Saturday, July 27, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር

ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ። ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ከወያኔ መከላከያ ጋር በሉግዲ ባካሔደው ውጊያ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል። በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በቀጠለው ውጊያ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከአምባገነኑ አገዛዝ 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ፣ጠመንጃ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርኳል። በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የአካባቢው ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ባሳየው ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብድ መደነቃቸውንና ድርጅቱ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቃት ያሳየ መሆኑን ገልፀው ፣ ወጣቶችም በዚህ ሃይል ጠላት ማሽመድመድ የሚችል ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲሉ ተናግረዋል። Read more... ኢሕአግ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአውስትራሊያ ሜልበርን ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄደ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በውጭ አገር ካቋቋማቸው ቻፕተሮች መካከል የአውስትራሊያ ሜልበርን ቻፕተር አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ቻፕተሩ የኢሕአግን ሁለንተናዊ የአርበኝነት ትግል በማጠናከር በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ከመሆኑም ባሻገር በአገረ አውስትራሊያ እና በሌሎች አገራት በሚገኙ ሚዲያዎች ተሳትፎ በማድረግና በፓልቶክ የግንባሩ ሰራዊት ለአገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ እየከፈለ የሚገኘውን መስዋዕትነት በማስተዋወቅ ብሎም የቻፕተሩን አደረጃጀት ለማስፋት ለግንባሩ የሚደረገው እገዛ መሻሻል እንዲያሳይ ትልቅ ድርሻም ነበረው። Read more... ወታደራዊ ጥቃት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ሉግዲ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ። የወያኔው አምባገነናንዊ ስርዓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን የግፍና የመከራ እንዲሁም የችግርና የሰቆቃ ዘመን ለማሳጠር ስርዓቱን በግንባር እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ሉግዲ በተባለው አካባቢ ከወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ጋር ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት በተካሄደው ውጊያ 44 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 66 በማቁሰል እንዲሁም ብዛት ያላቸው ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነሙሉ ትጥቃቸው በመማረክ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል። Read more... የውጭ ጉዳይ የኢሕአግ የቻፕተር ኮሚቴዎች ድጋፍ እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ የአለም ሃገራት የሚገኙ የድጋፍ ኮሚቴ ቻፕተሮች ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አስታወቀ። ድርጅታችን ከአሁን በፊት ባካሄደው ኮንፈረንስ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በየሀገራቱ ቻፕተሮች ተቋቁመው ተጠሪነታቸው ከድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ጋር መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት እስከአሁን በጀርመን፣ በአውስትራሊያ፣ በኖርዎይ፣ በስዊድን ፣ በቤልጅየም፣ በካናዳ ተደራጅተው እንቅስቃሴ መጀመራቸው ይታወሳል። Read more... ወታደራዊ ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞ ግንባር ሰራዊት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት ከቀናት በፊት በዋልድባ ሰቋርና አምቦ ጠበል ለሁለት ቀን ባደረገው ውጊያ 46 ገድሎ 64 ማቁሰሉን መዘገባችን ይታወቃል። ጥቃቱ እንቅስቃሴውን በማስፋት በሚያዚያ 15-2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ከወያኔው ፈጥኖ ደራሽ ሐይልና ከፌደራል ጋር በተካሔደው ውጊያ በወረዳ አድርቃይ ልዩ ስሙ አሌ በተባለው ቦታ 17 የጠላት ቅጥረኞችን በመግደልና 24 በማቁሰል ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል። Read more... መግለጫ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ሕ.አ.ግ/ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክና ማንነቱን ስንመረምር ሁሌም አስቀድሞ የሚታየን አትንኩኝ ባይነቱ ፣ ታጋሽነቱ፣ ብልሕና አስተዋይነቱ እንዲሁም ጀግንነቱ መቼም ቢሆን ከሕሊናችን የማይሰወር እውነታ ነው። ይህ ኩሩና ጀግና ሕዝብ ላለፉት 21 ዓመታት ማንነቱን የሚፈታተኑ ኢ- ሰብዓዊና ኢ-ሞራላዊ የሆኑ አስከፊ ግፍና መከራን በሀይል እንዲቀበል አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ከመፈተን ለአንድም ደቂቃ ቢሆን ቦዝኖ አያውቅም። የአካባቢ ምርጫ እየተባለ ለይምሰል ሁነኛ ተወዳዳሪ በሌለበትና የፖለቲካ ምሕዳር በጠበበት ሁኔታ ለግሉ በተቆጣጠረው ሚዲያ ለብቻው ተራ ድስኩር በሚያስተጋባበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አገር አድን ሰራዊት በሚያዚያ 8ና በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም ታሪካዊውን የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ ታች ላይ እያሉ በሚገኙ ሰራተኞች ጥብቃ እየተደረገ ከሚገኘው ከአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት ተመርጠው ከተውጣጡ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ2 ቀን ባካሔደው ከፍተኛ ውጊያ የጠላትን አንገት ያስደፋ በአንጻሩ ወገንን ያኮራ ድል መቀዳጀቱ ይታወቃል። Read more... የኢሕአግ ሰራዊት በዋልድባ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል። የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 ያቆሰለ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያው የተካሄደ ሲሆን በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ ሲሆን፣ በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር ማርኳል። Read more... ከአቶ የዋርካው መንግስቱ በአውስትራሊያ የኢህአግ ተጠሪ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ሜልበርን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ራዲዮ ጣቢያ)

No comments:

Post a Comment