Monday, October 21, 2013

መለስ የሚባል ራእይ የለም ሲሉ አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል።
የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ ሥራ ሠራ እንጂ ራዕዩ የመለስ አይደለም። ራይዩ የድርጅቱ ነው”ብለዋል። በዚሁ ቃለ-ምልልስ ከሟች ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ከወይዘሮ አዘዜብ መስፍን ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበርም አቶ ስብሀት በግልጽ ተናግረዋል። አቶ ስብሀት በዚሁ አስገራሚ መልሶችን በሰጡበት ቃለ-ምልልስ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ስለተሾሙት 33 ጀነራሎች ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ተናግረዋል። አቶ መለስ ማረፋቸውን ተከትሎ ከ አራቱ የ ኢህአዴግ ድርጅቶች በተውጣጡ አራት ምክትል ጠ/ሚ/ሮች እየተመራች ያለችው ኢትዮጵያ፤ያም አልበቃ ብሎ ከአራቱም ድርጅቶች የተውጣጡ አራት ከፍተኛ ካድሬዎች አማካሪዎች ተብለው አቶ ሀይለማርያም አጠገብ እንዲሆኑ መደረጋቸው ይታወሳል። አቶ ሀ ይለማርያም ደሳለኝም አመራራቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ፦በጋራ፣በኮሚቴ እየመራን ነው ማለታቸው አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment