Saturday, November 1, 2014

በክበር ሲጠበቁ የነበሩት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስላጣን ለዳግም ህክምና ሳውዲ አረቢያ ሾልከው ገቡ ።

በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞን ህመሙ ጠንቶባቸው ከሁለት ወር በፊት በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕልና ተጭነው በድበቅ ለህክመና ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የሚገኝ አንድ «ቡግሻን» hospital እየተባለ የሚጠራ ሪፈራል ሆስፒታል የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና ቢደረግላቸውም የባለስልጣኑ የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ ባለማሳየቱ ለዳገም ህክምና ቀጠሮ ተሰቷቸው ከሳምታት ቆይታ በሃላ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል ,ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬም የአቶ በረከት ጤንነት መልካም ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ምንጮች የሆስፒታሉን የምርመራ ውጤት አብነት ጠቅሰው ይናገራሉ ። አቶ በረከት በጤነታቸው መታወክ ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚገልጹት እንዚህ ውስጥ አዋቂዎች ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚስጠር ለህክምና መግባታቸውን ተከትሎ በተለያዩ ድህረገጾች ዜናው በስፍት መናፈሱ በውስጣቸው በተፈጠረው አለመረጋጋት በልባቸው ምት አለመስተካከል በወቅቱ በቂ ህክማና መውሰድ እናዳልቻሉ ታውቋል። የአቶ በረከት የጤነንት ሁኒታ ዛሬም አስተማማኝ እንዳልሆነ የሚያውሱ እንዚህ የአይን እማኞች ከእለት ተዕለት የባለስልጣኑ የአካል መጠን በማይጠበቅ ሁኔታ መቀነስ እና የፊታቸው ገጽታ መለዋወጥ በውስጣቸው መልካም ነገር እንደማይታይ ያሳብቃል ብለዋል።

የአቶ በረከት ስሞኦን ህይወት ለመታደግ የአቅማቸውን ያህል ጠረት እያደረጉ የሚገኙ «ቡግሻን» hospital የሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ዶክተሮች ሰለበሽታው አደገኝነት ግንዘቤ በማስጨበጥ አቶ በረከት ከተለያዩ መጠጦች እና አይምሮ አደዛዥ እጾች መራቅ እንዳለባቸው እና የጤነንታቸው ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ ከሲደርስ እረፍት መስውሰድ እንደሚገባቸው ሙያዊ ምክሮቻቸውን ለገሰዋቸዋል። ይህ በዚህ እንዳለ አቶ በረከት ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲያቀኑ የህክምና ውጪያቸውን እየሸፈኑ ከሚገኙት ሼክ አላሙዲን ባሻገር ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ባለስልጣናት ሚስጠር መሆኑ አያሌ ወገኖችን በስፋት እያነጋገር ነው ። ከሁለት ወር በፊት አቶ በረከት እኩለ ለሊት ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕልና በድብቅ ለህክማን መግባታቸው ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወሬው የደረሰው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዘ-ሃበሻ እና ጎልጉል ድህረገጾች በተለቅቁ መረጃዎች መሆኑን የሚናገሩ ምንጩች ለሁለተኛ ግዜ ዳግም ህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲመለሱ በሼክ አልሙዲን በኩል በክበር «በፕሮቶኮል» ሊገቡ እንደሚቸል በወቅቱ ከጅዳ ቆንሳል ጽ/ቤት የወጡ መርጃዎች ቢያረጋግጡም የአቶ በረከት ስሞኦን እንደ ተለመደ በድብቅ ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባት ባለስለስልጣኑ በውስጥም በውጨም ጥሩ ወዳጅ እንደሌላቸው የሚነገረውን ሃቅ ያጠናክረዋል ብለዋል ።
አቶ በረከት ትላንት በተደረገላቸው ምርመራ የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው የሚገልጹ የሆስፒታል መረጃዎች ባለስልጣኑ የተሰጣቸውን ምክር እና የተለያዩ መደሃኒቶቻቸውን ይዘው ከሆስፒታሉ ውጭ ወደ ሚገኘው ምስጢራዊ ማረፊያቸው ማቃናታቸው ተገልጾል፡ ይህ በዚህ እንዳለ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና መስረት አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ ማምሻውን ለአስቸኳይ ጉዳይ ህክምናቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልሱ ምስጢራዊ መረጃዎቻችን አክለው አረጋግጠዋል ።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi

No comments:

Post a Comment