Friday, November 1, 2013

በኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታ የቻይና ኩባያዎች ሊሰማሩ ነው

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓመት 50ሺ የኮንዶምኒየም ቤቶችን ለመገንባት የያዘው ዕቅድ ከባድ ትችትን ያስከተለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዓመት ከ 100ሺ በላይ የቤቶች ግንባታ ለማከናወን ፊቱን ወደቻይና ኩባንያዎች ማዞሩ ተሰማ፡፡
አስተዳደሩ ከ800ሺ በላይ የኮንዶምኒየም ፣ ከ 136 ሺ በላይ የ40 በ60 ቤት ፈላጊ ነዋሪዎችን የመዘገበ ሲሆን ከዚህ ፍላጎት ጋር በማይጣጣም መልኩ በዓመት 50ሺ ቤቶች ገደማ ለመስራት የያዘው ዕቅድ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ትችትን አስከትሎበታል፡፡ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ባለፉት ቀናት በተካሄደው የአስተዳደሩ ጉባዔ ላይ በቤቶች ግንባታ ረገድ ያለውን የአፈጻጸም አቅም ለማሻሻልና ለማሳደግ የውጪ ኩባንያዎች እንዲገቡ በመንግስት በኩል ፍላጎት መኖሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ ለአስተዳደሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በቤቶች ግንባታ የቻይና ኩባንያዎች እንዲገቡ በመንግስት በኩል ፍላጎት መኖሩንና ከአንዳንዶቹም ጋር ምክክር መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በዓመት 50ሺ ቤቶችን ለመገንባትም ዕቅድ መያዙ ከፋይናንስ አቅሙ አኩዋያ ሲታይ ጥሩ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ በላይ ለመገንባት ግን ገንዘቡም ስለሌለው ሊያቅድ አይችልም ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የታሰበው ዓመታዊ ግንባታውን ከ100ሺ በላይ ለማድረስ የገንዘብ ብድር ይዘው መምጣት የሚችሉ ኩባንያዎች እንደሚያስፈልጉ ፣የጠቀሱት እነዚህ ወገኖች ፡ በዚህ ረገድ አስካሁን ፍቃደኝነታቸውን ያሳዩት የቻይና ኩባንያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በፓርላማ በተገኙበት ወቅት ከብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጭ አቶ ግርማ ሰይፋ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች አንዱ የኮንዶምኒየም ግንባታ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣምን የሚመለከተው ነበር፡፡ አቶ ግርማ በቤቶች ልማት መስክ በአዲስአበባ የተጀመረውና በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ፍላጎታቸውን ያሳዩበት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ረገድ መንግስት የተመዝጋቢዎችን ፍላጎት ያረካል ብለው እንደማያምኑ በመጥቀስ ይህ ፕሮግራም መንግስት የሚፈተንበት እንደሚሆን ተናግረው ነበር፣ አቶ ኃ/ማርያም በሰጡት ምላሽ መንግስት ምንም እንደማይፈተንና ፕሮግራሙም እንደሚሳካ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ መንግስት 40 በ 60 የተመዘገቡትን ነዋሪዎች ቤቱን በማህበር ተደራጅተው በራሳቸው ወጪ እንዲሰሩ በማግባባት ላይ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ አብዛኛው ተመዝጋቢ ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም።577459_661295503902535_178973835_n

No comments:

Post a Comment