To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Wednesday, August 21, 2013
የመንግስት ብልግና ተቃዋሚዎች በተለያየ መልኩ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል
የመንግስት ብልግና ተቃዋሚዎች በተለያየ መልኩ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋልበነገራችን ላይ፤
ኢትዮጵያችን ድህነት ውስጥ ነች፣ ኢትዮጵያችን ድምፅ የሚታፈንባት ሀገር ሆነች፣ ኢትዮጵያችን ሰዎች የሚሰደዱባት ሀገር ሆነች፣ ኢትዮጵያችን ባለስልጣኖች እና አባሎች ብቻ የሚበለጥጉባት ሀገር ሆነች፣ ሆነች ሆነች ሆነች… የምንለው የሀገሪቱን ስም ለማጥፋት አይደለም፡፡
“አረ በቃ በቃ
ጉሮሯችን ነቃ”
ለማለት ፈልገን ነው…!
ለማንኛውም የመንግስት ብልግና ተቃዋሚዎች በተለያየ መልኩ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የፊታችን እሁድ አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ በባህር ዳር፣ በጂኒካ፣ በመቀሌ፣ በአርባ ምንጭ እና በወላይታ ሶዶ… የመንግስትን ብልግና ሊቃወሙ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል፡፡ መንግስትም ይለይላችሁ ብሎ ብልግናውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በ 24 ሰዓት ውስጥ መቀሌን ለቀህ ውጣ የሚል ብልግና፤ እስር እና ድብደባን የመሰለ ብልግና ከመንግስት ማይጠበቅ ብልግና…
የሰቆጣ ወጣቶች በቅርቡ በራሳቸው አነሳሽነት አሁንስ በዛ…. ብለው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ (ያልነገርኩዎት ነገር ሰቆጣን አውቃታለሁ፡፡ ከስምንት አመት በፊት ለአንዳች ልማታዊ ስራ ተጉዤባት ነበር፡፡ ታድያ ከትላንት ወዲያ ከወደ ሰቆጣ የሰማነው ተቃውሞ ያኔም በእያንዳንዱ የሰቆጣ ሰው ሲነገር የነበረ ነው፡፡ ሰቆጣዎች ያኔም ታጋዮቹን በሰንበት ሁላ ፈጭተን አብልተናቸው ከዱን እያሉ አብዝተው ያማርሯቸው ነበር፡፡ ኢህህዴግ ነፍሴ “ስክሪን ሴቨሯን” አዲሳባን ብቻ ባለ ሀብቶች እንዲያሳምሩ አድርጎ ውስጣ ውስጦቹን “ሀገራችሁ ለትግል እንጂ ለልማት አይመችም” እያለ “ላሽ” ብሏቸዋ የለ… (በሌላ ቅንፍ ፅንፈኛ ከተባልን አይቀር ደግሞ፤ ከአዲሳባም እነ ሽሮሜዳ የልማቱ ተቋዳሽ ሳይሆኑ የእንግዳ መውጫ መግቢያው ቦሌ ነው ያማረበት ብለን እናማርራለን)
…እናልዎ ሰቆጣዎች ከስምንት አመት በፊት ለእኛ ሲያወጉን የነበረውን ነው ዛሬ በአደባባይ ያሰሙት፤ “መንገድ መርተን አስገብተን መንገድ የሚሰራልን አጣን!” እያሉ ነው) ከሰቆጣዎች ጋር የሚመሳሰል ተቃውሞ ጎንደሮች በዛ ሰሞን አካሂደዋል፡፡ ወለጋዎችም ቀን እየጠበቁ ነው፣ ወልቂጤዎችም ቀጠሮ ሳይዙ አይቀሩም፣ ሃዋሳዎችም እስቲ ትንሽ እንየው ብለው እንጂ መቆጣታቸው አይቀሬ ነው፣ጋምቤላዎችም ከዛሬ ነገ እያሉ ነው እንጂ በየቦታው በርካታ የልማት ችግሮች አሉ፡፡
እና እንደነገርኩዎ አንደነት ፓርቲ እሁድ በባህር ዳር፣ በጂኒካ፣ በመቀሌ፣ በአርባ ምንጭ እና በወላይታ ሶዶ… ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ዶክተር ነጋሶ በሊቀመንበርነት የሚመሩት አንድነት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ብሎ መንቀሳቀስ ከጀመረ… ሰነባበተ ብዬ መቼም አልነግርዎትም!
ሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄዎቼ ካልተመለሱ ወይ ፍንክች ማለቱንም ያውቃሉ፤ ድምፃችን ይሰማ ያሉት ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ነገርም እየሰሙ ነው፡፡ ታድያ ኢህአዴግዬን፤
“ተጠየኩኝ ብለሽ አትበይ ጠመም ገተር
መመለስ ነው ደጉ ላንቺም ሆነ ላገር
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment