Saturday, November 9, 2013

አሳዛኝ ሰበር ዜና ሪያድ በዜጎቻችን ድም እና እንባ ታጠበች ! መንፉሃ በሳውዲ ፖሊስ ዳግም ታመሰች !

ኢትዮጵያውያኖች በብዛት እንደ ከተሙባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ጨምሮ በመላው ሃገሪቱ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረው የበቤት ለቤት አፈሳ መልኩን ለውጦ በአሁኑ ሰዓት መፉሃና አካባቢው ወደ ጦርነት አውድማ ተለውጦል ።

ሪያድ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጩሀት እና ዋይታው እይተሰማ ነው ! ቀደም ሲል ቤት ለቤት ይደረግ የነብረው አፈሳ በወንዶች ላይ ብቻ ያነጣጠጠር መሆኑንን የሚገልጹት የአካባቢ ምንጮች ዛሬ ማለዳ ኢትዮጵያዊው በሰላም ሃገራችን አሳፍሩን አትደብድቡን ብለው ከየቤታቸው ነቅለው መወጣታቸው ያስደነግጣቸ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች እጁን በሰላም ለመስጠት አደባባይ የወጣውን ከ 6 መቶ የሚበልጥ፡ ኢትዮጵያዊ ለመበተን የሃይል እርምጃ በመውሰዳቸው ኢትዮጵያውያኑ አሁን ማምሻውን በገዛ ቤታችን ከምታሰቃዩን በአደባባይ ግደሉን ብለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከየቤቱ መውጣቱን የሚናገሩ ምንጮች በፖሊስ እና በኢትዮጵያውያኑ መሃከል በተፈጠረ ግጭት የትራፊክ እንቅስቃሴ መስትጓጓሉን ይገልጻሉ ። 

የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተጨማሪ ሃይል ወደ ተጠቀሰችው መንደር በምጣት የኢትዮጵያውያኑ ላይ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸው እይተነገረ ነው ። ወደ ኤንባሲ ስለሁኔታው ለማረጋገጥ፡ደውዬ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ዲፕሎማት ጉዳዩን ለማጣራት ሁከቱ ተፈጠረ ወደተባለበት አካባቢ መሄዳቸው አውስተው ኤንባሲው ጉዳዩን ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ማሳወቁን ከኤንባሲ የሚወጡ መረጃዎች ይገልጻሉ ።

ትላንት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት በኢትዮጵያ የሚገኙት የሳውዲ ምክትል አንባሳደር በኢትዮጵያውያኑ ላይ እይተፈጸመ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ በጽሑፍ ማብራሪያ እንዲሰጡ መታዘዛቸውን ከኢትዮጵያ ውጭጉዳይ ሚንስቴር መ/ ቤት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያው ውጭ፡ጉዳይ ሚንስቴር ክቡር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሳውዲ አረቢያ እትዮጵያውያን ላያ ያነጣጠረውን ድርጊት በቅርብ እየተከታተሉ መሆኑን ትላት በግል ቲውተራቸው ላይ መግለጻቸው ይታወሳል ።

Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment