የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን ስራዎች የሚገልጽ
“የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከትናንት እስከ ዛሬ ” በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አዘጋጅቶ አውጥቷል።
ዘጋቢያችን እንደገለጸው በተሻሻለው የፀረ-ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 29 መሰረት በሙስና ወንጀል ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በሙስና ወንጀል የተገኘ ተመጣጣኝ ንብረት እንዲወረስ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይሰጣል ቢልም ፍርድ በቶች ይህን ለማስፈጸም እየተባበሩ አይደለም ብሎአል።
ኮሚሽኑ እስካሁን ድረስ በፍርድ ቤት እንዲታገዱ ጥያቄ ቀርቦባቸው ያልታገዱ በማለት ከጠቀሳቸው መካከል 1 ሚሊዮን 898 ሺ 495 ካሬ ሜትር መሬት፣ 151 ተሽከርካሪዎች፤ 74 ሚሊዮን 434 ሺ 240 ብር ከ70 ሳንቲም፤ 15 ሚሊዮን፣ 115 ሺ 26 ብር ከ41 ሳንቲም፤ 166 ቤቶች፣ 172 ሄክታር የእርሻ መሬት፣ 35 ድርጅቶችና 2 ፋብሪካዎች ይገኙበታል።
ኮሚሽኑ ከተቋቋመት ጊዜ ጀምሮ ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ በፍርድ ቤት ተወስኖ ገቢ ካልሆኑት መካከል 667 ሺ 25 ካሬ ሜትር መሬት፣ 26 ተሽከርካሪዎች፣ 2 ሞት ብስክሌቶች፣ 43 ሚሊዮን 99 ሺ 306 ሚሊዮን ብር ይገኙበታል።
ተመላሽ ከሆኑት መካከል ደግሞ ከብሄራዊ ባንክ ወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የተሰረቀ 81 ኪሎግራም ወርቅ እና ከዱባይ ተይዞ የተመለሰ 15 ኪሎ ግራም ወርቅ ተጠቅሰዋል።
በጸረ ሙስና ልዩ የስነ ስርዓት ህግ መሰረት በሙስና የተገኘ ሀብት እንዲወረስ ለማድረግ በቅድሚያ በሙስና ወንጀል የተገኘነው ተብሎ የሚገመት ንብረት ላይ የእግድ ትእዛዝ ይሰጣል። ኢሳት

No comments:
Post a Comment