Friday, November 1, 2013

4 ሺህ ዶላር ይዞ የተገኘው የናሽናል ጂኦግራፊ ፎቶግራፈር በጋምቤላ ታሰረ

(ፍኖተ ነፃነት) የናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ሮቢን ሃሞንድ በጋምቤላ ክልል በቁጥጥር ስር መዋሉን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዩጵያ ኢምባሲ ቪዛ ያገኘው ሮቢን በኢትዩጵያ በተለያዩ ክልሎች በመዘዋወር ፎቶ ግራፍ የማንሳት እቅድ እንደነበረው ተነግሯል፡፡የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ከኢትዩጵያዊ ረዳቱ ጋር ለእስር የተዳረገው 4000 የአሜሪካ
ዶላር በእጁ ይዞ በመገኘቱ ነው፡፡ወደ አገር የሚገባ ማንኛውም የውጪ አገር ዜጋ በእጁ የሚገኘውን ገንዘብ ማሳወቅ የሚገባው ቢሆንም ሮቢን ወደ አገር ሲገባ ከገለጸው ገንዘብ በላይ ይዞ መገኘቱ ለእስሩ እንደምክንያት ተወስዷል፡፡ ሮቢን በ2007 በዚምባቡዌ በሁለት አጋጣሚዎች ለእስር ተዳርጎ ነበር፡፡የሮበርት ሙጋቤ አስተዳደር በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ኢ ሰብአዊ ድርጊትና በአገሪቱ የተንሰራፋውን ድህነት በፎቶ ግራፉ ቀርጾ በማስቀረቱ ለ26 ቀናት ታስሮ በመጨረሻ አገሪቱን ለቅቆ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡በጋምቤላ ለእስር የተዳረገበትን ሁኔታየመንግስት ደጋፊዎች ከተናገሩት ውጪ ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልተቻለም ሲል ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገባውን አጠናቋል።

No comments:

Post a Comment