Wednesday, July 31, 2013

አሣ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል 2)

አሣ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል 2) washington-dc-ethiopia July 31, 2013 ናደዉ፣ ከዋሽንግቶን ዲሲ ባለፈዉ ሳምንት “እስቲ ቂማችን ጥቂት እናቆየዉ” በሚለዉ በዚህ አምድ የመጀመርያዉ ፅሁፌ በዳያስፖራዉ ዉስጥ ሰርገዉ ስለገቡ የወያኔ ጨካኝ አገዛዝ አባሎችና ሆድአደር ጀሌዎቻቸዉ ጥቂት በጣም ጥቂት ለማለት ሞክሬአለሁ።፦ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ ሆነና፣ ተላላኪዎቻቸዉ ተደፈርን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸዉን አንድ ወዳጄ ነገረኝ። ላለፉት አስራ አምስት አመታት ያህል እጅግ የተካኑበትን የተቃዋሚዉ ወገን አመራሮችን በስም እየጠቀሱ ጥላሸት መቀባት ዳያስፖራዉን ለመከፋፈል በወያኔ በጀት ተመድቦላቸዉ በሚያሰራጩት አጉራ ዘለል ራዲዮኖቻቸዉ ሲያላዝኑ ዉለዉ አደሩ ማለትንም ሰማሁ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ በተጠቀሱት የወያኔ ተላላኪዎችና ሆድ አደሮች ዉስጣቸዉ ሆኖ ለረጅም ጊዜያት መረጃዎችን ሲሰበስብ በመቆየቱ እነሆ አሁን እንደ መንደርደሪያ አይነት ባለፈዉ ፅሁፍ ዉስጥ ነካ ነካ ለማድረግና ተጠንቀቁ ማንነታችሁን እናዉቃለን አይናችሁን ሸፍኑና እናሞኛችሁ ማለት ከእንግዲህ ወዲያ አይሰራም ተመቸን ብሎ ከወያኔ በሚከፈላችሁ የመንደር ራዲዮ ሠዉን መዘርጠጥ ይቁም ለማለት ብጫ ካርድ ለማሣየት ሞክሬአለሁ፥ ይህ ግን እንደሞኝነት መቆጠሩን በዚህ ሰሞን ይህ ሆድ አደር መቶ አለቃ ያለፈዉን ፅሁፍ በመጥቀስ እንዳበደ ውሻ ግምታዊ ዘለፋውን ለማቅረብ መንገታገቱ ተመልክቻሁ፧Inside Washington Little Ethiopia በዚህ ምክንያት የሆነዉን ሁሉ በማስጃ በተደገፈ ፅሁፍ ቁልጭ አድርጌ ለማቅረብ ወንኩ፧እኔ አሁንም አጠገባቸዉ ነኝ። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች እንገናኛለን። በሚገባም እንተዋወቃለን። ከአጋላጭ ፅሁፎቼ በኋላ በሕዝብ ፊት እዉነቱን በገሀድ ፍርጥ አድርጌ በራሳቸዉ ራዲዮ ላይ ከጋበዙኝ ለመቅረብ ዝግጁ ነኝ። ይህን ካልኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ዛሬዉ የአጋላጭ ትኩረት አቅጣጫዪ ልዉሰዳችሁ። ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ ማነዉ? ምክትል የመቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ አሥመራ ከተማ ቃኘዉ ስቴሽን ይገኝ በነበረዉ የፖለቲካ መምሪያ ዉስጥ በካድሬነት ያገለግል የነበረ በዚያን ወቅት የሥራ ባልደረቦቹን መቆምያ መቀመጫ የሚያሳጣና ከፋፋይና ተንኮለኛ ስለነበር ከአጠቃላይ ባህርይው የተነሳ ትንኩሽ በሚል ቅፅል ስም የሚያዉቁት የሠራዊቱ አባሎች ዛሬ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ይገኛሉ።