To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Wednesday, August 28, 2013
የወያኔ መንግስት የግንቦት 7 ቡድን አባላት ናቸው ብሎ የጠረጠራቸው ላይ ክስ መሰረተ
የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን አባላት ናቸው በሚል የተጠረጠሩ 10 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው ።
ተከሳሾቹ ዘመኑ ካሳ በዕውቄ የግንቦት ሰባት ልዩ ሃይል ታጣቂ ፣ አሸናፊ አካሉ አበራ ፣ ደህናሁን ቤዛ ስመኝ ፣ ምንዳዬ ለማ ፣ አንሙት የኔዋስ አለኽኝ ፣ሳለኝ አሰፋ ወንድምአገኝ ፣ የአማራ ክልል የማረሚያ ቤት ረዳት ሽፍት መሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉዬ ማናዬ ረታ፣ፀጋው ካሳ እንየው ፣ የአለም አካሉ አበራ እና ሙሉ ሲሳይ መቆያ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከፈረጀውና እራሱን ግንቦት ሰባት እያለ ከሚጠራው ድርጅት አመራሮች ጋር በመገናኘት ለሽብር ስር በጋራ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ነው የፌዴራሉ አቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው ።
የፌዴራሉ አቃቤ ህግ መረጃዎችን ሰብስቦ ነሃሴ 13 ክስ መስርቶባቸው ትላንት በአቃቂ ጊዜያዊ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ተከሳሾቹ ጠበቃ የማቆም አቅም ስለሌላቸው የመንግስት ጠበቃ እንዲቆምላቸው ችሎቱ አዟል።
ችሎቱ 1ኛ ተከሳሽ በሌለበት ክሱ በመቅረቡ በጋዜጣ እንዲጠራ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ክሱን ለመስማትም ችሎቱ ለህዳር 2 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ይዟል ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment