Tuesday, July 30, 2013

እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ለመባል ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡

"እውነተኛ ኢትዮጵያዊ" መባልን አማሮት? እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ለመባል ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡ የአባባ ጃንሆይን የይሁዳ አምበሳ ያረፈበት የድሮው ሰንደቅ ዓላማ ተሸክሞ መቆዘም በተደጋጋሚ ድንበራችን ቀይ ባሕር ነው እያሉ መሸለል፡ ከአማርኛ ውጭ ሌላ የብሔር ቋንቋ የሚናገር ወይም አማርኛ አልችልም ያለ ኢትዮጵያዊን "ዘረኛ" ብሎ መዝለፍ፡ አንድ ህዝብ፡ አንድ ቋንቋ፡ አንድ ሃይማኖት፡ አንድ ባህል፡ አንድ አገር በሚሉ ቀረርቶዎች ሠዉን ማደንቆር፡ የተከፋፍለናል ዘፈን አስሬ እየከፈቱ ማላዘን፡ በኢትዮጵያ ድሮ ቀረች፡ አሁን ኢትዮጰያዊነት ረክሷል እያሉ መብሰክሰክ፡ ብብሔር የተደራጁ የልማትም ኾነ የፖለቲካ አደረጃጀቶች ጎሰኛ፡ ጎጠኛ፡ መንደርተኛ፡ ከሃዲ፡ ባንዳ ብሎ መፈረጅ፡ እናቴ ሀገሬ፡ ጋራሽ ሸንተረሩ፡ እሪ በይ ሀገሬ፡ እያሉ የግጥም ስንኞች መደርደር፡ ሐበሻ፡ ሐበሻነቴ፡ ሓበሻዊነቴ የሚሉ ቃላቶች በየንግግሩ መሐል መሰንቀር፡ የሚሉትን ይሞክሩ፡ በአቋራጭ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ተብለው ቁጭ። ኣሉላ ሰለሙን

No comments:

Post a Comment