Monday, August 26, 2013

በወያኔን “ያደገችዋን” ኢትዮጵያ ዓለም እንዴት ያያታል? August 26, 2013

ዶ/ር ዘላለም ተክሉነሐሴ 25 2013 በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢሳት የቀረበውን “ የእሁድ ወግ” ፕሮግራም ሳዳምጥ ነበር:: በዚሁ ፕሮግራም ከቀረቡት ዋና ዋና መወያያ ርዕሶች ውስጥ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ አጎናጸፉት እየተባለ ስለሚደሰኮረው ዕድገት የተሰጡት አስተያየቶች ትኩረቴን ስበውኝ ነበር:: በተለይ ሰውዬው (ከሳቸው የተማርኩት አባባል ስለሆነ ይቅርታ) ህዝቡን ጥጋብ በጥጋብ አደረጉት፣ ብዙ ሃብታም ገበሬዎችን ፈጠሩ፣ሚሊዮኖችን ከድህነት አረንቋ አላቀቁ ስለሚባለው አቶ ሲሳይ አጌና የሰጠው ምላሽ በጥሩ ትንተና የተደገፈ መሆኑ ያስደሰተኝ ሲሆን በዚች ትንሽ መጣጥፍ የበለጠ ማጠናከሪያ በመስጠት ፕሮፓጋንዳውን ለመሞገትና ምስኪኑ ህዝባችንም እውነታውን ራሱ ፈትሾ እውነቱን እንዲያውቅ ፈለኩ::

No comments:

Post a Comment