To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Saturday, August 24, 2013
የምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉን ነገሮች ምንድን ናቸው?
ዛሬ ኢትዮጵያ አገራችን ከምትገኝበት ልዩ ልዩ ማህበራዊ፣ የህልውና ቀውስና ችግር፣ ለማውጣትና የተሻለ ሥርዓተ ማህበር ለመመስረት ምን መደረግ አለበት የሚለውን ጥያቄ በርከታ የወገን መከራና ስቃይ የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚጠይቁት የወቅቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው።ለጥያቄዎቹ መልስ ይሆን ዘንድ ብዙ ታሪካዊና ወቅታዊ የፖለቲካ ትንታኔዎች ተሰጥቷል ፣ብዙም ተጽፏል ፣ብዙም ተነግሯል፣ ሆኖም ግን አገራዊና ማህበራዊ ችግራችን ከመቸውም ግዜ የበለጠ እየከፋና እየባሰ መጣ እንጂ ለመሰረታዊ የለውጥ መፍትሄ የሚያበቃን እውነተኛና ተግባራዊ መልስ አልተገኘም ። በተጨባጭ ወቅቱ የሚጠይቀውን አውንታዊ ምላሽ አልሰጠንም። በተገቢው ግዜ ተገቢውን መልስ በመስጠት የገጠመንን ውስብስብ ችግር በጥራት አውቀን ለድል አሸጋጋሪ የሆኑ መንገዶችን መፍጠር ለግዜው አልቻልንም። ስለዚህ ጥያቄው ለምን አልቻልንም ነው?እንድንችልስ ምን መደረግ ይኖርበታል? ለዚህ ጥያቄም ሆነ ለሌሎቹ አንድ ወጥና ለሁሉም ግልጽ የሆነ መልስ ባይኖርም ፣ ወሳኝ የሆኑትን የችግሮች ባህርያትና መንስኤዎች በትክክል መርምሮና ለይቶ ማወቅ ፣ለጥያቄያችን መልስና ለምንሻው መፍትሄ አስፈላጊ የመጀመርያ የተግባር እርምጃ ነው። የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና ዓላማም አንዳንድ ወሳኝ ጥያቄዎችን በማንሳት አሁን ከምንገኝበት የአስተሳሰብና የምግባር አዙሪት ውስጥ መንጥቆ ሊያወጣን የሚያስችል አቅም ገንቢ፣ መፍትሄ አዘልና ውጤታማ ሃሳቦችን ለመጠቆምና ለማመላከት ብሎም በትግላችን ሂደት ላይ እምርታዊ አስተሳሰብን ለመፍጠር እንዲያስችለን ነው።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment