Monday, October 7, 2013

ጎጃም ውስጥ 8 አብያተክርስቲያናት ተቃጠሉ።

ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም. ባሉት ወራት ውስጥ ስምንት አብያተክርስቲያናት መቃጠላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት አትላንታ ከሚገኘው የማኅደረ አንድነት ራዲዮ ጋር ዛሬ ጠዋት ባደረጉት ቃለምልልስ አስታወቁ። አውባርና ነደድ በሚባሉ ሁለት የምሥራቅ ጎጃም ወረዳዎች በ5 ወራት ውስጥ ስምንት ያህል ቤተክርስቲያናት መውደማቸውንና የወያኔ አገዛዝ በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ክትትል የማድረግና ጥፋተኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ ምንም እርምጃ እንዳልወሰደ ማኅደረ ለመረዳት ችሏል። በተባሉት ወረዳዎች የተቃጠሉት ቤተክርስቲያናት፦ 1- አንጋጫ ኪዳነምህረት 2-ዋሻ መድኀኒዓለም 3- ደማሙ ኢየሱስ 4- ዳገት ሚካኤል 5- መንክር ማርያም 6-ምስለዋስ ጊዮርጊስ 7- የደርበን ሚካኤል እና 8- ቀዝቀዝ ገብርኤል የተባሉት ናቸው። የወረዳው ሕዝብ ቤተክርስቲያናቱን ከቀጣዩ ጥቃት ለመጠበቅ ማኅበር ገብቶ በየተራ ጥበቃ መጀመሩን ኢንጂኔር ይልቃል አስታውቀዋል።

No comments:

Post a Comment