To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Monday, August 26, 2013
Monday, August 26, 2013 “እመኑኝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አምባገነኖች ይወድቃሉ ህዝብ ያሸንፋል!!!”
“እመኑኝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አምባገነኖች ይወድቃሉ ህዝብ ያሸንፋል!!!” ከኢቲቭ ውይይት የተወሰደ Minilik Salsawi
አቶ ሽመልስ በበደኖ ጭፍጨፋ ጊዜ እርሶ የመንግስት ወንበር ላይ ሳይሆን ለገሃር ያሲን ጫት ቤ ወንበር ላይ ነበሩ:: Minilik Salsawi “እመኑኝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አምባገነኖች ይወድቃሉ ህዝብ ያሸንፋል!!!” ከኢቲቭ ውይይት የተወሰደ በወያኔው ቴሌቭዥን (ኢቲቭ) ዛሬ ይቀርባል ተብሎ ከሚጠበቀው ቃላቶች በተለቀሙበት እና በተቆራረጡበት የጸረ ሽብር ውይይት ውስጥ ጠንከር ያለ ንግግር ከተባሉት አንዱን የኢቲቭ ሰራተኛ እንዲህ ያስነብበናል::
"....እነ እስክንድር ነጋ አንዷለም አራጌ በአደባባይ ጀግና እና ሰማእት እያላችሁ ስትፎክሩ ነበር ..ፍርድ ቤት አሸባሪ መሆናቸውን አረጋግጧል አሽባሪነትን ማበረታታት ደግሞ በአዋጁ መሰረት አሸባሪ መሆን ማለት ነው ስለዚህ ብትጠነቀቁ ይሻላል ...." በማለት እነሽመልስ ከማል ለማስፈራራት ሞክሯል::
እንደ ኢቲቭ ጋዜጠኛ እምነት በአለም አቀፍ ደረጃ የእስረኞች ጉዳይ አሳስቧቸው የሚጮሁ ሁሉ ለጋሽ አገራትን ጨምሮ አሸባሪዎች ናቸው ስለዚህ ሊጠየቁ ይገባል::
ከተወያዮች አንዱ ለዚህ የሰጠው መልስ ".....እስክንድር አንዷለም ርእዮት ፍርድ ቤት ነጻ አይደለም ብለው ሲታገሉ የነበሩ እኛም ነጻ አይደለም ብለን ስለምናምን ዛሬም በናንተ ፊት ነገም በአደባባይ ጀግኖቻችን ናቸው ብለን እናምናለን::እንመሰክራለን በዚህ ጉዳይ የመኢመጣ መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ::....አምባገነኖች የጊዜ ጉዳይ እንጂ ይወድቃሉ::ህዝብ ያሸንፋል!!!!..."
አቶ ሽመልስ ከማል "በአንድነት ፓርቲ ሽብር የለም ነው የምትሉት??" ብለው ያልተረጋገጠ ህገወጥ ንግግር ሲናገሩ
ከተወያዮች አንዱ "....እዛም እዚህም የተፈጸሙ የሽብር ተግባራት አይተናል ቁምነገሩ እነዚህ የሽብር ተግባራት በማን ተፈጸሙ ነው...በቅርቡ ዊክሊክስ ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው የቀድሞዋን የአሜሪካ አምባሳደር ጠቅሶ የሽብር ጥቃቶቹ በመንግስት እንደተቀነባበረ ስለተነገር ጉዳዩ በገለልተኛ አካል ሊጣራ ይገባል.....እናንተ ያሰራቹዋቸው የለውጥ ሃዋሪያ የሆኑ የተቃዋሚ አመራሮችን እና ጋዜጠኞችን እንጂ አሸባሪዎችን አይደለም...."
በስህተት አቶ ሽመልስ ስለ በደኖ ጭፍጨፋ አንስቶ ነበር...መልስ ያለጠፋው የተቃዋሚ ተወያይ የበደኖ ጭፍጨፋ በሕወሓት እና በኦነግ በሽግግር ወቅቱ የተፈጼመ ነው::....ሽመልስ ከማል በስህተት አምልጦት እንዳነሳው ከፊቱ ላይ ይነበብ የነበረ ድንጋጤ ያስታውቅ ነበር...... ይህንን እርስዎ የተናገሩትን የፍትህ ጋዜጠኛ በመናገሩ በአሁን ወቅት ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ይገኛል .....ህገመንግስቱ ለሃገር ሳይሆን ለኢናንተ ብቻ እንደፈለገ እያገለገለ ነው......
ዝርዝር ውይይቱን ቢቆራረጥም በ ወያኔ ቲቭ ጠብቁት:: ምንጮቻችን ኢቲቭዎች ናቸው::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment