዊድን ዜጎች ሆነው ለሌሎች ድርጅቶች የሚሰሩ ጋዜጠኞች በሙያቸው የምርመራ ስራ በመስራት ላይ እንዳሉ አቶ መለስ “በሽብርተኝነት” በመወንጀል ጥፋተኛ አድርገዋቸዋል፡፡ አቶ መለስ ጆሀን ፔርሶን እና ማርቲን ሽብዬን የሽብርተኛ ድርጅት አስፈጻሚዎች እና ተባባሪዎች ናቸው በሚል ፈርጀዋቸዋል፡፡ እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል፣ “ቢያንስ ቢያንስ የሽብርተኛ ድርጅት ተላላኪዎች ናቸው፡፡ ጋዜጠኞችም አይደሉም፡፡ ጋዜጠኛ ለምንድን ነው ከአሸባሪ ድርጅት ጋር የሚገናኘው እና በእነዚያ በታጠቁ አሸባሪዎች ከለላነት ወደ አገር ውስጥ የሚገባው እና ከአሸባሪዎች ጋር ተቀላቅሎ አብሮ የሚዋጋው? ጋዜጠኝነት ያ ከሆነ እኔ ሽብርተኝነት ምን እንደሆነ አላውቅም ማለት ነው፡፡“ በማለት ስላቅ ተናግረው ነበር፡፡
አቶ መለስ ጆሀን ፔርሶን እና ማርቲን ሽብዬ ጥፋተኛ መሆናቸውን በይፋ ከገለጹ በኋላ አጠቃላይ የፍትህ ሂደቱ ቀልድ መሆኑን በተግባር አሳዩ፡፡ የፍትህ ሂደቱ “የታዕይታ የፍትህ ሂደት” ሆነ፡፡ ዳኞቹ በአለቆቻቸው የተነገራቸውን ብቻ የሚፈጽሙ አሻንጉሊቶች ሆኑ፡፡ በአጭሩ አቶ መለስ ጆሀን ፔርሶን እና ማርቲን ሽብዬን የሚዳኘው ፍርድ ቤታቸው በህግ እና በህግ ብቻ የሚመራ ሳይሆን በገዥዎች ፈቃድ ብቻ እንደ ቅሪላ የሚነፋ እና የሚተነፍስ የይስሙላ ፍርድ ቤት መሆኑን ለዓለም ህዝብ በግልጽ አስመሰከሩ፡፡ አቶ መለስ ሁለቱን ጋዜጠኞች “የሽብርተኛ ድርጅት ተላላኪዎች ናቸው” በማለት አስረግጠው ካወጁ በኋላ በኢትዮጵያ ምን ዓይነት ዳኛ ነው (ከብርቱካን ሚደቅሳ በስተቀር) ከአቶ መለስ በተቃራኒ በመቆም “አቶ መለስ! የጋዜጠኞችን በህግ ፊት ነጻ የመሆን መብታቸውን በመንፈግ በፍርድ ቤቱ ላይ ዘለፋ ድፍረት እየፈጸሙ ነው! የተከሰሱትን ዜጎች ህገመንግሰታዊ መብት ዋጋ በማሳጣት በፍትህ ላይ ዘለፋ ድፍረት እያደረጉ ነው!“ በማለት ስብዕናውን የሚያስከብር እና የፍትህ ጀግንነቱን የሚያስመሰክረው?
እ.ኤ.ኤ በ2009 የአቶ መለስ ቁንጮ ሎሌዎች “ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመግደል እና የቴሌኮሙኒኬሽን እና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችነ ለማቋረጥ እና ለማውደም እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ሁከት እና ዕልቂት ለመፍጠር ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል” ያሏቸውን 40 የሚሆኑ “በድፍረት የተሞሉ ወንጀለኞች” ፈርጀው አቀረቡ፡፡ “ሁሉም” የፍርድ ሂደታቸው ታዬ እናም “ተወነጀሉ”: የረዥም ጊዜ እስራት ተበየነባቸው፡፡ ለአቶ መለስ የፍርድ ሂደት ማለት የሰርከስ ተውኔት አዘጋጅቶ ከማሳየት ባልተናነሰ መልኩ እንደዚያ የቀለለ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ምናልባትም የምዕራቡ ዓለም ለጋሾች ድርጊቱን በተሻለ መልክ እያወቁ ከአቶ መለስ የሚያገኙት ጥቅም እስካልነጠፈ ድረስ ከአቶ መለስ ጋራ አብሮ መጓዝን በመምረጥ አይተው እንዳላዬ ሰምተው እንዳላሰሙ በመቁጠር ጆሮ ዳባ ብለዋል፡፡ ያም በይስሙላውፍርድ ቤት ላይ የቀረበ የፍትህ ዘለፋመድፈር ነው!
