አንለያይም አንድ ነን የሚለውና ስለኢትዮጵያ አንድነት " በአብዛኛው " የሚጨነቀው ትውልድ ወያኔ ከበረሃ ውንብድና ወደ ከተማ ውንብድና ከመግባቱ አስቀድሞ ነፍስ ያወቀው ወይም ሃገራዊ ኃላፊነት የሚሰማው ስለመሆኑ በፌስቡክ የውይይት መድረክ ላይ ያለውን ታዳጊ ትውልድ ውይይትን በማንበብና ቀርቦ በመወያየት በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።
ከሁሉ ከሁሉ የሚገርመኝ፡ በዚህ በዲያስፖራው ወይም የስደተኛው ሕብረተሰብን ሁኔታ ስትመለከቱ፡ ሃገራዊ ውይይት የሚካሄደው በአብዛኛው በፓልቶክ ሆኖ ሳለ፡ አባት የፖለቲካ ጥገኛ፤ ስደተኛ ሆኖ ስለፋሽስት ወያኔ አምባገነንነት እየገለጸና የትግል አቅጣጫ መሆን ያለበት፡ እንዲህ ነው፤ የአንድነታችንን ጠላት ሕወሃትን መታገል ወይም መዋጋት ያለብን በእንደዚህ መልኩ ነው ቅብጥርሶ በማለት በሞራል ይናገራል፤ ይፎክራል። የልጆቹን ወያኔነት ፈጽሞ አያውቅም፤ ልጆቹን ስለፋሽስት ወያኔ መሰሪነትና ተንኮል ሳያስተምር የፓልቶክ ተዋናይ ሆኖ የታገለ ይመስለዋል።
- ወጣት ልጆቹ ደግሞ ወደ ስደቱ ዓለም ከእናትና አባታቸው ጋር ወደ ስደቱ ዓለም ሲቀላቀሉ የመለስ ዘባንዳዊን ፎቶግራፍ ፌስቡክና መኝታ ቤታቸው ውስጥ ሰቅለው፡ ወያኔ በየትምህርት ቤቱ የወያኔ አዲሱን የግንጠላና የብሔረሰባት መከፋፈያ CARICULUM የሞላቸውን ውንብድና ወይም የብሔር ፖለቲካ እንደ በቀቀን በግምባር ስታገኟቸውም ሆነ አንዳንድ የፓልቶክ መነታረኪያ ክፍል በወያኔ ካድሬዎች ስለተመሠረተላቸው፡ በመሃል ላይ በቀልድም ይሁን በኮስታራ አነጋገር ይህንንኑ ሲዘላብዱና ነፋስ እንዳንገላታት መርከብ ሲዋዥቁ መስማት እራስን ያሳምማል ውሏቸውም ወያኔ ኤምባሲ ከሚቃርሙ የወያኔ ካድሬዎች ጋር ነው። አባት አያውቅም፤ እራሱ ከመሳተፉ አስቀድሞ የሚያውቀውን ለልጆቹ ሳያሳውቅ አደጋ ላይ ያለ ወላዋይ ስደተኛ። ለማስረዳትና ከስህተታቸው ለማዳን ከጣራችሁ፡ የሚታያቸው በዲያስፖራ የወያኔ ኤምባሲ ካድሬ ወያላዎች የሚታደላቸው ጥቅም ንዋይ እንደሚቋረጥ ነው።
በእኛ ትውልድ አባቶቻችንም ሆነ መምሕራኖቻችን፡ ከምንም ነገር በፊት ያስተምሩን የነበረው፡ የነጻነታችን መሠረት የአንድነታችን ጽናት እንደነበር ነው። ፋሽስት ኢጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወርር ኢትዮጵያውያን የዘመናዊ አስተዳደርና በትምህርት የበሰለ ምሁር ሳይኖር፡ ስለአንድነት የታገሉት እርስ በርሳቸው ተጨቋቁነውና የበታችነት ስሜት ተሰምቷቸው አልነበረም።
የአሁኑ ትውልድ የዜግነት ውርደቱን እያየ፡ የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ጸንቶ፤ ታየ ሕዝባዊነት ብሎ የሚዘምር ባይተዋር ትውልድ ነው።
ካስተዋለ ግን በቁሙ መዋረዱን ተገንዝቦ ለመታገል፡ በየተቃዋሚው ያሉት አዋቂዎችን ፈለግ ተከትሎ፡ ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ኢትዮጵያ ክብሯን ለማስመለስ በትጥቁም ይሁን በሰላማዊ ትግል ከሕወሃት ጨካኞች መዳፍ ለማስመለስ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ በተሰለፈና ኢትዮጵያን ባዳነ!!!
ተቃዋሚ የትጥቅም ሆነ የሰላማዊ ትግል መሪዎች፡ ትኩረታቸውና የፖለቲካ ዋናው ፕሮግራማቸው መሆን ያለበት፡ ወያኔ የቀመረውን የፈጠራ ታሪክ፡ ወደ እውነተኛው የአንድነት ታሪክ መመለስና ማስተማር መጻፍ የግድ ነው። የሰሞኑ አስደንጋጩ ዜና የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን በግልጽ ሲፈረም የተወሰኑ በአካባቢው ያሉና የትጥቅ ድርጅቶች ብቻ ናቸው የአቋም መግለጫ እንኳን ያወጡት። የወቅቱ ታዳጊ ወጣት የኢትዮጵያ ድንበርና የባሕር ግዛት የት ድረስ እንደሆን እንኳን እንዳይማር የታፈነ ከመሆኑ የተነሳ፡ ያተኮረው፡ በፌስቡክ አምድ ላይ ልጠፋ ነው፤ መሰደድ አምሮኛልና እናንተ ጋር እንዴት ነው የምመጣው? ሴቶችና ወንዶች .....ወዘተርፈ
ልብ ያለው ልብ ይበልና ሁሉም ነገር ኢትዮጵያን ወደ ማዳን
ሞት ለፋሽስት ወያኔ
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!!!!!!!!!!!!!!
No comments:
Post a Comment