Sunday, November 3, 2013

ህወሓቶች እየተከተሉት ያለ የሃይል እርምጃ




የህወሓት የፀጥታ ሃይሎች በሰለማዊ የትግራይ ሰዎች ላይ እየወሰዱት ያለ የሃይል እርምጃ የትግራይ ወጣቶች በሰለማዊ ትግል ዉጤታማነት ተስፋ ቆርጠው የትጥቅ ትግል እንዲመርጡ የሚገፋፋ ነው።
የህወሓት ሰዎች በትግራይ ወረዳዎች ባጠቃላይ በሑመራና አፅቢ በተላይ ሰለማዊ ዜጎችን እየደበደቡና እያሰቃዩ ይገኛሉ። ሰለማዊ ሰው ቤቱ ሰላም አጥቶ እየተገረፈ ይገኛል። ዛሬ በአፅቢ ወረዳ በድሮ የህወሓት ታጋዮችና ባሁኑ ካድሬዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ከፍተኛ አምባጓሮ ማደጉ ታውቋል።
ባሁኑ ሰዓት የመከላከያ፣ የደህንነትና የፖሊስ አባላት ሲቪል ለብሰው በየከተማውና በየኮርነሩ ህዝብ እየሰለሉ ይገኛሉ። በገጠር ወረዳዎች ደግሞ ዜጎችን ይገርፋሉ። ወጣቶች በስርዓቱ ተስፋ የቆረጡ ቁጥራቸው እየተበራከተ መጥቷል።
ከወደ ህወሓት ሰዎች እንደሰማሁት ከሆነ ዴምህት (ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ህዝቢ ትግራይ) የተባለ የትግራዮች ታጣቂ ቡድን በተለያዩ የትግራይ ወረዳዎች እየተንቀሳቀሰና ድጋፍ እያገኘ መጥቷል። ለዚህም ነው የህወሓት ወታደሮችና የደህንነት ሰዎች በትግራይ ክልል በብዛት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ።
አንድ ያልተገነዘቡት ነገር ግን አለ። የህወሓት ሰዎች ህዝቡን እያስፈራሩ ወጣቶች ወደ ዴምህት እንዲቀላቀል እያደረጉ ነው። በዚህ የህወሓት ስትራተጂ ዴምህት ተጠቃሚ ይሆናል። ህወሓቶችም ያስፈራቸው ዴምህት ሊሆን ይችላል። ግን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለዴምህት የሚጠቅም ነገር ይሰራሉ።
ባለፈው አንድ ከፍተኛ የህወሓት የደህንነት ባለስልጣን መቐለ ዉስጥ በጥይት መገደሉ ይታወሳል። የተገደለበት ምክንያትና ሁኔታ ክሀገር ደህንነት ጋር የሚገናኝ ስለሚሆንና ጉዳዩ በፍርድቤት ተይዞ ይሆናል የሚል ግምት ስላለኝ ወደ ዝርዝሩ አልገባም። ጉዳዩ ግን አሳሳቢ ነው።
ህወሓቶች እየተከተሉት ያለ የሃይል እርምጃ ካላቆሙ ወዴት እንደምናመራ መገመት አይከብድም።
It is so!!! abreha desta

No comments:

Post a Comment