To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Thursday, August 1, 2013
ከመቀሌ፤ የአንድነት ከፍተኛ አመራር እና የፓርቲው አባል ታሰሩ
ሰበር ዜና ከመቀሌ፤ የአንድነት ከፍተኛ አመራር እና የፓርቲው አባል ታሰሩ በወላይታ ድብደባና ዝርፊያ እይፈጸሙ ነው
የአንድነት ከፍተኛ አመራር እና የፓርቲው አባል ታሰሩ
መቀሌ ውስጥ አንድ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት “መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በወላይታ የኢህአዴግ አባላት፣ፖሊስና ደህንነቶች በአንድነት አባላት ላይ ድብደባና ዝርፊያ እየፈፀሙ መሆኑ የደርሰን ዜና ይስረዳል። አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሶዶ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የበሩ የአንድነት አባላትን ፖሊሶችና ደህንነቶች በመደብደብና ያሰባሰቡትን የህዝብ ፊርማ በመንጠቅ ላይ መሆናቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የአንድነት የወላይታ ዞን አመራሮችም እንዳረጋገጡት ታርጋ ያልለጠፉ ባጃጆችንና ሞተር ሳይክሎችን የያዙ ፖሊሶችና ደህንነቶች በተደራጀ ሁኔታ የሚበተኑ በራሪ ወረቀቶችንና የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሻር እየተሰባሰበ የሚገኘውን ፊርማ በመቀማት ላይ ናቸው፡፡ አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የወላይታ ዞን ፖስ አባል ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፀው የዞኑ አስተዳደሮች “የአንድነት አባላትን በእጃቸው ያለውን በራሪ ወረቀትና የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅፅ ቀሙዋቸው እነሱን ማሰር አንዳች አይፈይድም” ተብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ሰብሳቢ አቶ ወኖ መንአሳ ለፍኖተ ነፃነት “ኢህአዴግ ያሰማራቸው ግለሰቦች ከአንድነት አባላት ላይ በራሪ ወረቀት ከመቀማት አልፈው ቦርሳ ፣ጫማ ፣በፌስታል የተያዘ ፍራፍሬ ሳይቀር በመቀማት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ለስብሰባ ስራ የተዘጋጁ ቁሳቁሶችም እንደተዘረፉ አስረድተዋል፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment