በሙስና የተጨማለቁት አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ደ/ፂዮንና ፀጋዬ በርሄ ከጁነዲን ጋር እንደተደራደሩ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። መጀመሪያም ወ/ሮ ሃቢባ የሰሩት ወንጀል ኖሮ አይደለም የታሰሩት ያሉት ምንጮቹ አቶ ጁነዲን ከስልጣን ለማንሳት ሲባል ብቻ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል። ጁነዲን ባለቤታቸው ከታሰሩ በኋላ በስልጣን ላይ እያሉ እንዲያውም ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ሚሚ ስብሃቱ በምታዘጋጀው ራዲዮ ጣቢያ « ጁነዲን መታሰር አለባቸው፤ መንግስት እስከ አሁን እርምጃ የማይወስደው ለምንድነው?..ባለቤታቸው አሸባሪ ናት» በማለት የፍ/ቤትን ነፃነት ጭምር በሚጋፋ መልኩ ቅስቀሳ ይካሄድ እንደነበረ ምንጮቹ አስታውሰዋል። አቶ ጁነዲን ከአገር ከወጡ በኋላ እውነቱን እያወቁ መደራደራቸውና ባለቤታቸውን በማስፈታት ሌሎች ንጹሃን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ በተዘዋዋሪ በመፍረድ የኢህአዴግና ካንጋሮው ፍ/ቤት ተባባሪ መሆናቸው አሳዛኝ ነው ብለዋል ምንጮቹ።
አቶ ጁነዲን ምናልባትም « ባለቤቴ በፍ/ቤት ነፃ ተባለች» በሚል በኢትዮጲያ የፍትህና የፍ/ቤት ነፃነት እንዳለ አስመስለው ሊናገሩ እንደሚችሉ ማረጋገጫ የለም ያሉት ምንጮቹ አክለውም ጁነዲን ምንም አሉ ምን በስልጣን እያሉ ለፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው እንደማይቀር መታወቅ አለበት ብለዋል።
No comments:
Post a Comment