ከዚያ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘዉ በወቅቱ ከፍተኛ ፩ በሚባለዉ መስተዳድር የአራዳ የአኢወማ ሊቀመንበርና ካድሬ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በከፍተኛዉ መዝናኛ ክበብ እሱ በሚመጣበት ሰአት ብዙዎቻችን ወጣቶች ሹልክ ሹልክ እያልን ከቦታዉ የምንሰወርበትን የብሄራዊ ዉትድርና ጭፍን የምልመላን ሽሽት ወቅት አንደነበር ዛሬ ብዙዎቻችን በቁጭት እናስታዉሰዋለን፤ አሁን ደግሞ ይኸዉ ግለሰብ ማልያዉን ገልብጦ የሌላዉ ጨካኝ አምባገነን አገዛዝ ሰርጐ ገብ ተላላኪ መሆኑ ፧ቀደም ሲል ይህንን ግለሰብ የምናዉቀውን ብዙዎቻችንን አስገርሞናል። ይህ ጓድ አይኑን በጨዉ አጥቦ ጅብ በማያዉቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንደሚባለዉ እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ መጣ።እኛም የሰፈሩ ወጣቶች የዛሬዎቹ ጎልማሶች አገኘነዉ አሁን ድረስ አንድ ጓደኛችን ባገኘዉ ቦታ ሁሉ ለዱላ ይጋበዝበታል እኛም ያለፈዉን እርሳዉ ብለን ገላጋይ መሆናችን አልቀረም። ያለፈዉ በደል ሳያንሰዉ አሁን ደግሞ ሌላ ቁማር ጀመረ፣ራዲዮ ጣቢያና ቤተክርስቲያን ከፈተ ።በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያዊነት ራዲዮ የሚልና ኡራኤል ቤተክርስቲያን፤ ራዲዮ ጣቢያዉን ራሱ ብቻዉን የሚያስተዳድረዉ ሲፈልግ የሚከፍተዉ ሲያሻዉ የሚዘጋዉ፤ ቤተክርስቲያኑንም እንዲሁ ቀዳሽ ቄስ ካገኘ አገኘ ካላገኘ ቅዳሴዉን በካሴት ያስነካዋል፧እሱ ማንን ፈርቶ አገሩ አሜሪካ አይደል! እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ይሏችኋል ይህ ነዉ!ጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ ዛሬም አለ ! በተመሳሳይ ተግባር ላይ፧ ይህ የወያኔ ተላላኪ የዋሽንግተን ዲሲንና የአካባቢዉን ኢትዮጵያዊ ይቅርታ ካልጠየቀ በተጨበጠ ማስረጃ አርጩሜዬን ማንሳቴ እዉነት ሊሆን ነዉ። ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ላለፉት ሀያሁለት አመታት እንደመዥገር ተጣብቆበት ደሙን በመምጠጥ ላይ ያለውን ፋሽስታዊ አምባገነን አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ዜጎች በተለያየ አቅጣጫ በአንድነት ርብርብ በማድረግ ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ከእንደዚህ አይነት ሆድአደር እበላባይ ተርታ አጉራዘለል ግለሰብ ጋር እሰጥ አገባ መግጠሙ ደግ ባይሆንም የሱና የመሰሪ ጓደኞቹ አካሄድ በሕዝባዊዉ ትግል ላይ የሚያሳድረዉ ተፅእኖ ቀላል ባለመሆኑ ቀይ ካርድ ማሳየቱ ወቅቱ የሚጠይቀዉ ቁም ነገር ነዉ። ያለፈዉን የመንደርደርያ ፅሁፍ የተመለከቱ ወገኖች በተለይ ደግሞ በዚህ ግለሰብ ጥቃት የደረሰባቸው ኢትዮጵያዉያኖች ሀብት ንብረታቸውን ተቀምተዉ ያዘኑትን ጨምሮ ራዲዮ ጣቢያው ሲመሠረት አብረዉ አጋር የነበሩና በራዲዮኑ ስም የሚሰራዉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን የማፍረስ ደባና የሚዘረፈዉ የየዋህ አገር ወዳዶች ገንዘብና ንብረት የተነሳ ጥለዉት የሄዱት አባሎቹ የሰጡት አጋላጭ የድምፅና የፅሁፍ ማስረጃ በጄ ገብቷል።