Thursday, August 1, 2013

በወላይታ የኢህአዴግ አባላት፣ፖሊስና ደህንነቶች በአንድነት አባላት ላይ ድብደባና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው

Posted: August 1, 2013 in Amharic News ሰበር ዜና በወላይታ የኢህአዴግ አባላት፣ፖሊስና ደህንነቶች በአንድነት አባላት ላይ ድብደባና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሶዶ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የበሩ የአንድነት አባላትን ፖሊሶችና ደህንነቶች በመደብደብና ያሰባሰቡትን የህዝብ ፊርማ በመንጠቅ ላይ መሆናቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የአንድነት የወላይታ ዞን አመራሮችም እንዳረጋገጡት ታርጋ ያልለጠፉ ባጃጆችንና ሞተር ሳይክሎችን የያዙ ፖሊሶችና ደህንነቶች በተደራጀ ሁኔታ የሚበተኑ በራሪ ወረቀቶችንና የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሻር እየተሰባሰበ የሚገኘውን ፊርማ በመቀማት ላይ ናቸው፡፡ አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የወላይታ ዞን ፖስ አባል ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፀው የዞኑ አስተዳደሮች “የአንድነት አባላትን በእጃቸው ያለውን በራሪ ወረቀትና የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅፅ ቀሙዋቸው እነሱን ማሰር አንዳች አይፈይድም” ተብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ሰብሳቢ አቶ ወኖ መንአሳ ለፍኖተ ነፃነት “ኢህአዴግ ያሰማራቸው ግለሰቦች ከአንድነት አባላት ላይ በራሪ ወረቀት ከመቀማት አልፈው ቦርሳ ፣ጫማ ፣በፌስታል የተያዘ ፍራፍሬ ሳይቀር በመቀማት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ለስብሰባ ስራ የተዘጋጁ ቁሳቁሶችም እንደተዘረፉ አስረድተዋል፡፡‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬ – See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5181#sthash.4PNh87Fg.dpufhp/v2/y4/r/-PAXP-deijE.gif

No comments:

Post a Comment