እ.ኤ.አ በዴሴምበር 2008 አቶ መለስ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ መሪ የሆነችውን ብርቱካን ሚደቅሳን በድንገት በቁጥጥር ስር በማዋል ቀደም ሲል ተቀብላ የነበረውን ይቅርታ ክዳለች በማለት የሸፍጥ ክስ በመመስረት በፈጣን ጊዜ ውስጥ ለእስር ቤት ዘብጥያ ወረወሯት፡፡ ለይስሙላም ቢሆን እንኳን ጉዳዩ በይስሙላው ፍርድ ቤት እንዲታይ ዕድል ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ አቶ መለስ ከመንገድ በማሳፈስ በቀጥታ ወደ እስር ቤት ለብቻዋ እንድትታሰር ከወረወሯት በኋላ ከጥቂት የእስር ጊዜ ቆይታ በኋላ እንዲህ የሚል ስላቅ አስተላልፈዋል፣ “ብርቱካንን ለመፍታት ከማንም ጋር የሚደረግ ድርድር አይኖርም፡፡ በፍጹም፡፡ አራት ነጥብ፡፡ ያ የሞተ ጉዳይ ነው፡፡“ አምባገነኑ አቶ መለስ የእርሳቸውን የሌብነት እና በጥባጭነት ባህሪ ሳትፈራ የተጋፈጠች ብቸኛ ሴት ላይ ባደረባቸው ከፍተኛ ንዴት ምክንያት በይስሙላው ፍርድ ቤት እንኳ ለይስሙላ ለማስመሰል ዕድል መስጠት ሽንፈት መስሎ ታያቸው፡፡ እ.ኤ.አ በዴሴምበር 2010 ይቅርታ እንድትጠይቅ ካስገደዱ በኋላ “ይቅርታ” አደረጉላት፡፡ አንድ የፖለቲካ ተቃዋሚን ከህግ አግባብ ውጭ ዘብጥያ በመወርወር የስሜታዊነት እናየጥላቻ ሃራራው ቀዝቀዝ ሲልለት ይቅርታእንዲጠይቁ ማስገድድ የፍትህ ዘለፋ መድፈር ነው!
እ.ኤ.አ በ2005 የአገሪቱን ታላላቅ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እና የበርካታ ጋዜጦች አዘጋጆችን ወደ ዘብጥያ ከወረወሩ በኋላ እንዲህ በማለት አወጁ፣ “ለእኛ እነዚህ በእርግጠኝነት ጋዜጠኞች አይደሉም፡፡ የፕሬስ ህጉን ተጻረዋል በሚል ክስ የሚመሰረትባቸው አይሆንም፡፡ ክስ የሚመሰረትባቸው እንደ ቅንጅት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ አመራሮች በአገር ክህደት ወንጀል የሚፈለጉት ናቸው… የቅንጅት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ አመራሮች በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት በአገር ክህደት ወንጀል መንግስትን በኃይል ለመገረሰስ በመንቀሳቀሳቸው ያስከስሳቸዋል፣ በህግ ፊት እንዲቆምም እናደርጋለን፡፡“ ብለው ነበር፡፡ አቶ መለስ አስቀድመው እንደተነበዩት በቅንጅት አመራሮች ላይ በይስሙላው ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው፣ ወንጀለኛ ተብለውም ብይን ተላለፈባቸው፡፡ ያ በይስሙላው ፍርድ ቤት የፍትህ ዘለፋ ድፍረትነው!
እውነታው ሲታይ ግን የኢትየጵያ “ፍርድ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የይስሙላ ፍርድ ቤት ትክክለኛ ማሳያዎች መሆናቸውን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲ ቡድኖች፣ በኢፍትሃዊነት ላይ በሚያምጹ አመጸኞች፣ እና በሌሎች ላይ ፍትህን እንዲሰጡ ዳኞች ተብለው የሚሰየሙት የፍትህ ካባን የደረቡ የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች እና ታማኝ ታዛዦች ና ሎሌዎች ናቸው፡፡ ይህ አባባል በተቃዋሚ ቡድን ወይም ግለሰብ ብቻ የተሰጠ ድምዳሜ አይደለም፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት እና ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌም ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ በ2007 ባወጣው ዘገባ እንዲህ የሚል ድምዳሜ ሰጥቶ ነበር፣ “ታላላቅ በሆኑ በህግ የተያዙ ጉዳይች ላይ ፍርድ ቤቶች በጣም የተመናመነ ነጻነትን ያሳያሉ፣ ወይም ደግሞ በህግ ከለላ ጥላ ስር ባሉ ተከሳሶች የህግ ስነስርዓት ሂደቶች ላይ የሳሳ የምንግዴለሽነት ባህሪያትን ያንጸባርቃሉ… የህግ ስርዓቱ በጣም ረዥም ቀጠሮዎችን ከሰጠ በኋላ ነው ጉዳዮችን የሚያየው፣ ይህም የሚሆነው አንዳንድ ጊዜ በፍርድ ቤቶች የስራ መደራረብ ጫና ምክንያት በይበልጥም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ማስረጃ ይፈለግባቸዋል ተብሎ በሚያዙ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጊዜን እና የተንዛዙ ቀጠሮዎችን በመጠየቃቸው“ የሚሉ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ የ2010 የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ባወጣው ዓመታዊ ዘገባው መሰረት የሚከተለውን መደምደሚያ ሰጥቷል፣ “የአገሪቱ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ነጻ ሆኖ እንዲሰራ ይፈቅዳል፡፡ የሲቪል ፍርድ ቤቶች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ነጻ ሆነው የሚሰሩ ቢሆንም የወንጀል ፍርድ ቤቶች ግን ደካማ ሆነው፣ በስራ ጫና ተወጥረው እና ለፖለቲካ ጣልቃገብነት እና ተጽእኖ ተጋልጠው የሚገኙ ናቸው“ በማለት ዘገባውን ቋጭቷል፡፡ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት የፍትህ ሂደት ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ ለፖለቲካ ጣልቃገብነት ከተጋለጠ ይህ የፍትህ ዘለፋ ነው!
