Saturday, November 9, 2013

አንድነት ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርስባቸው ጥቃትና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሳቸውን ገለፀ፡፡

 


ከትላንት በስቲያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርስባቸው ጥቃትና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሳቸውን ገለፀ፡፡ፓርቲው በፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከ2003 አንስቶ በአባላቱና ደጋፊዎቹ ላይ የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር አቅርቧል ፡፡
 “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት” በሚል ባወጣው ሰነድ፤ ከተዘረዘሩ ጥቃቶች መካከል:-
1- በድብደባ አካል ማጉደል፣ 
2በህገወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር ማዋል፣ 
3-ማሰቃየት፣ 
4-ማስፈራራትና መዛት እንዲሁም
5- በማስገደድ መረጃ ከፓርቲያቸው እንዲያመጡ ማድረግ፣ 
6-የመኖሪያ ቦታን በህገወጥ መንገድ መበርበር፣ 
7-ይዞታና ንብረትን ያለ ካሳ ነጥቆ መውሰድ… የሚሉት ይገኙበታል፡፡
 አንድነት  ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ,ጉዳታቸው በአካል በማሳየት በህገመንግስቱ እውቅና የተሰጣቸውን በህይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት እንዲሁም በህግ ፊት እኩል የመታየት ተብለው የተዘረዘሩት መብቶች መጣሳቸውን አቶ ደምሴ መንግሥቱና አቶ ገበየሁ ይርዳው የተባሉ የፓርቲው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

addis admas

No comments:

Post a Comment