ለዚህ ነው የዛሬዉን ርእሴን የመረጥኩበት ሁለተኛዉ ምክኒያቴ፧የንጉሴ ወልደማርያም ሀገር ፍቅር ራዲዮ፣የመቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ ኢትዮጵያዊነት ራዲዮ፧የፀሀዬ ደባልቄ ሰላም ራዲዬ፤ልዩ ራዲዮና የዮሴፍ ግዛቸዉ አንዲት ኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያዎች በዋሽንግተንና አካባቢዉ የሚገኘዉን ኢትዮጵያዊ ከወያኔ አምባገነን ስርዓት ምስረታ ማግሥት ጀምሮ ገንዘቡን በመዝረፍና የትግል ተነሳሽነት ወኔዉን በማኰላሸት የጨካኙን የወያኔ አምባገነን ሥርዓትእድሜ እያራዘሙለት ይገኛሉ። በዚህ ጽሁፍ መደምደሚያ ላይ አንባቢዎቼን ላስገነዝብ የምፈልገዉ አንድ ቁምነገር ፧አለ ፧ይኸዉም መቶ አለቃዉ የወያኔን አምባገነን አገዛዝሥርአት ከማዉገዙ ጎን ለጎን የሚያስተላልፋቸዉ ከፋፋይ የተቃዋሚ መሪዎችንና ታዋቂ አገር ወዳድ ግለሰቦችን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጐደለዉ በአጉራዘለል ቋንቋ መዝለፍ ጥቅሙ ለማን ነዉ? የማንን ጡንቻ ነዉ የሚያፈረጥመዉ የየትኛዉስ የትግል ጎራ ነዉ የሚኮስሰዉ?! ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያኖች የህሊና ፍርድ እተወዋለሁ!የዚህ ግብዝ ማንነት የቆመለትንም አላማና ተልእኮ ማወቅ ያስችላል። ገንዘብ ሲያጣም ሆነ ሲያገኝም የሚያሳብደዉን የጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉን አይን ያወጣ መሠሪ ከፋፋይ እንቅስቃሴዎች ከነማስረጃዎቼ በሚቀጥለዉ ፅሁፊ እመለስበታለሁ ፅሁፎቹም የሚያተኩሩት በሚከተሉት ነጥቦች ዙርያ ይሆናል፦ ፩ኛ፦ቤተክርስቲያን በመክፈት ስለሚያገኘዉ ጥቅምና በዚህ ዙርያ የፈፀማቸዉን አስነዋሪ ተግባራት፣ ፪ኛ፦ከስራ ጓደኞቹ ጋር በመሆን የተሰበሰበ የዕቁብ ገንዘብ ይዞ ስለመሰወሩ ፫ኛ፦በደርግ ዘመን በወገኖቻችን ላይ ያደርስ ስለነበረዉ በደል ፬ኛ፦በሚያሰራጨዉ ራዲዮ ላይ በአንድ ወቅት ሼክ መሐመድ አላሙህዲንን በመዝለፉ ምክንያት ስለተመሰረተበት ክስና አማላጅ ልኮና እግር ላይ ወድቆ ይቅርታ ስለመጠየቁ ፭ኛ፦ደራሽ ግብረሀይል ብለዉ በድርቅ በተጐዱ ወገኖቻችን ስም የተሰበሰበዉን ከሁለት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ከንጉሤ ወልደማርያምጋርበመሆንዘርፈዉስለተሰወሩት ገንዘብ ፮ኛ፦በቅንጅት መሪዎች መፈታት ማግስት ኢንጅነር ኃይሉ ሻወልን በማጥመድ ይህንን ተትሎ ከመሠል ጓደኞቹ ጋር በመሆን ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት የተጫወተዉ ከፍተኛ ሚና ፯ኛ፦ቀደም ሲል ከዋሽንግተን ዲሲ በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፈዉን የቪኦኤ ራዲዮ ጣቢያ ለማዘጋት የተቃዉሞ ሰልፍ በማደራጀት ስላስተባበዉ እንቅስቃሴ ፰ኛ፦እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ከቅርብ አመታት ወዲህ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ሕዝቡን ለትግል በማነሳሳት ላይ የሚገኙት የኢሕአፖ ወጣቶች ክንፍ ዉስጥ ሰርጎ በመግባት ከእናት ድርጅታቸዉ ለመነጠል የሚያደርገዉን እንቅስቃሴና መሰል ወያኔያዊ ተልዕዎቹን በዝርዝር እንመለከታለን ዉድ ለአንባቢዎች፦ እነዚህን የመሳሰሉ የዳያስፖራውን አንድነትና ትግል በወያኔ የምፅዋት ገንዘብ ሽባ የሚያደርጉትን አረመኔ ሆድ አደር ተላላኪዎች በቃችሁ እንበላቸዉ!!! ክፍል ፫ ይቀጥላል፦ ናደዉ። http://ecadforum.com/Amharic/archives/9155/

No comments:

Post a Comment