Tuesday, November 5, 2013

መንጌ ስለ ጄኔራል አማን አሟሟት በራሱ አንደበት


<<ጄኔራል አማን ብቸኛ ነበሩ:: ቤታቸውን የሚጠብቁትና አትክልት የሚኮተኩቱ አንድ ሽማግሌ ዘበኛ ናቸው ቤታቸው ያሉት:: ከብቸኝነታቸውም የተነሳ ሊሆን ይችላል ማታ ማታ ቤት ሲገቡ መጠጥ በሀይል ይጠጡ እንደነበር በኋላ ተረዳን:: ምግብ ከእህታቸው ቤት እየመጣላቸው ነው የሚመገቡት:: ቤተሰብ የላቸው ምን የላቸው::
እንደተነገረኝ መትረየሳቸውን ቤታቸው መስኮት ላይ ጠምደው ቁጭ ብለው ሊይዟቸው የሄዱትን ወታደሮች አላስጠጋ አሉ:: አስቀድመው በደንብ ተዘጋጅተዋል:: ጥይት ሞልቷቸዋል:: ወደቤታቸው መግቢያ ያለ አንድ መንገድ ነው:: ያንን መቃረቢያውን ይዘው መሳሪያቸውን ጠምደዋል:: ግራና ቀኙ በሙሉ መኖሪያ ሠፈር ነው:: ይሄን መትረየስ ይዘው ሲለቁት በየጎረቤቶቻቸው ቤት በየመስኮቱ በየበሩ ጥይት ይገባል::
በትዕዛዙ መሠረት በድምጽ ማጉያ እጃቸውን እንዲሰጡ ተጠየቀ:: መልስ የሚሰጡት ተኩስ በመክፈት ነው:: ጐረቤቱ <ኡ ኡ> ይላል:: ሠፈርተኛው ተሸብሯል:: እነ ተስፋዬ ተቸገሩ:: አሁን እንግዲህ ለአመጸኛና በዚህ አይነት የሠላማዊውን ነዋሪ ሕዝብ ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ሰው ምንድነው መደረግ ያለበት? ያለው አማራጭ ታንከኛ መጥራት ነው:: ምክኒያቱም ከሳቸው ጋር ተኩስ በመለዋወጥ ማንም ሰው መሞት የለበትም:: ወታደሮችስ አስፈላጊ ያልሆነ መስዋዓትነት ለምን አንድ ሰው ለመያዝ ብለው ይክፈሉ? ታንክ መጣ:: በዚያ ቤታቸውን ደርምሰው ገቡ:: በእንዲህ አይነት ሁኔታ የአማን ፍጻሜ ሆነ:: በኋላ እንደተወራው ራሳቸውን አልገደሉም:: በታንክ ነው ያጨማለቋቸው::
መንግሥቱ ነው ይገደሉ ያለው የሚለው ነገር ትክክል አይደለም:: እንኳን እኔ ደርጉም ቢሆን ይገደሉ አላለም:: እንዲታሰሩ በደርጉ ተወሰነ:: ያንን ማስፈጸም ኃላፊነቱ የኔ ነው:: የደርጉን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለተስፋዬ ገብረኪዳንና ለዳኔል ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ:: እነሱ በሥፍራው ላይ ተገኝተው ያጋጠማቸው ነገር ሠላማዊ ሰዎችንም ወታደሮችንም አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ አስፈላጊውን እርምጃ ወስደዋል::
ይሄ በማንኛውም የሚሊታሪ ግዳጅ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው:: ለአንድ ግዳጅ አንድ ሠራዊት ሲላክ በቦታው ላይ ተለዋዋጭ ነገር ሊያጋጥመው ይችላል:: ያንን እንደ አስፈላጊነቱና እንደ ሁኔታው ይከላከላል:: ይመክታል:: ይደመስሳል:: ይሄም ከዚያ አይለይም:: አንድ አመጸኛ ሊይዝ የሄደ ወታደራዊ ቡድን በሥፍራው ላይ ደርሶ በገጠመው አስገዳጅ ሁኔታ የተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ነው:: መስኮታቸው ላይ መትረየስ በመደቀን ቤታቸውን የጦር አውድማ ለማድረግ የመረጡት ጄኔራል አማን ራሳቸው ናቸው::>>
source: facebook

No comments:

Post a Comment