To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Wednesday, October 2, 2013
የትምህርት ተቋማትን ከፖለቲካ እና ሃይማኖት እንቅስቃሴ ማጽዳት በሚል ሰበብ ደህንነቶች ስልጠና እየወሰዱ ነው:: ለትምህርት ጥራት መውደቅ ተጠያቂው የፖሊሲ አውጪው አካል ነው::
ምንሊክ ሳልሳዊ
የወያኔው ጁንታ ለአገዛዙ ያመቸው ዘንድ በየትምህርት ተቋማቱ የፈጠራቸው የፖለቲካ እና የሃይማኖት አልበሞች ጆሮው ላይ እያፏጩ ራስ ምታት እየሆኑበት ስለሆነ ይህንንም በዜጎች ላይ በአሸባሪነት እና በጽንፈኝነት ለመላከክ ቢሞክርም ስላልተሳካለት እና የሚያምነው ስላጣ በአዲስ መልክ ደህንነቶችን በየትምህርት ተቋማት በማሰልጠን ሊሰገስግ ስልጠናዎች መጀመሩ ተሰምቷል:; መሰግሰግ የማይሰለቸው የስልጣን ጥመኛው ወያኔ የትምህርት ተቋማቱ ከፖለቲካዊ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላማጽዳት በሚል በቁጥር የላቁ ካድሬዎቹን የስለላ እና የደህንነት ትምህርት በፌዴራል ጉዳዮች በኩል እየሰጠ መሆኑ ታውቋል::መመሪያ ለማስፈጸም በሚል ሰበብ በዜጎች ላይ ትልቅ ወንጀል እየተፈጸመ ሲሆን ተማሪው በስጋት እና በፍርሃት እንዲኖር ማሸማቀቅ የካድሬዎቹ ዋነኛ ተግባር ነው::
የወያኔ መንግስት የተማሪውን እና የአስተማሪውን የወላጅ እና የአሳዳጊውን የትምህርት ጥራት ጉድለት ሮሮ መስማት የጀመረው ስልጣኑ መፈረካከስ ሲጀምር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በማይረባ የትምህርት ፖሊሲ የአገሪቱን ትምህርት እና ተማሪውን ለውድቀት ለስራ አጥነት እና ለስደት እየዳረገው ከመገኘቱም በተጨማሪ የትምህርት ጥራትን አሳድጋለው በሚል ሰበብ በየትምህርት ተቋማቱ ደህንነቶችን ለመሰግሰግ ዝግጅቱን አጠናቋል:: የወያኔው ጁንታ በየትምህርት ተቋማቱ ከትንሽ እስከት ትልቅ ድረስ የደህንነት መዋቅሮችን በመዘርጋት የፖለቲካ መጠላለፍ በመፍጠር በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ አደጋ በመፍጠር ብቁ የተማሩ ዜጎች እንዳይወጡ ትልቁን አስታውጾ አበርክቷል::
ባለፉት 20 አመታት ወላጆች እና መምህራን የሃገሪቱ ስርአተ ትምህርት አዋጪ ያልሆነ እና መንግስት እንኳን ቢያምንበት በአግባቡ አለመተግበሩ እና ለፖለቲካ ፍጆታ መዋሉን ፣ ከሃገሪቱ የትምህርት ሂደት እና ታሪክክ እንዲሁም የትምህርት ፍላጎቶች ውጪ ለማስተማር ሂደት ስራ አመቺ ባልሆኑ ቦታዎች የእውቀት መገበያያ ተቋማትን ከፍቶ ማስተማርና የትምህርት ፖሊሲው የፈጠራቸው የተዘበራረቁ አሰራሮች ፥በስፋት እየታዩ ያሉ ችግሮች ኢሆኑ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሰው የቀጠሉ እና በየትምህርት ቤቶቹ ደጆች ላይ የጫት ቤት የሺሻ ቤት የማሳጅ ቤት ስርኣቱን ያልተበቀ የመዝናኛ ካፌ አልቤርጎዎች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ይህንን የአገልግሎት መስጫ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት የስርኣቱ ታማኝ ሰዎች እና የፖሊሲ አውጪው አካል ታዛዦች ናቸው::
ስርኣቱ የፈጠራቸው እና የፖለቲካው ድጋፍ ያላቸው የትምህርት ተቋማት በዘፈቀደ አሰራር የሚመሩና ጥራትና ደረጃውን ያልጠበቀ ትምህርት የሚያቀብሉ ከመሆናቸውም በላይ በተለያዩ ምክንያቶች የህብረተሰቡ የፋይናንስ አቅም ከማዳከምም አልፈው አስፈላጊውን የትምህርት ጥራት እንደማይሰጡ ሲነገራቸው ጌታዋን የተማመነች በግ .... እንደሚባለው በወላጆች እና በትጉህ መምህራን ላይ ሲደነፉ የተማኢዎችን ሰነድ ሲያበላሹ ይታያሉ :: የስርኣቱ አጋፋሪ አንሆንም ብለው በጥራት ትምህርት ሲሰጡ የነበሩት ለምሳሌ እንደ ዩኒት ዩንቨርስቲ አይነቶች ባለቤቶቻቸው ከአገር ጥለው እንዲተፉ ከፍተኛ ጫናዎችን በማድረግ ተማሪው አስፈላጊውን የትምህርት ጥራት እንዳያገኝ አትኩሮት እንዲያጣ እየተደረገ ነው::
የመንግስት ለስልጣኑ ብቻ አትኩሮት መስጠቱ አስፈላጊ የትምህርት ፖሊሲዎች መሻሻሎች መተግበሮችን እና አፈጻጸሞችን አለመከታተሉ ለሃገሪቱ የትምህርት እድገት አለመሰራቱ እና አስፈላጊ ካድሬዎች በሰው አገር በከፍተኛ ወጪ እንዲማሩ መደረኩ ያለው ስርኣት ለትውልዱ የትምህርት ሞራል ውድቀት ተጠያቂ ነው::የትምህርቱ ጥራት የአስተማሪው የማስተማር ጥበብ የእውቀት ግብይት የፋይናንስ ብዝበዛ የፖለቲካ እና የሃይማኖት ነቆራ የዘረኝነት ድባብ የሙስናው መንሰራፋት የስልጣን ማስረዘሚያ ሩጫ የደህንነቶች መሰግሰግ እና መንግስታዊ ማፊያነት አሸባሪነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ግድያ በህቡእ እና በግልጽ እየተፈጸመ ነገ አገሬ የማይል ትውልድ እና ወገኑን የማይጠቅም ዜጋ በየመንገዱ ከማፍራቱም በላይ ይህ የፖለቲካ አካሄድ የሚከተለው የፖሊሲ አውጪው አካል ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ማሳሰብ እወዳለሁ::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment