ማስታወቂያ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ከችሎቱ ጀርባ ያለው ጥቁር ዳኛ ማነው?,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
በርዕዮት ላይ የተላለፈባትን የአስራ አራት አመት እስር አስመልክቶ ከአመት በፊት አንድ ተባራሪ መረጃ ደርሶኝ ነበር፡፡ መረጃው ችሎቱን ይመራ የነበረው ዳኛ ተጽፎ የተሰጠውን የፍርድ ውሳኔ ያነበበ መሆኑን የሚገልጽ ነበር፡፡ ፍርዱ በተላለፈበት ዕለት የነበረው የዳኛው ሁኔታ መረጃው እውነት ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዲያድርብኝ አድርጓል፡፡ ስለሆነም በርግጥ ዳኛው የተጻፈለትን ነው ያነበበው? ከሆነስ ማነው ጽፎ የሰጠው? የሚሉትን ሁለት አበይት ጥያቄዎች ለመመለስ ተጨባጭ ማስረጃዎችን ማግኘት አስፈላጊ ነበር፡፡
በዚህ ሂደት ያገኘኋቸው ሁለት ማስረጃዎች አሉ፡፡ አንደኛው በዳኛው የተነበበው የጥፋተኝነት ውሳኔ የእጅ ጽሁፍ ሲሆን ሁለተኛው የዳኛው የእጅ ጽሁፍ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ማስረጃዎች በእርግጥም የጥፋተኝነት ውሳኔው በዳኛው እንዳልተጻፈ የሚያረጋግጡ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡
ለዳኛው ጽፎ የሰጠው ማነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ማስረጃ ለማግኘት ያደረግኩት ፍተሻ ግን እርግጥ ያለ መልስ ሊያስገኝልኝ አልቻለም፡፡ በመሆኑም እኔ የደረስኩበትን እውነት ይፋ አድርጌ የጸሀፊውን ማንነት ለማወቅ አብረን ብርበራ እንድናካሂድ መጋበዝ የተሻለ መንገድ እንደሆነ አምኛለሁ፡፡ እናም ርዕዮት የታሰረችበት 30ኛ ወር በሚሆንበት ታህሳስ 14 2006 ዓ.ም መረጃው ይፋ ይሆናል፡፡

No comments:
Post a Comment