Wednesday, October 30, 2013

Reshuffles within the ENDF የሰሜን ዕዝና የአየር ኃይል ዋና አዛዦች በሌሎች ተተኩ

The Ethiopian National Defense Force (ENDF) has reshuffled at least two of its long serving top commanders. Both commanders were former gurriella fighters and current members of the core member party of the ruling Front, EPRDF, the Tigre People’s Liberation Front (TPLF). According to the Addis Abeba based Amharic biweekly, Reporter, Lieutenant General Se’are Mekonen, Commander of the Northern Command since 1998 and Major General Mola Hailemariam, Head of the Ethiopian Air Force, have both been removed from their posts and ”brought in to the center for a better appointment and responsibilities”. Major General Yohannes Woldegiorgis, who has been heading the Ethiopian force in Somalia, has now become the Head of the Northern Command replacing Se’are. Mola was replaced by Major General Adem Mohammed. All the
appointees come from the same Front, TPLF. Other reshuffles and reappointment have also been made. -የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ፡፡ በሽግሽጉ መሠረት ኤርትራ ኢትዮጵያን ከወረረች ጀምሮ የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ታዋቂው ሌተና ጄኔራል ሰአረ መኮንን በተሻለ ኃላፊነት ወደ ማዕከል እንዲመለሱ መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በተለይም የኤርትራን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የመከታተልና የመመከት ኃላፊነት በተሰጠው የመከላከያ ሠራዊቱ የሰሜን ዕዝ አወቃቀር ላይ ማሻሻያ መደረጉን ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ በተደረገው ማሻሻያ መሠረት የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ የነበሩት ሌተና ጄኔራል ሰአረ ወደ ማዕከል እንዲመለሱ ሲደረግ፣ በምትካቸው ሜጀር ጄኔራል ዮሐንስ ወልደ ጊዮርጊስ ተሹመዋል፡፡ ሶማሊያ የዘመተውን ሠራዊት የመሩና በተለያዩ ኃላፊነቶች የሠሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጄኔራል ሞላ ኃይለ ማርያም ምትክ ሜጀር ጄኔራል አደም መሐመድ መተካታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ሜጀር ጄኔራል አደም በአየር ኃይል አብራሪነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በመከላከያ ሠራዊት የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ደግሞ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት የአቢዬ ግዛት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ምክትል አዛዥ የነበሩ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር በሌሎች ጄኔራል መኮንኖች ኃላፊነቶች ላይም ሽግሽግ ማድረጉን የገለጹት ምንጮች፣ ከአየር ኃይል አዛዥነታቸው የተነሱት ሜጀር ጄኔራል ሞላ እንደ ሌተና ጄኔራል ሰአረ ወደ ማዕከል ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት መሾማቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ላለፉት አሥር ዓመታት በላይና በአሁኑ ወቅትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ የጠቅላይ ማኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሕግና ፍትሕ አስተዳደር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ተሹመዋል፡፡ አቶ አስመላሽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንባር ቀደም የሥራ ኃላፊነት በሆነው የሕግ ማውጣት ተግባር በስተጀርባ ቁልፍ ከሚባሉት ግለሰቦች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ባገኙት የሕዝብ ውክልና ባሳለፏቸው በርካታ ዓመታት የምክር ቤቱ የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ የሚመሩት ቋሚ ኮሚቴ ለፓርላማው የሚቀርቡ ረቂቅ ሕጐችን በተለይም ሕግና አስተዳደርን የተመለከቱትን በዋናነት የሚመለከት ሲሆን፣ የአገሪቱ የሕግና የፍትሕ ሥርዓት የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማትንም የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት አለው፡፡ በቅርቡ በአቅም ማነስ ምክንያት ከኃላፊነት የተነሱት የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ ከመሰናበታቸው አንድ ቀን በፊት ለፓርላማው ያቀረቡትን ሪፖርት በመተቸትና የሚኒስቴሩን ጉድለቶች በማስረዳት እንዲያስተካክሉ አቶ አስመላሽ መመርያ መስጠታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ethiopianreporter

No comments:

Post a Comment