የኢትዮጵያ ፍትህ ወይስ “ለኛ ብቻ የግል ፍትሕ”?
ከብዙ ጊዜ ጀምሬ “ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ” የተባለው ድርጅት ያነበረውን “የፍትህ ዘርፍ” በማስመልከት አሳፋሪ፣ ሙሰኛ እና ምናባዊ መሆኑ ላይ ትኩረት አድርጌ ትችት አቅርቢያለሁ:: እንዲሁም የቀልድ ፍትሕ ስርዓት መሆኑን አጋልጫለሁ፡፡ በኢትዮጵያ “የፍትህ ስርዓት” ህግ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው ማሰብ በገበያ ቦታ ሄዶ “ፍትህ” በአንድ ሰው ቀጥሎም በአንድ ፓርቲ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ማንነታቸው በማይታወቁ፣ በስም የለሾች፣ ፊተ ድብቆሽ ታማኝ ሎሌዎች፣ በስልጣን ጥላ ስር በመደበቅ ለመራመድ የሚፈልጉ ኃይሎች ጠቅላይነት የሚገዛ እና የሚሸጥ ሸቀጥ ከመሆን ያለፈ ሆኖ አይገኝም፡፡ የፍትህ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ ማጭበርበር የተሞላበት፣ ምዕናባዊ ፍትህ የታጨቀበት፣ በእጅ ተለቅመው የተቀመጡ መሃይም ዳኞች የሞሉበት፣ ክህሎቱ የሌላቸው ሰዎች የተሰየሙበት፣ የሸፍጥ አሰራር ያለበት እና የፍትህ ውጤቱም ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የተወሰነበት ስርዓት ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የህግ መርሆዎች እና ፍትህ የተነፈገበት፣ ወደጎን የተወረወሩበት፣ መልካም ነገር ከማድረግ የታቀቡበት፣ እና ውጤታማ ያልሆነ የፍትህ ስርዓት ነው፡፡ ድሆች፣ ከማህበረሰቡ የተገለሉ ሰዎች፣ ተስፋ ያላቸው ጋዜጠኞች፣ በኢፍትሃዊነት ላይ የሚነሱ አመጸኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች ትችቶች፣ አስቸኳይ ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች፣ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያልተሳኩ ጩኸቶች የሚያሰሙ ቢሆንም ቅሉ ሁሉንም ነገር በህግ መሰል መሳሪዎች እየገደሉ ጉዞ የሚያደርግ የፍትህ ስርዓት ነው የተዘረጋው፡፡ የገዥው አካል አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና አደግዳጊዎቻቸው ከህግ በላይ የሆኑበት እና ፍትህ ማለት ለኛ ብቻ የግል ፍትሕ ነው ብለው የሚያስቡ ፍጡሮች የተሰገሰጉበት የፍትህ ስርዓት ነው ያለው፡፡
የኢትዮጵያን “ለኛ ብቻ የግል ፍትሕ” ፍትህ ስነስርዓትን ማሻሻል
እ.ኤ.አ በ2008 ብሄራዊ የፍትህ ተቋም ለካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/National Justice Institute for Canadian International Development Agency የተባለ ድርጅት “ነጻነት፣ ግልጸኝነት፣ እና ተጠያቂነት በፍትህ ስርዓቱ“ በሚል ርዕስ አጠቃላይ የሆነ ጥናት በማድረግ 33 ተግባራዊ የሚሆኑ የመፍትሄ ሀሳቦችን ያካተተ የጥናት ዘገባ አቀረበ፡፡ ቁልፍ ከሆኑ የተሰጡ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፣ 1ኛ) የፍትህ ነጻነት መርሆዎች እና መብቶች በዳኞች እና በባለስልጣኖች እንዲተገበሩ ግፊት ማድረግ፣ 2ኛ) ጠንካራ እና ግልጽ የሆነ የሰራተኛ የመምረጫ ስርዓት በመዘርጋት በጣም ጠቃሚ የሆኑ “የፍትህ” ሰራተኞች ለመምረጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ 3ኛ) “ገለልተኛ የሆኑ፣ የስራ ብቃት ያላቸውን ዳኞች [ለጥበቃ] ከተጽእኖ እና ከሙስና እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቀልጣፋ የፍትህ ስርዓት ለማረጋገጥ ዋስትና መስጠት”፣ 4ኛ) “በህዝቡ ዘንድ ታማዕኒነት እንዲኖረው የፍትህ ስርዓቱን የማሻሻል ስራዎች በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ“፣ 5ኛ) “ለፍርድ ቤት ሰራተኞች ተገቢ የሆነ የስነምግባር ስልጠና” መስጠት፡፡ ማንም የገዥው አካል አባል ትንሽ እንኳ ጊዜ በመስጠት የጥናቱን ዘገባ እና ግኝቶችን በማንበብ ቢያንስ ጥቂቶችን የተሰነዘሩ የመፍትሄ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ያሸጋግራል የሚል ጥርጣሬ አንክዎን የለኝም፡፡ ከገዥው አካል ፍትሕን መሳለቅያ ከማድረግ ሌላ ብዙም ቁምነገር አልጠብ ቅባቸዉም፣ ለዚህም ነው በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት መሻሻሎች ሊፈጠሩ ይችላል የሚል አምነት የለለኝ የማልጠብቀዉም፡፡ የይስሙላው “ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ፍርድ ቤት የትኛውንም ዓይነት ሌላ ስም ቢሰጠውም ያው የይስሙላ ፍርድ ቤት ነው፣ እናም ፍትህ “ለኛ ብቻ የግል ፍትሕ” ተብላ ትነበባለች በዝያ የዝንጀሮ የፍርድ ስርዓት፡፡
ለአቶ አስራት እና ለአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የማበረታቻ ቃላት
በአቶ አስራት ላይ የተመሰረተው የሸፍጥ የዘለፋ ክስ በጣም መራራ የሆነ የህግ ማስፈራሪያ ዓይነት፣ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ የፖለቲካዊ ማስፈራሪያ ዘመቻ ለማካሄድ በልክ የተሰፋ የህግ ሽፋን ነው፡፡ የዘለፋው ክስ አቶ አስራት ወይም አንደነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ተሸማቀው አርፈው ይቀመጣሉ ወይስ ትግላቸውን ይቀጥላሉ የሚለውን ሁኔታ ለመሰለል የተደረገ ሙከራ ነው፡፡ አቶ አስራት ለተዋረደው ህግ ማመልከቻ አስገብተው ፍትሃዊነት በጎደለው መልኩ ከመሞዳሞድ ይልቅ ተቃወሟቸውን በማሰማት ትግሉን ለመቀጠል መርጠዋል፡፡ ትልቁ መልዕክት አዚህ ላይ ገዥው አካል ተቃዋሚዎችን ጸጥ እረጭ ለማድረግ፣ ለማፈን እና አፋቸውን ትርቅም አርጎ ለመለጎም “ፍርድ ቤቶችን” ከህግ አግባብ ውጭ እየተጠቀመባቸው ይገኛል፡፡
ዶ/ር ማርቲን ሊተር ኪንግ ከመብት ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልክ እንዲህ የሚል አመክንዮ አቅርበዋል፣ “አንድ ሃይል ስሜትን በማይቆጣጠር መልክ ህግን በመጣስ እየወተወተ ጫናውን ባበዛ ቁጥር ሌላው ተጎጂ ስርዓቱን ለመስበር እና ከኢፍትሃዊነት ጋር ላለመተባበር የሞራል ግዴታን ለመጎናጸፍ ይገዳዳል“ በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ከቢርሚንግሃ እስር ቤት በጻፉት ደብዳቤ ዶ/ር ኪንግ እንዲህ ብለዋል፣ “ማንም ቢሆን የሚፈጽመው ተግባር ፍትሃዊ አለመሆኑን ህሊናው እየነገረው ህግን የሚጥስ እናም የእስር ቅጣቱን በፈቃደኝነት የተቀበለ እና ለህብረተሰቡ ህሊና ኢፍትሃዊነቱን እያሳዬ ያለ በእርግጠኝነት የህግን ከምንም በላይ የበላይነት የተቀበለ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ አንድ ሰው ህጋዊ መሆን ብቻ አይደለም የሚጠበቅበት ሆኖም ግን ለትክክለኛ ህጎችም ተገዥ የመሆን የሞራል ግዴታ አለበት፡፡ በተገላቢጦሽ አንድ ሰው ፍትሃዊ ላልሆኑ ህጎች ላለመታዘዝ የሞራል ግዴታ አለበት… ፍትሃዊ ያልሆነ ህግ በምንም ዓይነት መልኩ ህግ አይደለም፡፡“ ዶ/ር ኪንግ በቀጣይም እንዲህ ብለዋል፣ ማናቸዉም ሰው “ከጭራቃዊነት ጋር ያለመተባበር ከደግ ነገር ጋር የመተባበርን ያህል የሞራል ግዴታ አለበት፡፡“ ጋንዲ ፍትሃዊ ያልሆኑ የቅኝ ግዛት ህጎችን ላለመቀበል በመቃወም እና ለበርካታ ጊዚያት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ለእስር ሲዳረጉ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፣ “ኢፍትሃዊ ህግ የኃይለኛነት ዝርያ ነው፡፡ በእርሱ ሸፍጥ ለእስር መዳረግ ደግሞ የበለጠ ግፍ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የህሊና ህግ እንዲህ ይላል፣ ኃይለኝነት በሌላ እርሱን በሚገዳደር ኃይለኝነት ሊወገድ አይገባም ሆኖም ግን ኃይልአልባ በሆነ መንገድ ነው መወገድ ያለበት፡፡ በዚህም መሰረት ህጉን በመጣስ እና በሰላማዊ መንገድ በቁጥጥር ስር በመዋል ለእስራት ተዳርጊያለሁ፡፡“
አቶ አስራት የማህተም ጋንዲን እና የዶ/ር ኪንግን መንገድ ተከትለዋል፡፡ ፍርድ ቤትን በመዘለፍ በሚል በቀረበባቸው የሸፍጥ ክስ ለመከላከል በመቃወም የሀሰት የፍርድ ሂደት የሰርከስ ተውኔት ከሚሰራው የይስሙላው ፍርድ ቤት ጋር ላለመተባበር ያላቸውን ጽኑ አቋም አስመስክረዋል፡፡ የዘለፋው ክስ ፍትሃዊ ያለመሆኑን ህሊናቸው ነግሯቸዋል፣ እናም በዚህ ኢፍትሃዊነት ላይ የህብረተሰቡን ህሊና ለማነሳሳት እንዲቻል በማሰብ “የመታሰርን ቅጣት በፈቃደኝነት ተቀብለዋል፡፡” አቶ አስራት ላሳዩት የሰለጠነ እምቢተኝነታቸው ታላቅ አድናቆት አለኝ፡፡ አቶ አስራት ላሳዩት ሰላማዊ የእንቢተኝነት ተቃውሞ አርአያነት እኛ ታላቅ ከበሬታ፣ አድናቆት እና ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡ በጣም ታላቅ የሆነ ድንቅ ትምህርት አስተምረውናል፣ “ከጭራቃዊነት ጋር ትብብር ለማድረግ የሞራል ግዴታ የሌለብንን ያህል ከደግ ነገር ጋር ለመተባበር ደግሞ የሞራል ግዴታ አለብን፡፡”
አጭር መልዕክት ላንባቢ
በፍርድ ቤት ዘለፋ ሰበብ ገዥው አካል አቶ አስራትን ወደ ዘብጥያ የመወርወሩ ሁኔታ ባዘጋጀው ደጋን የመጀመሪያው የዒላማ ተኩስ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ይህ ክስተት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን እንዲሁም በኢፍትሃዊነት ላይ የሚነሱ አመጸኞችን እ.ኤ.አ በ2015 ለሚያደርገው የታዕይታ አገራዊ ምርጫ ዝግጅት (ማስታወሻ፣ ምርጫ ለመስረቅ ዝግጅት አላልኩም፣ አልወጣኝም) አፍ ማስያዣ የማስጠንቀቂያ ደወል መሆኑ ነው፡፡ ገዥው አካል የተቃዋሚ መሪዎችን የጥንካሬ ስብዕና ለመለካት የተጠቀመበት ዘዴ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር መዋል እና ለእስራቱ መዳረግ በመፍራት ገዥውን አካል ከመገዳደር ወደኋላ ሊያፈገፍጉ ይችላሉን? ስልጣናቸውን በመጠቀም የእራሳቸውን ፍላጎት በሌሎች ላይ ለመጫን ከሚቅበዘበዙ ወሮበሎች ሮጦ በማምለጥ ለመደበቅ ይሞክራሉን? ወይም ደግሞ በአንድ ላይ ቆመው እንዲህ በማለት ያውጃሉ፣ “በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን፣ የናንተን ኢፍትሃዊ ህጎች እና የዘፈቀደ እርምጃዎች ማለትም የነጻ ሀሳብ መብቶቻችንን የሚጨቁኑትን፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመሰብሰብ ነጻነት፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫዎች፣ እና መብቶቻችንን መደፍጠጣችሁን እንድታቆሙ አጥብቀን እንቃወማለን እንዲወገዱም እስከመጨረሻው እንፋለማለን!“ ወደፊት ጊዜ የሚያሳዬን ይሆናል፣ ሆኖም ግን ገዥው አካል አቶ አስራትን ለእስር በመዳረግ የመጀመሪያዋን የደጋን ዝግጅት ተኩስ የተኮሰ መሆኑን እያንዳንዱ ሰው በአጽንኦ ሊመለከተው ይገባል፡

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ!
ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የተፈጠረው ቅራኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩት ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒቲው ሊቀመንበር እና በማህበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21 /2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል፡፤
በቅርቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የጠራውን የአባላት ሰብሰባ ተከትሎ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ደጋፊዎቻቸውን ወደ አዳራሹ በማስገባት ከማህበሩ ሊቀመንበርነቴ የተነሳሁት ያለአግባብ ነው በሚል በኮሚኒቲው ሊቀመንበር ላይ ቡጢ በመሰንዘራቸው ተከትሎ በተቀሰቀሰው መለስተኛ ግጭት ስብሰባው ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሺክ ሙስጠፋ ሁሴን የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21-2014 የኮሚኒቲው ስራ አመራር በጠራው ጠቅላላ የአባላት ጉባኤ ላይ ሁከት ለመፍጠር በብሄር ላይ የተመሰረተ ቅስቀሳዎችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች ከሪያድ አረጋግጠዋል።
ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ፌብሩዋሪ 14-2014 ምሸት አያሌ ደጋፊዎቻቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኘ አንድ ቢሮ ውስጥ በማን አለብኝነት ሰብሰብው ሲመክሩ መታየታቸውን የሚገልጹት ምንጮች ሼኩ ለግብረ አበሮቻቸው አማራ ስልጣናችን ስለነጠቀን ማንነታችንን ለማስከበር እና ስልጣናችንን ለማስመለስ እኛ ኦሮምዎች እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ፡አይገባንም ብለው በመናገር የጥቂት መስል ደጋፊዎቻቸውን በተሳሳተ መንገድ ቀልብ በመሳብ የኮሚኒቲውን አባላት በዘር በሃይማኖት ከፋፍሎ ለማጋጨት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አጋልጠዋል። የሼክ ሙስጠፋን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ብሄርተኝነትን በስፋት በማራገብ ላይ የተሰማሩት ቅጥረኞች በህገ ወጥ የሃዋላ ንግድ ላይ የተሰማሩ እና ቀደም ሲል በእህቶቻችን ህይወት ዶላር ሲሰብሰቡ የከረሙ የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ደላላዎቻቸው መሆናቸውን የሚናገሩ ወገኖች ግለሰቦቹ የትኛውንም ብሄር አሊያም የሃይማኖት ተቋም እንደማይወክሉ ገለጸው ህብረተሰቡ ከእንደነዚህ አይነት ሴጣናዊ መርህ ካነገቡ መሰሪዎች እራሱን በመከላከል በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል እንደወትሮው ሁሉ በአንድነት የኮሚኒቲውን ንብረት ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባው መክረዋል።
የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን በስማቸው በከፈቱት ሁለት ሰራተኛ እና አስሪ አገናኝ ኤጄንሲ ያስመጡዋቸው እህቶቻችን በህክምና እጦት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን የሚያስታውሱ ታዛቢዎች ሼኩ በሳውዲ አረቢያ የደህነት ሃይሎች ለእስር በመዳረጋቸውን ተከትሎ በኮሚኒቲው መተዳዳሪያ ህገ ደንብ መስረት የሊቀመንበሩን ቦታ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ያሲን ተረክበው መሸፈናቸው ሊያስመስግናቸው እንጂ ቡጢ ሊያሰነዘርባቸው እንደማይገባ የሚናገሩ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሼኩ ከወህኒ ከወጡ በሃላ ጤንነት እንደማይሰማቸው በመጥቀስ የኮሚኒቲ ሊቀመንበርነቴን ለምን በአማራ ብሄር ተነጠኩ በሚል ዘረኝነት የተጠቀሱትን ደጋፊዎቻቸውን በመስብሰብ በአባላቱ መሃከል የብሄር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመጫር እያሰሙ ያለው ጩሀት አብነት መሆኑንን ይገልጻሉ።
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር በስሩ ከሁለት ሺህ በላይ ህጻናትን ተቀብሎ የሚያስተናገድ አንድ አለም አቀፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባለቤት እንደነበር የሚገልጹ አንጋፋ የማህበሩ አባላት ት/ቤቱን ከኮሚቲው በመነጠል ኤምባሲው በራሱ ስልጣን ባስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ት/ቤቱን እንዳሻው እየዘወረ ላለፉት 4 አመታት ገቢ እና ወጪው ሳይለይ እስካሁንም የጥቂቶች ኪስ ማደለቢያ ሆኖ መቀረቱን ይናገራሉ። ዛሬ በኮሚኒቲው ስራ አመራር እና በሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች መሃከል የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ ከጥቅም ጋር የተቆራኘ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች በአሁኑ ግዜ ብቸኛ የማህበሩ ንብረት የሆነው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል ከት/ቤቱ ባላነሰ ሁኔታ ዘረፋ እየተፈጸመበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፤
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ከ8 መቶ የሚበልጡ አባላት እንዳሉት የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ማህበሩ የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21 2014 ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ መወሰኑን በመግለጽ በወቅቱ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ኤምባሲው እና የሚመለከታቸው አካላቶች የዜጎቻችን ህይወት ለመታደግ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባቸው አክለው ጠቁመዋል።
ጎልጉል
“ከአሜሪካ በላይ፣ ራሳችን ተፅዕኖ መፍጠር አለብን” ታማኝ በየነ
የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት (ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ከፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል። በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል። በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል። አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
Read more http://www.ethiomedia.com/14news/interview_tamagne_beyene.pdf

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን
አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤
እኚያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለትኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤ ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!
አቤ ቶኪቻው
አቤ ቶኪቻው
ወያኔን የሚጠላ ብቻ እየተመረጠ የሚያብድባት ሀገር
ከተወልደ በየነ(ተቦርነ) የካቲት 19 2014
በአንድ ወቅት የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፈን ወደ አንድ የአእምሮ ህመምተኞች ሆስፒታል ለመጎብኝት ያመራሉ:: በመጀመሪያ ያገኛቸው የአእምሮ ህመምተኛ አቀባበል ያደረገላቸው እንዲህ በሚል ነበር
“የባለቤትዎን የ22 ዓመት የስራ ውጤት ለመጎብኘት እንኳን ደህና መጡ::” መራር እውነት ያለው ቀልድ::
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወያኔ የተባለው የስብስብ ቡድን በአመራሩ ተማረው ከህዝብ ወግነው ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር ብለውጥያቄና ተቃውሞ የሚያነሱ የህዝብ ወገኖችን በተለያዩ መንገድአሳንሶ ለማየት የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች እየተጋለጡና እያሳጡት ከመጡ ሰነባበቱ:: የቅርብ ጊዜውን እንኳን ብናስታውስ የመምህር የኔሰው ገብሬን ሰላማዊ የተቃውሞ መስዋዕትነት አጣጥሎና አሳንሶ ለማየት በአእምሮ ህመምተኝነት በተለያዩ እፅች ተጠቃሚነት መወንጀሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ያለውን የአፈናና የጭቆና ስርዓት በሞያው መስዋእትነት ከፍሎ ለአለም ያሳወቀውን ጀግና ረዳት ካፒቴን ሀይለመድህን አበራ የጤንነት ችግር እንዳለበት ተደርጎ እህቱ ነኝ በምትል ግለሰብ በተለያዩ ድረ ገፆች የሀሰት አሉባልታዎች ማናፈስ ጀምረዋል::
እኔ ለእነዚህ ፈጣን የአሉባልታ አናፋሽ ባለሞያዎችና ቤተሰብነን ባዮች 3 ጥያቄዎችን ማንሳት እወዳለሁ::
ጥያቄ 1:- እንደዚህ በፍጥነት የረዳት አብራሪውን የጤንነት ችግር ለማሳወቅ የፈጠናችሁትና የጣራችሁትን ያህል ምነው ስለ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አሟሟትና የህመም አይነት ለመናገር ጊዜ ወሰደባችሁ? ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቆርቋሪ ቤተሰብና አጣሪ ባለሞያ የላቸውም?

ጥያቄ 2:- የህውሃት ነባር የኪነት ቡድን አባላት የነበሩ ዘጠኝ ታጋዮች ወደ ሱዳን በጉዞ ላይ ሳሉ በበሬና አሞራ ጣምራ ስህተት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል ታዲያ እንዲህ ችግሮች ሲፈጥሩ አጣርቶ ውጤቱንና ምክንያቱን የሚሳውቅ ፈጣንየባለሞያ ስብስብ ካለ የነዛ ታጋዮች ገዳይ የሆኑት የአሞራውና የበሬው ጤንነት ተጣርቶ ለምን እንደ አሁን ፈጥኖ አልተነገረንም ነበር?
ጥያቄ 3:- የመጨራሻው ጥያቄዬ የህወሀትን የትግልና የጀግንነት ገድል በሚተርከው ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ መፅሀፍ ላይ የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ስዩም መስፍን ታሪክ የሚዘክረው ቦታ ለይ በአንድ ወቅት አቶ ስዩም መስፍን በጠላት እጅ ወድቀው ለማምለጥ የተጠቀሙት ዘዴ እብድ መሆንን እንደነበር ማንበቤን አስታውሳለሁ::
ታዲያ አቶ ስዩም ለአላማቸው ሲሉ ያደረጉትን እብደት የኛው መምህር የኔሰው ገብሬና ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ለዓላማቸወ ሲሉ ቢያደርጉትስ ምን ያስገርማል?
ቸር እንሰንብት

Tuesday, February 18, 2014
የረዳት ፓይለቱ ሀይለመድህን እህት መልዕክት Message from co-pilot Hailemedin's Sister
በመጀመሪያ ይህን ጽሁፍ የምታነቡ ሰዎች በሙሉ የተዝረከረከ ከሆነባችሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ እስካሁን ኢንተርኔትና ቴለቪዥን ላይ ያለማቋረጥ ተተክየ ስለቆየሁና በጥልቅ ሃዘን ስለተመታሁ አይምሮየ ትክክል ላይሆን ይችላል።
‘የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ሮም ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን ጠልፎ ጄነቫ ላይ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ እጁን ለስዊዝ ስጠ። ምክንያቱም ስዊዘርላንድ ውስጥ ጥገኝነት ለመጠየቅ ነው ብሏል።’ የሚለውን ዜና በርካታ የዜና ማሰራጫዎች ከየፊናቸው አስተያየት ጋር አቅርበውታል። የዜና ማሰራጫዎች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ወገኖች ያሻቸውን ብለዋል። የፖለቲካ ድርጅቶች የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና እንደ አቤ ቶኪቻው ያሉ ቀልደኞች የየራሳቸውን ሃሳብ ለማስተላለፍ ተጠቅመውበታል። በጣም አሳዝኝ ነገር ነው። ሁሉም የየራሱን እምነት ለማስተላለፍ እንጂ እሱስ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ አለማሰቡ ልብ ይሰብራል።
ወንድሜ ሃይለመድህን አበራ የሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል አይደለም እንስሳትን ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው አይደልም። ደግሞም ያንን የጨነቀውን ያክል ከፈራው ነገር ለመሸሽ ሞከረ እንጂ ማንንም ባለመጉዳቱና ሃሳብ እንኳ እንዳልነበረው ምንም አይነት ማጥቂያ መሳርያ ባለመታጠቁ አሳይቷል። በሁሉም ዘንድ የሚታወቀው ለተቸገሩ በመድረስና ባዛኝነቱ ነው። ካገር ውጪ ሄዶ ለመኖር የሚፈልግ ሰው ቢሆን ለሱ በጣም ቀላል ነገር ነው። ከጥቂት ወራት በፊትንኳ ዩኤስ ኤ ሄዶ ነበር። ከ አስር ቀናት በላይንኳ መቆየት አልፈለገም። ዝም ብሎ ካገር መውጣት ቢፈልግ ከዛ የተሻለ አጋጣሚ አልነበረም። ደግሞም በኑሮ ደረጃ ውጪ ቢኖር ያን ያክል የሚያሻሽለው ነገር አይደለም። ምክንያቱም የገንዘብ ችግር የለበትም። ከራሱም አልፎ ለብዙ ሰዎች የሚተርፍ ገቢ ነበረው።
ከልጅነቱ ጀምሮ ጎበዝ ሳይሆን እጅግ በጣም ጎበዝ ጭንቅላት ያለው ወጣት ነው። አብዛኛዎቹን ክፍሎች ሁለት ሁለት እያለፈ አስራ ሰባት አመት ሳይሞላው ሀይስኩል ሲያጠናቅቅ የ አስራሁለተኛ መልቀቂያ ውጤቱ ሁሉም ኤ ነበር። የጀመረውን የ አርክቴክቸር ትምህርት ትቶ ወደ ፓይለትነት የገባው ለሙያው ካለው ፍቅር የተነሳ ነው። ለኢትዮጵያ አየር መንገድም የተለየ ክብር አለው።
