Wednesday, October 2, 2013

በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከተፈቱት 39 ሰዎች መካከል 14ቱ ዛሬ የስራ ስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው

በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከተፈቱት 39 ሰዎች መካከል 14ቱ ዛሬ የስራ ስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጫ ከወራት በፊት የነተሳውን ተቃውሞ መርታችሁዋል በሚል 40 ሰዎች በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከቆዩ በሁዋላ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ቢያዝም ፖሊስ አልፈታም በማለቱ ሰዎቹ ለተጨማሪ ወራት ከታሰሩ በሁዋላ ከቀናት በፊት መፈታታቸው ይታወቃል። ይሁንና የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ ወደ መስሪያ ቤታቸው ሲያቀኑ ለ14ቱ የስራ ስንብት ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል። ከስራ ከተሰናበቱት መካከል አቶ ቲንኮ አሻንጎ ለኢሳት እንደገለጹት መስሪአ ቤታቸው በስራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም በሚል እንዳሰናበታቸው ገልጸዋል ግለሰቦቹ ማስረጃ አልተገኘባቸውም በሚል ፍርድ ቤት ነጻ እንዳደረጋቸው ቢናገሩም፣ የአካባቢው ሹሞች ትእዛዙ ከበላይ አካል የመጣ መሆኑን በመግለጽ ምንም ለማድረግ እንደማይችሉ ለሰዎች ገልጸውላቸዋል። ከስራ ከተባረሩት መካከል አቶ ደፋሩ ዶሬ፣ አቶ ቲንኮ አሻንጎ፣ አቶ አማኑኤል ጎተሮ፣ አቶ ሳምበል ሸዋ፣ አቶ ባንቲርጉ ሄባና፣ መምህር መሸሻ ዜና፣ መ/ር ዶሌቦ ጎንጃ፣ ወ/ሮ ጊፍቲ ሰለማ፣ አተፐ እዮብ ጦና፣ አቶ አስፋው ይና፣ አቶ አሊሙሳ አርባ፣ አቶ አበራ ገ/መስቀል እና አቶ ዘውዴ ጎአ ይገኙበታል። ተቃውሞውን በማስተባበር የተከሰሱት መቶ አለቃ ማሴቦ መዳልጮ አሁንም በአርባምንጭ በእስር ላይ ይገኛሉ። በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment