Wednesday, October 2, 2013

ህወሓቶች/ኢህአዴጎች ዉስጣዊ ችግራቸው ለመሸፈን በተቃዋሚዎች ላይ አላስፈላጊ እርምጃዎች ሊወስዱ ይችላሉ ተባለ

ህወሓቶች በዉስጣዊ ቀውስ እየታመሱ ነው። ከታሪካቸው እንደምንረዳው ዉስጣቸው ሲበሰብስና የመውደቅ አደጋ ሲደቀንባቸው የዉጭ ‘ጠላት’ ያፈላልጋሉ። ጠላት ከዉጭ መጣ ሲባል የርስበርስ ንትርኩ ለግዜው ይተውታል፤ ምክንያቱም ሁላቸውም የሰሩት የጋራ ጥፋት አለ። ለውድቀት ከተዳረጉ ጉዳቸው ይወጣል።
ስለዚ የውጭ ጠላት ሲመጣ ለጋራ ህልውናቸው ሲሉ ይተባበራሉ። ስለዚህ ህወሓቶች የዉጭ ጠላት ይፈልጋሉ፤ ከሌለም ራሳቸው ይፈጥራሉ። በነሱ እምነት የዉጭ ጠላቱ ህልዉናቸው የሚፈታተን ግን መሆን የለበትም። በኢህአዴግ ደረጃ ጠላታቸው ለይተዋል። አንድነቶች፣ ሰመያዊዎችና ሙስሊም ጠያቂዎች ለኢህአዴግ ህልውና አስጊ የሆኑ የውጭ ‘ጠላቶች’ ናቸው። ግን በኢህአዴግ የሚፈለጉ ዓይነት ጠላቶች አይደሉም፤ ምክንያቱም ለፓርቲው በትክክል አስጊ በመሆናቸው ለኢህአዴግ ዉስጣዊ ትብብር የሚረዱ ሳይሆን ክፍፍሉ የሚያባብሱ ናቸው። በህወሓት ደረጃም ጠላት ተለይተዋል። የህወሓት ጠላት ተደርጎ የተወሰደው ዓረና ፓርቲ ነው። ዓረና እንደ ዋነኛ አስጊ ጠላት ተይዞ እርምጃ እንዲወሰድበት ተመካክረውበታል። እንደዉጤቱም የዓረና ፓርቲ አባላት ማሰርና ማንገላታት ጀምረዋል። ለምሳሌ በተምቤን ቀሲስ ሃይላይ አረጋይ፣ በራያ ደግሞ ወጣት አድሃና ንጉሰ ያለምንም ጥፋት በህወሓት ታስረዋል። በመቐለም ይርጋ ገብሩ የተባለ የኮሌጅ መምህር ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ከስራው እንዲባረር ተደርጓል። ስለዚህ ህወሓቶች/ኢህአዴጎች ዉስጣዊ ችግራቸው ለመሸፈን በተቃዋሚዎች ላይ አላስፈላጊ እርምጃዎች ሊወስዱ ስለሚችሉ ከወዲሁ መጠንቀቅ ጥሩ ነው።

No comments:

Post a Comment