ሃይለመድህን ሁሉንም አስታዋሽ ቤተሰቡን የሚወድና ተጫዋች ሰው ነበር እስከ ቅርብ ጊዜ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ለኛ ያለውን ፍቅር ደህነታችንን በማረጋገጥና የሚያስፈልገንን ሁሉ በመታዘዝ ቢገልጽም ከዘመድ ወዳጆቹ ጋር መገናኘትና አቆመ። የወትሮው ጨዋታና ደስተኝነቱ ቀርቶ ብቸኝነትን የሚወድ ዝምተኛ ሆነ። ህይወቱ ደስታ የራቀው መሰለ። በሁኔታው ተደናግጠን ደጋግመን በመጠየቅ ያወቅነው ሊያጠቁት የሚከታተሉት ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ነው። ስልኩን እንደጠለፉት ያስባል፤ በላፕቶፑ ካሜራ ሳይቀር ያዩኛል ብሎ ስለሚሰጋ ካሜራውን ሳይሸፍን አይከፍተውም፤ ወጥቶ እስኪገባ ቤቱን ሲበረብሩ የቆዩ ስለሚመስለው ካሜራ ጠምዶ መሄድ ሁሉ ጀምሮ ነበር። ባጠቃላይ በታላቅ የመንፈስ ጭንቀት እየተሰቃየ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ጉዳቱን ለኛ ለቤተሰቡንኳ አብራርቶ አለመናገሩ ነው። ወንድሜ ለሰዎች እርዳታ ለመድረስና የሌሎች አዳኝ ለመሆን የማይታክት ሰውንጂ እንዲህ በሚያንገበግብ ስቃይ ውስጥንኳ ለራሱ አስቦ እርዳታን የሚጠይቅ ሰው አይደለም። ሁኔታውን በደበስባሳው በታወቀበት ጊዜንኳ የሚያስፈልገውን የህክምና በማቅረብ ስላልረዳነው ቤተሰቡ ሁሉ እንደግር ሳት ይከነክነዋል።እሱ ግን እንዲህ ባለ ጥልቅ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥንኳ ለኛ አንድም ቀን ሳያስብ ቀርቶ አያውቅም።
ይህን የምታነቡ ወገኖች ሁሉ ዛሬ እኔ ይሄን ከምጽፍ እግዚአብሄር ምስክሬ ነው እሱ ወደነበረበት ጤናና ሁኔታ ተመልሶ እኔ ሞቼ ቢሆን እመርጣለሁ። ውሸት ከሆነ ይህንን በማድረግ የውሸቴን መልስ እንዲያሳየኝ አምላኬን እለምነዋለሁ። በኛ አገር መስሪያ ቤቶች የሰዎችን እውቀት ብቃትና ቁመና ሳይቀር ሲመዝኑ የዐይምሮ ጤንነት ሁኔታን አለመከታተላቸው እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው።
ወንድሜ ትናንት አውሮፕላኑ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ምን አጋጥሞት ይሆን እነዛ የሚላቸው ሰዎች ሲመለስ ጠብቀው እንደሚገሉት ዝተውበት ያንን ፈርቶ ይሆን ወይም ፓይለቱ ከጠላቶቹ ጋር በመተባበር ሊይጠቃው እንደሚችል ብማመን ሰግቶ ይሆን ሲወጣ ራሱን ለመከላከል በሩን የዘጋው ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም እንደሆነ አምናለሁ። አስቡት በዛች ቅጽበት አለሙን በሙሉ ሊያናጋ የሚችል ምንም አይነት ራሱን ሊከላከልበት የሚችል መሳርያ ሳይዝ ይህንን ድርጊት የሚያስፈጽም ምን ነገር ሊኖር ይችላል ስዊዘርላንድ ገነት አይደለችም። የዐይምሮ ህመም ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ለዚያውም በማንም ላይ ምንም ጉዳት ባልፈጸሙበትና ሊፈጽሙም ባላሰቡበት ሁኔታ ወደስር ቤት እንዲወረወሩ ህግ የሚፈቅድ አይመስለኝም። ሃይለመድህን ለህይወቱ ሰግቶ ነበር። የሰው ልጅ ሊቋቋመው በማይችል የመንፈስ ጭንቀት ገሃዱና ሃሳባዊው አለም በተዘበራረቀበት የስቃይ አለም ውስጥ ብቻውን ሲሰቃይ ነው የቆየው። በተስተካከለ የዐይምሮ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሰው ላይገባው ይችላል። እኔ ግን የሱን ግማሽ ባያክልም የተወሰነ ይህንን መሰል ችግር ስላለብኝ ህመሙን አውቀዋለሁ። ሁሌም በሳት እየተጠበሱ መኖር ማለት ነው
ወገኖች መልዕክቴን አንብባችሁ በምትችሉት ሁሉ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ፍትህ አግኝቶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ በመጣር እንድትተባበሩን መላ ቤተሰቡ በምታምኑት ሁሉ እንለምናችኋለን! እኛም የሚያስፈልገውን የህክምና እርዳታ አግኝቶ ወደ ቀድሞው ጤናው ከተመለሰ በኋላ ለዚች አገር ባለው አቅም ሁሉ እንዲያገለግል በማድረግ እንክሳለን!
እባካችሁ ይህን መልእክት በማስተላለፍ ተባበሩን!
Subscribe to:
Posts (Atom)