Tuesday, November 4, 2014

ከሻእቢያ ጉያ መኖር ይበቃል። ያሉ አምስት የአማራ ንቅናቄ አባላትን ሻእቢያ ሲገድል ሁለቱን አፍኖ መውሰዱ ታውቋል። ምርጥ መረጃ


Postby አስጨናቂ ካሳበል » 

Imageከአስመራ የመጣውን መረጃ ከዚህ በመቀጠል እንዳለ አውርጀዋለው። 
ከሻእቢያ ጉያ መኖር ይበቃል። ያሉ የአማራ ንቅናቄ አባላት ሻእቢያ ከኤርትራ ወጥቶ ማንኛውም የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅት እንዲታገል አሊያም አንድም የኢትዮጵያ አከባቢ እንዲቆጣጠር ፈቃደኛ አይደለም። ሻእቢያ እና ወያኔ ማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ከኤርትራ እንዲወጣ አይፈልጉም። እዛው አስመራ ተቀምጠን አለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እንድንሆን ይፈልጋሉ። ኤርትራ ውስጥ ተቀምጦ ወያኔን እለውጣለሁ ማለት ዘበት ሲሆን በዋዛ ፈዛዛ እድሜ መጨረስ ነው።ታግለን ወያኔን እንጥላለን ብለው ኢርትራ ያሉ ታጋዮች ከ15 አመት በላይ ተቀምጠውው ካለምንም ጦር አሊያም ውጊያ አርጅተዋል። 
ለመዋጋት ካሰብክ አሊያም ወያኔን በተኩስ ለመግጠም ካሰብክ በፍጹም አይፈቀድም ጭራሹኑ ይህ አይነት ሃሳብ ያለው ሰው ተይዞ ይገደላል ይታሰራል ከሰው እንዳይገናኝ ይደረጋል ለዚህም ባለፉት ወራቶች የተገደሉት አምስት የአማራ ንቅናቄ አባላት እና ታፍነው ወደ እስር ቤት የተወሰዱት ሁለቱ ታጋዮች በቂ ምስክሮች ናቸው። 
ታጋይ ነህ ኢትዮጵያን ነጻ ታወጣለህ እየተባልን የሻእቢያና ወያኔ መጫወቻ ሆነናል።ሻእቢያ ያለውን ገቢ ለማስጠበቅ እና ለወያኔ እና ለራሱ የጥቅም ማስከበሪያ እንጂ ለኢትዮጵያውያን የተቃዋሚ ድርጅቶች አስቦ አይደለም ከግብጽ እና ኳታር በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገቢ በድርጅቶቹ ስም በመሰብሰብ ለድርጅቶቹ አንድ ሚሊዮን ዶላር ሳያወጣ ታጋዮቻችንን በጉልበት ስራ እያደከመ ሞራላውን እየገደለ ነው። 


No comments:

Post a Comment