Monday, August 5, 2013

Monday, August 5, 2013 after 4 years Ethiopian government has lunch meeting on the anti terrorist law

መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ለማሻር የጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በሀገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና የመዋያያ አጀንዳ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ህጉ ከፀደቀ ከ4 ዓመት በኋላ ፓርቲዎች በህጉ ላይ ያላቸውን አቋም የሚያስረዱበት መድረክ አዘጋጀ፡፡ ኢቲቪ አንድነት ፓርቲን ጨምሮ ለተለያዩ ፓርቲዎች ደብዳቤ የላከ ሲሆን አንድነት ፓርቲ በበኩሉ በ5 የክልል ከተሞች ለሚያደርገው ህዝባዊ ንቅናቄ አመራሮቹን ስላሰማራ የውይይት መድረኩ እንዲራዘምለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በስኬት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡‪#‎millionsofvoicesforfreedom ‪#‎Ethiopia ‪#‎UDJ

No comments:

Post a Comment