Thursday, July 25, 2013

ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን

ከ40 በላይ የቁጫ ወረዳ ሽማግሌዎች ጉዳያቸውን ለፌደራል መንግስቱ አቀረቡ ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀምሌ ወር መግቢያ በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩትን ከ60 በላይ የከተማዋ ታዋቂ ሰዎችን ለማስፈታት እና ላቀረቡትም ጥያቄ መልስ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በትናንትናው እለት 40 አገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ጥያቄአቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል። ምክር ቤቱም ጥያቄውን የማየት ስልጣን ያለው የክልሉ መንግስት በመሆኑ አጥጋቢ መልስ ሳይሰጣቸው እንደቀረ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ከአገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ ለኢሳት ተናግረዋል የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ ክፍል ሃለፊ የታሰሩት በነጻ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው እንዲታይ ትእዛዝ ቢያስተላልፍም፣ እስረኞቹ ግን አሁንም ፍትህ አጥተው በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ከታሰሩት መካከል ከ70 አመት በላይ እድሜ አላቸው የከተማው ታላላቅ ሰዎች ይገኙበታል። ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ማሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

1 comment:

  1. why people go to prison when they ask their own right.......
    for how long the voice of Ethiopian people is going to be undermined ?
    we need justice

    ReplyDelete