Friday, November 8, 2013

በሳዑዲ መቆየት የማይችሉ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት የሚመለሱበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን መንግሰት ገለፀSaudi Arabia police
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ መንግሰት በአገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየፈፀመ ያለውን ማዋከብ እንዲያቆም ጠየቀች።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዜና መፅሄታችን እንደገለፁት፥ የሳዑዲ ፖሊስ እያከናወነ ባለው አሰሳ ወቅት በተፈጠረ ግብግ የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉን ከተሰማ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃ ወስዷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአገሪቱ የሚገኙትን የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር አዲስ አበባ ባለመኖራቸው ምክትላቸውን በመጥራት ፥ መንግሰት በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ድርጊት እንደሚቃወምና ማዋከቡ እንዲቆም ጠይቋል።
በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየተወሰደ የሚገኘውን ተቀባይነት ስለሌለው ድርጊትም የሳዑዲ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥ መንግስት መጠየቁን ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲም በዚያ መቆየት የማይችሉ ኢትዮጵያውያን መመለስ የሚችሉበትን ሁኔታ እያመቻቸ እንደሚገኝና ይህን ጥረቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋለ ።

No comments:

Post a Comment