Sunday, October 13, 2013

ስብሃት ነጋን አጅበው አክቲቪስት መስፍን ላይ ድብደባ የፈጸሙት ግለሰቦች ማንነት ታወቀ

(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው ዕለት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ባቀረበቸው ቪድዮ ላይ አክቲቪስት መስፍንን በቡጢ የተማቱትና የቆሙ መኪናዎችን ገጭተው ያመለጡት ግለሰቦች ማንነትን ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አረአያ ማወቁን ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ፡፡ የሕወሓት መንደርን ከቃረምኩት በሚል በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ የሕወሓት ምስጢሮችን በሚያጋልጠው ጽሁፎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ አረአያ ተስፋማርያም (ኢየሩሳሌም አረአያ) በትናንትናው እለት
ሱበአክቲቪስቱ ላይ ድብደባ የፈጸሙትን በሕግ የሚጠየቁት ግለሰቦች ሶስቱም የሕወሓት አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ ማንነታቸውን ዘርዝሯል። 1ኛው. የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ወንድም ታምራት ገ/መድህን፣ 2ኛው. የወያኔ ኪነት አባልና ጊታሪስት ወዲ ሰቦቃ (በአሜሪካ ፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ)፣ 3ኛው ሃይሌ በአሜሪካ – የኢትዮጲያ ኤምባሲ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ ሹፌር የነበረና በአሁኑ ወቅት በቪዛ ክፍል የሚሰራ ናቸው። አክቲቪስት መስፍን ለደረሰበት ድብደባ ሕክምና የተከታተለ ሲሆን ጉዳዩን በሕግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። በሌላ በኩል የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አንድ የቨርጂኒያ ጠበቃ አነጋግሮ ባቀረበው ዘገባው ስብሃት ነጋን ጨምሮ እነዚህ ግለሰቦች ሰውን በመደብደብና የሰው መኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀሎች ከተከሰሱና ፍርድቤትም ጥፋተኛ ካላቸው በ እያንዳዱ ክስ እስከ አንድ አመት የሚያስቀጣ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። ስብሃት ነጋም የወንጀል ተባባሪ፣ እንዲሁም የሰው መኪና ገጭቶ ባመለጠ መኪና ውስጥ በመሄዳቸውና ወንጀልን በመተባበር ክስ በአሜሪካ ህግ በወንጀል ተባባሪነት ሊከሰ የሚችሉበት ህግ አለ።

No comments:

Post a Comment