Thursday, November 7, 2013

አሸባሪውም ተሸባሪውም እራሱ ወያኔ ነው ::

ገዛኽኝ አበበ ከኖርዌይ የኢትዮጵያ መንግስት በተለያየ ጊዜ እና ሰአት ስለ አሸባሪ እና ሽብርተኝነት ማውራቱ አዲስ ያልሆነ እና የተለመደ ነገር ነው :: ይህንንም ወሬውን ሆነ ብሎ እና ከፍርአት የተነሳ የሚያደርገው እንደሆነ
በአንዳንድ የአገሪቱ ሕዝቦች ዘንድ እየተነገረ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የተቀወሚ ሀይሎች በየቦታው ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ሀይላቸውን እና ትግላቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸው እና ይኼ የወያኔ መንግስት መርዝ እንደበላች ውሻ በአገሪቱ ላይ የሚገኙትን ዜጓች እየለከፈ የሚገኝ ሲሆን በክርስትናም፣ በእስልምናም እምነት ውስጥ የሚገኙ አብዛኛው የሀገሪቱ ዜጓች ከወያኔ መንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ናቸው:: በኢትዮጵያም ሕዝብ ዘንድ በእጅጉ የሚጠላ መንግስት ሆኖል:: ይህንንም በሚገባ የሚያውቀው ነገር ነው:: ለዚህም ከሚገኝበት ፍርሃት የተነሳ ይመስላል በትናትናው እለት የጸረ ሽብር ግብረሀይል ነኝ ባዩ ለህዝቡ በአልሸባብ እና በኤርትራ መንግስት የሚደገፉ ሀይሎች በመላው አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል በማላት በውሸት በተቀነባበረ ድርጊት የሽብር ፐሮፖጋንዳውን እየነፋ የሚገኛው:: ይኼው አሸባሪው የወያኔ መንግት ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሃይለኛ ፍተሻ ሲያደርጉ እና ሕዝቡን ሲያስሸብሩ እንደነበሩ እና በዚህ ፍተሻ ሰበብ በባህር ዳር ከተመ የከተማውን ነዋሪ ሕዝብ በጣም ሲያጉላሉ እና ሲያስጨንቅ እንደነበር እናህዝቡም በከፍተኛ ደረጃ እየተንገላታ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ሲናገሩ እንደነበር ለማወቅ ችለናል:: የኢህአዲግ መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር ሀይሎች ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጅተዋል ብሎ በትናትናው እለት ይናገር እንጂ ነገር ግን እነዚህ በኤርትራ መንግስት ይደገፋሉ ያላቸውን ድርጅቶች ስማቸውን በዝርዝር አላስቀመጣቸውም :: በኤርትራ የሚደገፉ አሸባሪዎች በማለት የወያኔ መንግስት የፈረጃቸው ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦብነግ ፣ የግንቦት 7 ድርጅቶች ናቸው:: የወያኔ መንግስት የሽብር ጥቃት አደጋ ሊደረግ እንደታሰበበት በሃሰት የተሞላውን ትንበያ በመለፍለፍ ላይ ይገኝ እንጂ ከኢትዮጵያውያን ሕዝብ ዘንድ የመንግስ የሃሰት ትንበያ እና ማስጠንቀቂያ ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም :: ነገሩ ተቃራኒ ነው የሆነው አንዳንድ ዜጓች የወያኔ መንግስት በሕዝቡ ላይ ሊያደርስ ካለው የተቀነባበረ የሽብር ጥቃት እራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው እየመከሩ ይገኛሉ:: በርግጥም የወያኔ መንግስት የሀገሪቱን ዜጓች ለማሸብር በየቦታው ሊያደርግ ያሰበውን የማፍያ ስራውን እንዲያቋም እያሳሰብን ሕዝብም ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ እንድለበት እንመክራለን:: ለቀባሬ መርዶ አረዱት እንዲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሸባሪው ማን እንደሆነ እና ስለ አሸባሪ እያንዳንዶን ነገር ጠንቅቆ የሚውቅ ሕዝብ ሲሆን ወያኔ ኢህአዲግ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ አስርት አመታት ውስጥ የስልጣን እድሜውን ለመስረዘም አሸባሪን ሽፋን በመደረግ በአሸባሪነት ስም በአገሪቷ ላይ በእራሱ በወያኔ ካድሬዎች የተቀነባባረ ፍንዳታዎችን ሲያደርግ እና ሕዝብን ሲያቆስል እና ሲገድል መቆየቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ጠንቅቆ የሚያቀው ሀቅ ነው :: የወያኔ ኢአዲግ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቅንጣትም ያህል ግድ የሌለው እና የእራሱን እድሜ ለማራዘም ብቻ የቅጡን የባጡን እየዘባረቀ የሚኖር መንግስት መሆኑን ሰሞኑን እንኮን በሳውድ አረቢያ አሰቃቂ እና ዘግናኝ የሆነ ነገር በሕዝባችን ላይ እየደረሰ እያል የከፋ በደል እና ግፍ እየደረሰባቸው ስላለው ሕዝብ ጆሮ ዳባ ልበስ ማላቱ የወያኔ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ራዕይ የሌለው መንግስት መሆኑን የሚያሳይ ነው:: ለሕዝብ ራዕይ ያለው መንግስት የዜጓቹ መጎዳት መሰቃየት እና መሞት ግድ የሚለው ሲሆን የእራሱን የስልጣን እድሜ ለማራዘም ሽብርተኝነትን ሽፋን በማድረግ ሕዝብን የሚገድል አይደለም:: ስለዚህ ነብሰ ገዳዩ አሸባሪው የወያኔ መንግስት በሽበርተኝነት መጠየቅ አለበት ::

No comments:

Post a Comment