To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Tuesday, July 30, 2013
ፖሊስ ማሰሩን አንድነቶችም ወረቀት መበተናቸውን አላቋረጡም
ፖሊስ ማሰሩን አንድነቶችም ወረቀት መበተናቸውን አላቋረጡም
=============================================
የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ የጀመረው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዜጎች ህገ መንግስቱን በመጨፍለቅ በጸረ ሽብርተኝነት ሽፋን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣ጋዜጠኞችንና የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ መግባት የሚቃወሙ ዜጎችን በሽብርተኝነት በመወንጀል ወህኒ እያወረደ ያለውን የጸረ ሽብር አዋጅ በመቃወም እንዲሰረዝ ፊርማቸውን በፓርቲው ጽ/ቤት በመገኘት በተዘጋጀው የፊርማ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት ለህዝቡ ማሰራጨት ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ፖሊስና ደህንነት በጥምረት በመሆን የፓርቲውን አባላት ሲያስሩና ሲፈቱ መቆየታቸው የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
እንደተለመደው ዛሬ 22/07/2005 ይህንኑ በራሪ ወረቀት ለመበተን በልደታና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ከተንቀሳቀሱ ወጣት የፓርቲው አባላቶች መካከል ፖሊስ የተወሰኑትን ለሰዓታት ካሰረ በኋላ ‹‹ሁለተኛ ወረቀት ስትበትኑ ለምትበትኑበት ወረቀት ፈቃድ ካላመጣችሁ በወንጀል እጠይቃችኋለሁ ››በማለት ለቅቋቸዋል፡፡በፖሊስ ተይዘው የነበሩት ወጣቶች ‹‹አንድ ህጋዊ ፓርቲ ወረቀት ለመበተንና ዜጎችን የእንቅስቃሴው አካል ለማድረግ ፈቃድ የሚጠይቅበት አግባብ የለም፡፡ይህንን ወረቀት የሚበትኑት የኢህአዴግ አባላት ቢሆኑ አስቁማችሁ እንደማትጠይቋቸው እያወቅን እኛን ማጉላላታችሁ አሳስቦናል››በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
#millionsofvoiceseforfreedom #ethiopia #udj

Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment